ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የ100 ቀን ዕቅድ አፈጻጸም እና የባለስልጣን መ/ቤቱ የሩብ ዓመት አፈጻጸም ላይ ውይይት ተደረገ፡፡
ጥቅምት 19/2017 ለምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሠራተኞች በማክሮ ኢኮኖሚ ፋይናንስ ሪፎርም ላይ ገለፃ ያደረጉት የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወሪ/ት ሄራን ገርባ እንደተናገሩት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሙ በዋናናት ሲደረግ ትኩረት የተደረገው በሁሉም ዘርፍ አቅርቦትና ፍላጎትን ማጣጠም ፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችትን በዘላቂነት ማሳደግ ፣ ምርትና ምርታማነትን መጨመር፣ የዜጎችን አካታች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን መፍጠር ፣የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብና ሁለንተናዊ አገራዊ ዕድገት ማምጣት ነው፡፡
ኃላፊዋ አክለውም በዚህም በጎ ለውጦች የታዩ ሲሆን የውጭ ምንዛሬ በስፋት መገኘት፣ የውጭ ኢንቨስትመንት መጨመር፣ የወጪ ንግድ ማደግ፣ የኮንትሮባንድ ንግድ መቀነስ እና ገቢ የመሰብሰብ መጠናችነን ማደግ መገለጫዎቹ ናቸው ብለዋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ልንሻገራቸው የሚገቡን ተግዳሮቶች መኖራቸውን የጠቀሱት ወሪ/ት ሄራን ገርባ የዋጋ ግሽበት እና የስራ ዕድል ፈጠራ አበክረን ልንሰራበት የሚገባን ዘርፍ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሙን ስንገመግም ከተቋሙ ጋር ተዛማጅነት ያላቸዉን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞች ወስደን ልንሰራባቸዉና የራሳችንን አበርክቶ ማስቀመጥ አለብን ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም የ2ዐ17 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተለይተው በቀጣይ ሩብ ዓመት ትኩረት ሰጥቶ ሰራተኛው በመቀናጀት በላቀ ሁኔታ ህብረተሰብን ለማገልገል መስራት እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡