ቁም ኑዛዜ ስጦታ
ሟች ከአንድ በላይ የሆኑ ልጆች ወይም ወራሾች ቢኖሩትና ከነዚያ መካከል ለአንደኛው የኑዛዜ ስጦታ ቢያደርግ የሌሎችን ወራሾች ከሟች ውርስ መነቀል አያስከትልም፡፡ ይህንንም የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 913 የኑዛዜው ቃል የተናዛዡን ተቃራኒ ሀሳብ የሚገልጽ ካልሆነ በቀር ከውርስ ሀብት አንድ ድርሻ ወይም አንድ ንብረት ሟቹ ለወራሾቹ መስጠቱ ተራ የሆነ የክፍያ ደንብ እንጂ እንደ ኑዛዜ ስጦታ ነው ተብሎ አይቆጠርም፡፡
በፍ/ብ/ሕ/ቁ ከአንቀጽ 1117 ጀምሮ ያሉት ድንጋጌዎች አግባብነት አላቸው አንቀጽ 1117 አባትና እናት ወይም ሌሎች ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆች ለልጆቻቸው እና ሌሎች ተወላጆች ሀብታቸውን ለመስጠትና ለማከፋፈል እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡ ይህ ክፍፍል ሥርዓት አንድን ተወላጅ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዳት ደርሶበት እንደሆነ የስጦታ አከፋፈሉ እንዲቀር ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችል በአንቀጽ 1123 ተደንግጓል፡፡
አንቀጽ 1123/1/ ሲነበብ “በስጦታ አከፋፈል ውስጥ ተቃራኒ ቃል ከሌለ በቀር ወደታች ከሚቆጠሩ ተወላጆች አንዱ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዳት ደርሶበት እንደሆነ የስጦታ አከፋፈሉ እንዲቀር ለመጠየቅ ይችላል”
ሰ/መ/ቁ 32337 ቅጽ 5፣ ፍ/ህ/ቁ. 882፣ 913፣ 2428፣ 2443