በመላ ሐገሪቱ ወጥ የሆነ የቁጥጥር ስርዓት ለመዘርጋት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተገለፀ
ታህሳስ 14/2017 አዲስ አበባ፡- አዲስ በተዘጋጀው የማህበረሰብ መድኃኒት ቤትቸ ብሔራዊ ደረጃ ዙሪያ በተዘጋጀ የምክክር መድረክ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ እንደተናገሩት የቁጥጥር ስርዓቱን Maturity level 3 ለማድረስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንና ከፌዴራል ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ወጥ የሆነ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊነትን አስረድተዋል።
የማቹሪቲ ሌቭል 3 ጉዳይ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ለቁጥጥር ስርዓቱ እንደህልውና ተይዞ ሊሰራ እንደሚገባ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሯ የቁጥጥር ስርዓቱ ለሀገር እድገት አቅም መሆን እንዳለበትና ሁሉም ክልል ሁሉም ከተማ መስተዳደር ለስኬቱ ያላሰለሰ ጥረት እንዲያደርጉ የጠየቁ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወጥ የሆነ የቁጥጥር ስርዓት ለማስፈን አደረጃጀቶችን ከማስተካከል ጀምሮ የክልሎችን አቅም ለመገንባት ከUSPQM+ ጋር በመተባበር ክልሎች የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ የሚያዩበትን መንገድ ማመቻቸቱን አስታውቀው ብዙውን ጊዜ የህክምና ምክርና ህክምና ለማግኘት የሚፈልጉ ዜጎች የመጀመሪያ ተደራሽ የሆኑት የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቶች በመሆኑ የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቶች ብሔራዊ ደረጃ እንደአዲስ መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡
በመድረኩ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ ከክልል ጤና ቢሮዎች፣ የክልል ተቆጣጣሪዎችና የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የቅርንጫፍ ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፣ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩትና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙ ፅሁፍ አቅራቢዎች ጥናቶችና ፅሁፎችን አቅርበው ሠፊ ውይይት ተደርጓል፡፡