የፍርድ ቤት ውሣኔዎችና ትዕዛዞችን ያለመፈጸም የሚያስከትለው የወንጀል ተጠያቂነት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 51 እና 52 ላይ እንደተመለከተው:-
በማንኛውም ፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ እና ትዕዛዝ በህግ እስካልተለወጠ ድረስ የፀና ሆኖ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸዉን ዉሳኔዎች ወይ ተእዛዞች በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ዉስጥ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
በማንኛዉም ክልል ዉስጥ የሚገኝ የመንግስት አካል፣ ተቋም ወይም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ወይም ማንኛዉም ሰው ውሳኔዎቹን ወይም ትእዛዞቹን የመፈጸም እና የማስፈጸም ግዴታ አለበት።
ማንኛዉም ሰዉ በዚህ አዋጅ የተጣለበትን ግዴታ የማይወጣ ከሆነ በዚህ አዋጅና አግባብ ባለው ሌላ ህግ ተጠያቂ ይሆናል።
የፍርድ ቤት ወይም የዳኞችን በነጻነት መስራት የሚጋፋ ወይም በዳኞች ላይ ተጽእኖ የሚያደርግ ወይም ለማድረግ የሞከረ ማንኛው ሰዉ በሌላ ህግ ከፍ ያለ ቅጣት ከሌለ በቀር #ከሦስት ወር እሥራት ባላነሰ #ከሁለት አመት ባላበለጠ ጽኑ እስራት ይቀጣል።
የፍርድ ቤትን ትእዛዝ ወይም ዉሳኔ የማይፈጽም ወይም ለመፈጸም መሰናክል የሚፈጥር ወይም ሲጠየቅ ለመፈጻም ተባባሪ የማይሆን ማንኛዉም ሰዉ በሌላ ህግ ከፍ ያለ ቅጣት ከሌለ በቀር ከሁለት አመት በማይበልጥ #ቀላል እስራት ወይም #ከአምስት ሺህ ብር በማይበልጥ ገንዘብ ይቀጣል።
👇
@ethiolawtips