የፍ/ቤት ፕሬዝዳንት በእስራት ተቀጣ
---------------------------------------------
ስልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም እና የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት ወንጀል በፈጸመ የፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ላይ የ6 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ ቅጣት ማስተላለፉን የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለጸ።
በወንጀሉ ተባባሪ የነበረች ሌላ ግለሰብም የእስራትና የገንዘብ መቀጮ ቅጣት ማስተላለፉን ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ገልጿል።
የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቢኒያም ባቡ እንደተናገሩት አንደኛ ተከሳሽ አቶ ሙሉጌታ መሰረት እና 2ኛ ተከሳሽ ወይዘሮ ፈጠነች በዛብህ በፈጸሙት የሙስና ወንጀል የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን ገልጸዋል።
አንደኛ ተከሳሽ አቶ ሙሉጌታ መሰረት የደቡብ ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛና ፕሬዝዳንት ሆነው እየሰሩ በነበሩበት ወቅት ከሁለተኛ ተከሳሽ በፍርድ ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪና ቼክ ፈራሚ ሆና ከምትሰራው ከወይዘሮ ፈጠነች በዛብህ ጋር ለራሳቸውና ለሌሎች ሰዎች ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ ለፍርድ ቤቱ ከተመደበው በጀት ውስጥ ከተቋሙ ስራ ጋር ለማይገናኝ አላማ የተቋሙ ሰራተኛ ላልሆኑ ነጋዴዎች በ2013 ዓ.ም 163ሺ ብር አበል ክፍያ ፈጽመዋል ብለዋል።
በዚሁ መዝገብ ግለሰቧ በ2014 ዓ.ም ለሌላ ነጋዴ 197ሺ 706 እንዲሁም በ2015 ዓ.ም 721ሺ 442 ብር ፣ በ2016 ዓ.ም 309ሺ 822 ብር ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ በድምሩ 1 ሚሊየን 361ሺ 768 ብር በአበል ክፍያ እንዲፈጸም አድርገዋል ብለዋል።
በዚህም ያለአግባብ ስልጠናቸውን በመጠቀም ወንጀሉ በሚሰጠው ሙሉ ፍሬ ተካፋይ ለተቆሙ የተመደበውን በጀት ለታለመለት አላማ እንዳይውል ማድረጋቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጧል ብለዋል።
በዚህም የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዐቃቤ ህግ በቀረበለት መዝገብ ላይ ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ በትላንትናው ዕለት የቅጣት ውሳኔና ፍርድ ሰጥቷል ብለዋል። በዚህም አንደኛ ተከሳሽ እጃቸው ከተያዘበት ከቀን 27/05/2016 ዓ.ም ጀምሮ በሚታሰብ የ6 ዓመት ጽኑ እስራትና የ7ሺ 500 ብር መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል ብለዋል።
2ኛ ተከሳሽ እጃቸው ከተያዘበት ከቀን 27/05/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚቆጠር በ5 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራትና በ5ሺ 500 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ፍርድ የተሰጠ ሲሆን አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሽ በጋራ ያጎደሉትን 1ሚሊየን 345ሺ 320 ብር በጋራ እንዲከፍሉ የተወሰነ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ በግል በኦዲት የተገኘባቸውን ተጨማሪ 16ሺ ብር 448 ብር እንድትመልስ ውሳኔ መሰጠቱን ገልጸዋል።
አቶ ቢኒያም በመጨረሻም በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች የሙስና ወንጀሎች አይነትና የመፈጸሚያ ስልቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መምጣታቸውን ገልጸው ህዝቡ ሙስናን በመፀየፍና ተፈጽሞ ሲገኝ ጥቆማ በምስጠት የዜግነት ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።