የቤት ሽያጭ ውል መደረጉን ክደው ተከራክረው እያለ የሥ/ፍ/ቤቶች ሽያጭ ውል መደረጉ በሰው ምስክር ተረጋግጧል በሚል ሻጮች ቤቱን ለገዢ እንዲያስረክቡ በማለት የተሰጠ ውሳኔ የማይንቀሳቀስ ሽያጭ ውል አደራረግ ሥርዓት በሚመለከት የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723(1) የተደነገገውን የፌ/ሰ/ሰ/ችሎት በሰ/መ/ቁ 21448 ላይ ከሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሚቃረን በመሆኑ ተሽሯል በማለት በዚህ የሰበር ውሳኔ የተሰጠው የህግ ትርጉም ቀብድ እንደከፈሉ ገልፀው ክስ ቢያቀርቡም ከሥር ፍ/ቤት ጀምሮ ክፍያው ቀብድን የሚመለከት ሳይሆን ከዋናው ሽያጭ ገንዘብ ውስጥ በቅድመ-ክፍያ ብር 1 ሚሊዮን መክፈላቸውን በመረጋገጡ ከጅምሩ በዚህ ረገድ የቀረበው የቀብድ ከፍያለው መከራከሪያ ውድቅ ሆኖ ነገር ግን በፍ/ብ/ህ/ 1723 መሰረት በውል አዋዋይ ፊት ያልተደረገ የቤት ሽያጭ ውል በሻጩ ተክዶ ክርክር በቀረበበት ሁኔታ ውል ስለመኖሩ በምስክር ሰምቶ በማረጋገጥ እንደ ሽያጭ ውሉ ሊፈፅም(ቤቱን እንዲያስረክብ) እና ቀሪ ገንዘብ ተቀብለው ቤቱን ሻጮች ሊያስረክቡ ይገባል ተብሎ የተሰጠ ውሳኔን መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት የፌ/ሰ/ሰ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 215762 እርማት ያደረገበት መዝገብ ነው።
Join👇👇
https://t.me/ethiolawtips
Join👇👇
https://t.me/ethiolawtips