ኦክሎክ ሞተርስና ግሎባል ዩካር የ30 ቢሊዮን ብር
ኢንቨስትመንት በጋራ ለመሥራት ተስማሙ
ኦክሎክ ሞተርስ ከቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ግሎባል- ዩካር ቴክኖሎጂ ጋር በጋራ ለመሥራትና በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ውስጥ 20ሺ ገደማ ተሽከርካሪዎችን ለደንበኞች ለማቅረብ ከስምምነት ላይ ደረሱ፡፡
ሁለቱ ኩባንያዎች በሸራተን አዲስ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፤ በ30 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት በጋራ ለመሥራትም የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ መሰረት፤ አክሎክ እና ግሎባል ዩካር ቴክኖሎጂ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ውስጥ 20 ሺ ገደማ ተሽከርካሪዎችን ለአገር ውስጥ ደንበኞች ያቀርባሉ፡፡
20ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ለማክበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው ኦክሎክ ሞተርስ፣ በመዲናዋ አዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢና በመቀሌ ከተማ ባስገነባቸው የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካዎቹ 16 ዓይነት ሞዴል ተሽከርካሪዎችን በመገጣጠም ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡
በድርጅቱ ለረዥም ዓመታት ላገለገሉ ሰራተኞች ሽልማቶችንም አበርክቷል፡፡ ሽልማቶቹ ከመኪና እስከ ቻይና ጉብኝትና ዳጎስ ያለ ገንዘብ ያካተቱ ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት፤ 6 ሠራተኞች ድርጅቱ ከሚገጣጥማቸው መኪኖች የተበረከተላቸው ሲሆን ፤9 ሠራተኞች ደግሞ የቻይና ጉብኝት ሙሉ ወጪ ተሸፍኖላቸዋል፡፡ በተመሳሳይ 3 ሠራተኞች የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡