የ London Court of International Arbitration በሀገራችን የግልግል ዳኝነት ማዕከል ሊከፍት በሚችልበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት ተደረገ
**************
ከታች ባለው link የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ 👇👇👇👇👇👇👇
t.me/ethiolawblog
t.me/ethiolawblog
t.me/ethiolawblog
አለምአቀፍ የግልግል ዳኝነት ተቋማት በሀገራችን መስራት እንዲችሉ ያሉትን አስቻይ ሁኔታዎችና የመንግስትን ቁርጠኝነት በማሳየት የ London Court of International Arbitration (LCIA) በሀገራችን ቅርንጫፍ በሚከፍትበት ሁኔታ ዙሪያ ከለንደን አለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ማዕከል የአፍሪካ ካውንስል ፕሬዚዳንት Mr. Kamal shah ጋር በበይነ መረብ ውይይት ተከናውኗል፡፡
ውይይቱ በክቡር የመንግስት ህግና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስር ዴኤታ አቶ በላይሁን ይርጋ የተመራ ሲሆን በዋናነት LCIA በሀገራችን ቅርንጫፍ መክፈት በሚያስችሉት ምቹ ሁኔታዎችና ሊኖሩ የሚችሉ የጋራ ተጠቃሚነት እድሎች ዙሪያ በማጠንጠን ተካሂዷል። በተጓዳኝም ሌሎች በፍትሐብሄርና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሊኖሩ በሚችሉ የትብብር ማዕቀፎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይትም ተደርጓል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በውይይቱ እንደገለጹት አማራጭ አለመግባባት መፍቻ አገልግሎት የሚሰጡ አለም አቀፍ ተቋማት በሀገራችን አገልግሎት ለመስጠት ቅርንጫፍ ቢከፍቱ ወይም ከሀገራችን ተቋማት ጋር በመቀናጀት በጋራ ቢሰሩ ሊኖራቸው የሚችለውን የጋራ ተጠቃሚነት ያነሱ ሲሆን ይህም ከመስከረም 9-10 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው 11ኛው የምስራቅ አፍሪካ አለምአቀፍ የግልግል ዳኝነት ጉባኤ /EAIAC/ ወቅት ጉዳዩን አስመልክቶ ከ LCIA ጋር የተጀመረው የጎንዮሽ ውይይትን ውጤታማ ለማድረግ ውይይቱ አጋዥ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
አክለውም በሂደቱ የተሳተፉ የሚመለከታቸው የፍትህ ሚኒስቴር የሰራ ኃላፊዎች ሀገራችን ከግልግል ዳኝነት ጋር በተያያዘ ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን ለማስቻል እየሰራች ያለችውን ዘርፈ ብዙ የህግና ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎች፣ በአፍሪካ ህብረትና በተ.መ.ድ. እና ሌሎች ቀጠናዊ ትብብሮች ያለንን የተቋማት መዳረሻነት ልምድና ተመራጭነት፣ እንዲሁም በቅርቡ የተደረጉ የኢኮኖሚ ሪፎርሞች እንደ LCIA ያሉ መሰል አለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ተቋማት እንዲሰሩ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን አንስተዋል፡፡
Mr. Kamal shah በበኩላቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ ያደረገችውን የህግ ለውጦች እና የመንግስት ቁርጠኝነት አድንቀው ዘርፉ የሚፈልገውን የተደራሽነት ጉዳይ ለመፍታት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካለው ሰፊ መዳረሻነትና አስተዋጽኦ አንጻር ሀገሪቱ በምስራቅ አፍሪካ ያላትን ቀዳሚ ተመራጭት በጉልህ የሚያሳይ እንደሆነ እና እነዚህን ለውጦች ከግምት በማስገባት LCIA በሀገሪቱ ቢሰራ የተሻለ እንደሚሆን መረዳታቸውንና ቅርንጫፍ የመክፈቱን ውሳኔ ከሚመለከታቸው የማእከሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመነጋገር እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ ውይይቱ ሀገሪቱን ተመራጭ የግልግል ዳኝነት መዳረሻ ማዕከል ለማድረግና የግልግል ዳኝነት ዘርፉን ለማሳደግ መንግስት ያለውን ከፍተኛ ቁርጠኝነትና ተግባራዊ እርምጃዎች በማስታወስ እንደ LCIA እና መሰል አጋሮች ጋር በመስራት የሀገር ውስጥ ተቋማትን ከእነዚህ ማዕከላት ጋር በመቀናጀት እንዲሰሩ ለማስቻል ያለውን ዝግጁነት በመግለጽ በዚህ ረገድ LCIA ጋር ቅርንጫፍ ከፍቶ ከመስራት ባለፈ የአማራጭ አለመግባባት ዘዴዎችን ትግበራ ለማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮችና ከተቋም አቅም ግንባታና ቴክኒካዊ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ሊኖሩ በሚችሉ ቀጣይ የግንኙነት ምዕራፎች ዙሪያም መግባባት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቅቋል፡፡