#legalupdates
ለህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ከዚህ በፊት የጊዜ ገደብ ያልነበረባቸው መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባፀደቀው መመሪያ ቁጥር 7 አንቀፅ 79 መሰረት ከፍርድ ቤት እና ከአስተዳደራዊ ውሳኔዎች የሚመነጩ የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄዎች በ 3 ወር ጊዜ ካልቀረቡ ተቀባይነት የላቸውም። በመሆኑም በዚሁ አግባብ መብትን መጠይቅ ይመከራል። ይህ አንቀፅ ከህገመንግስቱ ጋር የሚቃረኑ ህጎችን አይጨምርም እንዲህ አይነቱ ጥያቄ በማናቸውም ጊዜ ሊቀርብ ይችላል።
ይህ የመመሪያው ገደብ የህገመንግስቱን የበላይ ህግ መሆን ይቃረናል የሚል ቅሬታን የሚያስነሳ እና ራሱ መመሪያው ለራሱ ለጉባኤው ለህገ መንግስት ትርጉም ሊቀርብ የሚችልበት እድል አለ።
ምክንያቱም ህገመንግስቱን የሚጥስ የፍርድ ቤት ውሳኔ እና አስተዳደራዊ ውሳኔ ህገመንግስቱን እንደጣሰ እንዲቆይ እድል ይሰጣል የሚል መከራከሪያ ስለሚቀርብበት ነው። በሌላ በኩል ደሞ መብቱ ላይ የተኛ ሰው ህገመንግስታዊ ድንጋጌ ተጣሰ ብሎ ሊመጣ አይገባም የሚል መከራከሪያም ይቀርባል።
https://t.me/mulugetalegaloffice
ተወያዩበት