የቀብድ ህጋዊ ውጤት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
1 ቀብድ ሻጭና ገዥ በተነጋገሩበት ጉዳይ ላይ ውል መፈፀማቸውን እርግጠኛ ሲሆኑ የሚቀባበሉት ገንዘብ በመሆኑ ይህን ማድረጋቸው ገንዘቡን ለመቀባበላቸው ብቻ ሳይሆን ውሉን ለመዋዋላቸውም ማስተባበያ የማይቀርብበት ማስረጃ መሆኑን የፍትሀ ብሄር ህግ ቁ 1883 ይደነግጋል።
ገዥና ሻጭ አንድን ቤት ሲሻሻጡ በፍትሀ ብሄር ህግ 1723(1) ስር የተመለከተውን ፎርም ባያሟሉም ሻጭ ለዚሁ የሽያጭ ውል ማስፈፀሚያ ቀብድ መቀበሉ ከተረጋገጠ በማያከራክር ሁኔታ ውሉ መደረጉን ያረጋግጣል። አንድ ውል የህጉን ፎርም ካላሟላ በህግ ፊት የማይፀና ይሆናል ነገር ግን በልዩ ሁኔታ የቀብድ ገንዘብ ክፍያ ካለ ውሉ የህጉን ፎርም ያላሟላ ቢሆንም የቤት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ የማያከራክር ማረጋገጫ ስለሆነ ውሉ የፀና ይሆናል።
(የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ መዝገብ/ቁ 56794 ቅፅ 12)
የተከፈለው ክፍያ ግን ቀብድ መሆኑ በውሉ ላይ ካልተገለፀ በቀር ቀብድ ነው ተብሎ ሻጭ አጠፌታውን እንዲከፍል የማያስገድድ ከመሆኑ በላይ ውሉ መኖሩንም ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም።
2 የቀብድ ክፍያ መኖሩ የውሉን መኖር የሚያረጋግጥ ብቁ ማስረጃ ቢሆንም ተዋዋይ ወገኖች ውሉን ለማፍረስ ተቃራኒ ስምምነት ካላደረጉ በቀር ቀብድ ተቀባዩ የተቀበለውን ገንዘብ እጥፍ አድርጎ በመመለስ፥ ቀብድ ሰጪው ደግሞ ይህንኑ የሰጠውን ገንዘብ ለተቀባዩ በመልቀቅ ያለሌላ ተጨማሪ ሁኔታ ውሉን የማፍረስና በመካከላቸው የተመሰረተውን ግዴታ ለማስቀረት መብት አላቸው። ይህም አሰራር በቀብድ የታሰረ ውል ከሌሎች ውሎች የሚለይበት ልዩ ባህሪ ነው። (የፍትሀ ብሄር ህግ ቁ 1885)
ፍርድ ቤቶችም በተዋዋይ ወገኖች መካከል ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ሻጩ የቀብዱን አጠፌታ ከፍሎ ውሉን በማፍረስ የሸጠው ቤት እንዲመለስለት ከጠየቀ መወሰን የሚገባቸውና ተገዶ እንዲፈፅምም ማድረግ የሌለባቸው መሆኑ ግልፅ ነው።
የተደረገው ውል ሊፈፀም የማይችል (impossible)፣ ወደ ገዥ ሊተላለፍ የማይችል እና ህገ ወጥ (unlawful) ከሆነ ግን ውሉ ፈርሶ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት ከሚመላለሱ በቀር ሻጭም እጥፉን እንዲመልስና ገዢም የከፈለውን እንዲለቅ የሚጣልባቸው ግዴታ የለም።
3 ውሉ በአግባቡ ከተፈፀመ እና ለ ቀብዱ ገንዘብ ዕጣ ፋንታ በተዋዋዬቹ መሀል የተደረገ ሌላ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ የቃብድ ሂሳቡ ከጠቅላላው የሽያጭ ዋጋ ላይ የሚታሰብ ወይም እንዲመለስ የሚደረግ ይሆናል። (የፍትሀ ብሄር ህግ ቁ 1884)
Join 👇👇
https://t.me/ethiolawtips