የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከምግብ አምራች እና አስመጪ ተቋማት ጋር በተዘጋጁ ረቂቅ መመሪያዎች ዙሪያ ምክክር አካሄደ፡፡
ታህሳስ 17 /2017 ዓ.ም በተቋሙ በተከለሱ አጠቃላይ የምግብ ምዝገባ መመሪያ( general food registration directive) እና የምግብ መልካም አመራረት ስርዓት ቁጥጥር አሰራር ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተደርጓል።
በወይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የምግብ ምዝገባና ፍቃድ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መንግስቱ አስፋው እንደተናገሩት በረቂቅ መመሪያው ላይ ውይይት ያስፈለገው የምግብ አምራች እና አስመጪ ተቋማት የመመሪያው ባለቤት ከመሆናቸውም በተጨማሪ በዘርፉ ካላቸው ክህሎት፣ ዕውቀትና ልምድ ተነስተው በምግብ ቁጥጥር መመሪያው ጥሩ ግብዓት ማበርከት እንደሚችሉ በማመን ሲሆን አካታችነትን ለማስፈን እና የተሳለጠ የቁጥጥር ስራን በጋራ ለመስራት ያስችላል ያሉ ሲሆን መመሪያዉን በየወቅቱ መከለስና ማዘመን፣ ጊዜውን ያማከለ በማድረግ እና ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍ የወደፊቱን የጋራ ስራ እንደሚያቀና ተናግረው ተሳታፊዎች ገንቢ ትችት እንድያቀርቡም ጠይቀዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ከ50 በላይ የምግብ አምራች እና አስመጪ ተቋማት ባለቤቶች ፣ ስራ አስፋፃሚዎች እና ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በተካሄደውም ውይይት የተነሱ ሃሳቦችና አስተያየቶች በግብዓትነት ተወስደው በመመሪያው ውስጥ እንደሚከታቱ ታውቋል፡፡