የ2ዐ17 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡
ጥቅምት 16/2ዐ17 ዓ.ም በተካሄደው ግምገማ የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወሪ/ት ሄራን ገርባ አንደገለጹት የዝግጅት ምዕራፍን ከወትሮ ለየት ባለ መልኩ ቀደም ብሎ በማጠናቀቅ ወደ ተግባር የተገባበት ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው የተቀመጡ ኢላማዎች መሳካታቸው የሚታይበት መድረክ በመሆኑ የህብረተሰብን ጤና ከመጠበቅ አንጻር ከምግብና የጤና ግብዓቶች ደህንነትና ጥራት ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች ጠንካራ ስራዎችና ያጋጠሙ ችግሮች መፍትሄ አቅጣጫ የሚቀመጥበት መድረክ ነው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ባሳለፍነው የሩብ ዓመት የአገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም እንዲሁም የማቹሪቲ ደረጃ ሶስት ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸው ጠቅሰው የቁጥጥር ዘርፉን ለማዘመን፤ከአፍሪካና ከአለም አቀፍ አንፃር ተፎካካሪ ሆኖ ለመውጣት የመንሰራበት ወቅት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡
የማይክሮ ፋይናንስ ሪፎርም ከተደረገ በኋላ ብዙ በጎ ለውጦች የታዩ በመሆኑ ከለውጦቹ ጋር ተያይዞ የፎሬይን ከረንሲ እድል በስፋት መገኘቱና የውጭ ኢንቨስትመንት መጨመር ጋር ተያይዞ አዲስ ጥያቄዎች እና እድሎች መኖራቸውን ገልፀው የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥሩን ተግባር ከዚህ ጋር ማዛመድና ማጠናከር እንደሚገባ በማስገንዘብ በእጅ ያለ ሀብትን በአግባቡ በመለየት በቁጠባ በመጠቀም ስራዎችን እያላቁና እያዘለቁ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ መስራት አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተለይተው በቀጣይ ሩብ ዓመት ትኩረት ተሰጥቶ የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር ስራ በቅንጅት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በላቀ ሁኔታ ህብረተሰብን ለማገልገል መስራት እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡