የመቃወም አቤቱታ (ከውሳኔ በኋላ የሚቀርብ ክርክር ሥነሥርዓት)
================
1 • ተካፋይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ውሳኔ መብቴን ይነካል በማለት አስቀድሞ ለአንድ ወገን የተሰጠውን ውሳኔ ለማሰረዝ በመቃወም አመልካች የሚቀርብ አቤቱታ ነው።
የመቃወም አቤቱታ ሲቀርብ ክርክሩ የሚካሄደው በመቃወም አመልካች እና አስቀድሞ በተሰጠው ውሳኔ ተጠቃሚ በሆነው የመቃወም ተጠሪ በሚባለው ወገን መካከል ሲሆን የዚህ ዓይነቱ ክርክር የሚቀርብበት እና የሚመራበት ስርዓት እንዲሁም የዚህ ዓይነቱን ክርክር የሚሰማው ፍርድ ቤት ስላለው ስልጣን በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ከቁጥር 358 እስከ 360 ተመልክቷል፡፡ የመቃወም አቤቱታው መቅረብ የሚገባው በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 222 እና 223 ድንጋጌዎች መሰረት ክስ እና የማስረጃ መግለጫ የሚቀርብበትን ስርዓት መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ በግልጽ ተደንግጎአል፡፡
የመቃወም አቤቱታው እና የማስረጃው ቅጂ የመቃወም ተጠሪ ለሆነው ወገን እንዲደርስ መደረግ የሚገባው መሆኑን ከመግለጽ በስተቀር የመቃወም ተጠሪው የጽሁፍ መልስ እና የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚገባው በእነዚህ ድንጋጌዎች ላይ በግልጽ የተጻፈ ባይሆንም የመቃወም ተጠሪ የሆነው ወገን በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 234 ድንጋጌ መሰረት ለቀረበበት የመቃወም አቤቱታ ያለውን የመከላከያ መልስ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚገባው ስለመሆኑ ከቁጥር 360(1) እና (2) ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተለይም የመቃወሚያው ክርክር የሚሰማው የመጀመሪያው ክርክር በተሠማበት ስነ ስርዓት መሰረት ስለመሆኑ በቁጥር 360(2) የተመለከተው አስገዳጅ ድንጋጌ በቀጥታ የቀረበ ክስ እና ክርክር የሚስተናገድበትን ስርዓት በተመለከተ በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከቱት መሰረታዊ ድንጋጌዎች የመቃወሚያ ክርክርን በማስተናገድ ረገድም በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጻሚ ሊደረጉ የሚገባቸው መሆኑን በግልጽ የሚያስገነዝብ ነው፡፡
በዚህ ድንጋጌ የተመለከተው የክርክር አመራር ስርዓት ዓይነተኛ ዓላማ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች እኩል ዕድል እንዲኖራቸው እና በተለይም የመቃወም አመልካች የሆነው ወገን የክርክሩ ተካፋይ ባልነበረበት ጊዜ የቀረበውን የመቃወም ተጠሪ ወገን የሰው እና የሰነድ ማስረጃ በመስቀልኛ ጥያቄ እና በማስተባበያ ክርክር ጭምር የመፈተን ዕድል እንዲያገኝ ለማስቻል እንደሆነ ይታመናል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 86398 ቅጽ 16፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 222፣ 223፣ 350-360
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 አንድ የክርክሩ ተካፋይ መሆን የሚገባው ሰው የክርክሩ ተካፋይ ሳይሆን ውሳኔ ተሰጥቶ ከሆነ እና ውሳኔውም ያረፈው በአንድ የክርክሩ ምክንያት በሆነ ንብረት ላይ ሁኖ ይህንኑ የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነ ወገንን መብትና ጥቅም የሚነካ መሆኑ ከተረጋገጠ ፍርዱ ይኸው ወገን ባለበት እንዲታይና በሕግና በማስረጃ የተደገፈ ሁኖ ሲገኝ እንዲነሳለት የሚደነግግ ነው፡፡ አቤቱታው የሚቀርብበት ሥርዓትም በቁጥር 359 ስር በተመለከተው መንገድ መሆን እንደአለበት የተቀመጠ ሲሆን ይህ ድንጋጌ የመቃወሚያ አቤቱታ አቀራረብ በክስ አመሰራረት አይነት ሁኖ ማስረጃ ዝርዝር ሁሉ ይህንኑ ስርዓት ማሟላት እንደአለበት ያስገነዝባል፡፡ የዚህ ድንጋጌ ይዘቱና መንፈሱ ሲታይ ክርክሩ መኖሩን ከጅምሩ እያወቀ ውጤቱን በመጠበቅ ከፍርዱ በኋላ የፍርድ መቃወሚያ የሚያቀርበውን ወገን አቤቱታውን በመቀበል ለማስተናገድ አስፈላጊ ያለመሆኑን ሁሉ ያስገነዝባል፡፡