በአፍሪካ ህብረት ጉባዔ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሀገራቸው መመለስ ጀመሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሀገራቸው መመለስ ጀምረዋል።
በዚህ መሰረትም የአልጄሪያ ፕሬዚዳንት አብዱልመጅድ ተቡን፣ የርዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ፣ የፍልስጤም መሪ መሐሙድ አባስ፣ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞተሊ እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በአዲስ አበባ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቅቀው ተመልሰዋል።
ለመሪዎቹ የመንግስት ከፍተኛ ስራ ሃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የክብር አሸኛኘት ያደረጉላቸው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።