«አቶ ጌታቸው ረዳን በሚተኳቸው ተሿሚ ዙሪያ ከፌደራል መንግስቱ ጋር እየተነጋገርን ነው» ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር
በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የጽህፈት ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረግዚአብሔር ፓርቲያቸው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ማንሳቱን አስታውሰው እሳቸውን በሚተካ ተሿሚ ዙሪያ ከፌደራል መንግስቱ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገር ነው ሲሉ አስታወቁ።
“ሁለታችንም ያመንበት ነው የሚሆነው፣ አንዳችን ካላመንበት አይሆንም” ብለዋል፤ ማን ይተካ በሚለው ዙሪያ መነጋገር አለብን ሲሉ ጠቁመዋል።
ህወሓት በግዜያዊ አስተዳደሩ ያለው ኮታ በመጠቀም የካቢኔ ተሿሚዎቹ ላይ ምደባ በማድረጉ ጊዜያዊ አስተዳደሩን ሊያፈርስ ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም ሀሰት ነው ማለታቸውንም ፓርቲው ባጋራው መረጃ ላይ አመላክቷል፤ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አጠቃላይ 27 ወንበሮች አሉት ሲሉ ገልጸው ህወሓትን የሚመለከተው 14ቱ ብቻ ናቸው ሲሉ ጠቁመዋል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩን የመሰረቱት ከትግራይ ሰራዊት፣ ከምሁራን እና ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ የተመደቡ 13 የካቢኔው ተሿሚዎች አሁንም በቦታቸው አሉ ሲሉ ያብራሩት ዋና ጻሃፊዋ የህወሓትም ቢሆን በጊዜያዊ አስተዳደሩ ምስረታ ወቅት የተመደቡ 6 ተሿሚዎች ቀጥለዋል ሲሉ አስታውቀዋል።
ይህም በጊዜያዊ አስተዳደሩ ያሉ እና የቀጠሉ የካቤኒ አባላትን 19 ያደርሰዋል ሲሉ ጠቁመው ከዚህ ውጭ ደግሞ 3 የሚሆኑ የካቢኔ አባላት ቀደም ብለው ቦታውን በመልቀቃቸው በነሱ ምትክ ነው ሰው የተመደበው ብለዋል ሲል አዲስ ስታንዳርድ ነው የዘገበው።