Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
''የሀዋሳ ኮሪደር የራሱ ልዩ አሰራር ያለው ሆኖ በአዲስ አበባ የተጀመረውን የከተማ ልማት ጥረት ያስቀጠለ ሥራ ነው። ሰፋ ያሉ የእግረኛ መንገዶች፣ የተለዩ የብስክሌት መንገዶች፣ በሀገር ውስጥ የተመረቱ ስማርት የመብራት ምሰሶዎች ወዘተ የሥራውን ፈጠራን እና ቀጣይነትን ያሳያሉ። ይሁንና የከተማ ልማት የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ አይደለም፤ የተሳካ ይሆን ዘንድ የማኅበረሰቡን ንቁ ተሳትፎ ይሻል። ርምጃዎቻችን መልካም ቢሆኑም እነዚህን አሻጋሪ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ ብዙ ሥራ ይቀረናል። ኢትዮጵያ ሰፊ እና ሀብት የሞላባት ሀገር እንደመሆኗ እምቅ አቅሟ ግዙፍ ነው። ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህን በመገንዘብ ለሥራ የሚነሱበት ጊዜው አሁን ነው።'' ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)