#አዲስ_የሰበር_ውሳኔ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን በሰው ምስክር ለማስረዳት የሚችሉበት የህግ መሠረት ባለመኖሩ ገዥ ቤቱን ገዝቼዋለሁ በማለት የሚያቀርቡት መከራከሪያ በሻጭ ሚስት ላይ ህጋዊ ውጤትን የሚያስከትል አይሆንም ሰ/መ/ቁ 224476 በቀን 05/02/2017ዓም የተወሰነ
==========================
የማይንቀሳቀስ ንብረት ካለዉ ልዩ ባህርይ አንፃር ንብረቱን ከአንድ ወደ ሌላ ሰዉ በሽያጭ ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል በሦስተኛ ወገን ላይ ህጋዊ ዉጤት ያስከትል ዘንድ ዉሉ በህግ አግባብ በሚመለከተዉ አካል ዘንድ ካልተመዘገበ ውሉ ፈራሽ እንደሚሆንና የፍ/ሕ/ቁ አንቀጽ 2878 ን ዋቢ በማድረግ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 153664 ላይ አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠበት ሲሆን በተያዘው ጉዳይም ተጠሪው ይህ አከራካሪ ቤት ከአመልካችዋ ባለቤት ላይ በግዢ ያገኙት መሆናቸውን ከመግለጽ በቀር፤ ቤቱን በግዢ ስለማግኘታቸውና በህግ አግባብ ባለው አካል ዘንድ የግዢና የሽያጭ ውሉ የተመዘገበበት የሰነድ ማስረጃ ተጠሪው በሥር ፍርድ ቤት ያላቀረቡ በመሆኑና የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን በሰው ምስክር ለማስረዳት የሚችሉበት የህግ መሠረት ባለመኖሩ አመልካቹ ቤቱን ገዝቼዋለሁ በማለት የሚያቀርቡት መከራከሪያ በአመልካችዋ ላይ ህጋዊ ውጤትን የሚያስከትል አይሆንም
https://t.me/ethiolawtips