ከኢትዮጵያ የተባረሩት የኤርትራ ዲፕሎማቶች ኤርትራ ደረሱ
#FastMereja I በኢትዮጵያ የነበሩ የኤርትራ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች እንዲሁም አፍሪካ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የኤርትራ ተወካዮች ከአዲስ አበባ ተነስተው አስመራ መግባታቸው ተገለጸ።
የኤርትራው ዲፕሎማት አስመሮም ተከስተ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ እንደገለጹት፤ ከአዲስ አበባ የተመለሱት ዲፕሎማቶች እና የስራ ባልደረቦቻቸው በአስመራ ሲደርሱ በኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት እና በአምባሳደር እስቲፋኖስ አፈወርቂ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ዲፕሎማቶቹ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የኢትዮጵያ መንግስት በሰጣቸው የ48 ሰዓታት ጊዜ ገደብ መሰረት ነው።