𝐅𝐄𝐑𝐈💥𝐃 𝐓𝐔𝐁𝐄


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Telegram


📍𝐇𝐃 𝐩𝐫𝐨𝐟𝐢𝐥𝐥𝐞 𝐩𝐢𝐜
🌹𝐖𝐚𝐥𝐥𝐩𝐞𝐫𝐬
🌹𝐀𝐦𝐚𝐳𝐢𝐧𝐠 𝐩𝐢𝐜𝐭𝐮𝐫𝐞𝐬
🌹𝐈𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐡𝐨𝐭𝐨𝐬
ለ አስተያየት :- @EzedinM1
✨𝐂𝐫𝐞𝐚𝐭𝐞𝐝 𝐃𝐞𝐜𝐞𝐦𝐛𝐞𝐫 𝟐𝟗.𝟐𝟎𝟐𝟒
Buy ads: https://telega.io/c/HD

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Telegram
Статистика
Фильтр публикаций


እንዴት ከዛ መከራ ውስጥ
እንደሚያድንሽ አላህ ብቻ ነው
የሚያውቀው ❤️‍🩹





.


​🖤 «የጨለማ ብርሃን» ⚪️

(እውነተኛ ህይወትን መሰረት ያደረገ አሳዛኝና አስተማሪ ታሪክ)

ከቤተሰቦቼ ፍቅርና ሰላም ተከብቤ አድጌአለሁ...አሚሬ ላይ ትልቅ ተስፋ አለኝ... ግን ዘመኑ ያስፈራኛል! ነገር ግን የካምፓስ ህይወት ደግሞ የራሱ የሆነ የጨለማ መንገድ አለው..."

አንብበው የማይጨርሱት፣ በደስታና በሀዘን የተሞላ ውብ ታሪክ!


ክፍል 8 ይቀጥል ወይ?




ምን ተማርኩ መሠላችሁ;
ካለማንም እና ካለምንም
ህይወት መቀጠል እንደሚችል
!🙌




‹‹በኛ ሃይማኖት ታዲያ መቆጣጠሪያው ብቻ ነው የማይቻለው? ለምን ዝሙቱ አላሳሰባችሁም?››
‹‹እኔ የምለው አሁን አታሳዝንህም በዚህ እድሜዋ ልጅ ተሸክማ ስታሳድግ? በዚህ እድሜዋ ለባሏ የቤት ሰራተኛ ስትሆን? እንደ ልቧ በምትሆንበት ዕድሜ ስትታሰር?›› ቤቲ ሰላሀዲንን እያየች ትጠይቃለች፡፡
‹‹አይ ቤቲ ትዳር መታሰር የሚሆንበትኮ በአንድ መርጋት ለማይሆንለት ለእንደናንተ አይነቱ ነው፡፡ በዚህ ዕድሜዋ የምታሳዝነኝ እንደናንተ ከክለብ ክለብ እየተመላለሰች አስሩ ቢሰካባት ነው፡፡ ለባል የቤት ሰራተኛ መሆን ምን ችግር አለው? እሷ ለባሏ ምግብ ነው ብትሰራ … የበሉበትን ነው ብታጥብ … የተኙበትን ነው ብታነጥፍ! እሱንም ሰራተኛ ከሌላት! እናንተ አፋችሁና ፊታችሁ ራሱ የስንቱ ሎድ ማራገፊያ አይደል እንዴ? እሷ በእጇ ነው የምታጥበው እናንተ በአፋችሁ አይደል እንዴ የምታጥቡት … በፊታችሁ! ሺ ሰው አይደል እንዴ የሚፀዳዳባችሁ! እንዴት ነው የጥብቅ ሴት ድካም የጎላባችሁ ባክሽ! ደርሶ ጥብቅና የምትቆሙት ነገር ነው የሚገርመኝ! ጥብቅና መቆም ያለበትኮ ለእናንተ ነው፡፡ በዚህ እድሜዋ በብዙ ወንድ ተቆፈረች … በየክለቡ ተንዘላዘለች … ተናቀች … ክብሯ በዘመናዊነት ስም ተደፈረ ተብሎ … ለናንተ ነው ጥብቅና መቆም ያለበት! በምን ሞራላችሁ ነው በተቀደሰ መልኩ ላገባች ሴት ጥብቅና የምትቆሙት?››
‹‹እኛ ፈልገን ወደን የምናደርገው ነገር ነው፡፡ ጠበቃ አያስፈልገንም!››
‹‹ሲሀም ተገደሽ ነው እንዴ ያገባሽው?››
‹‹አስገድጄ ነው እንደውም … ሀሀሀ››
‹‹ትዳር ሲባል ለምንድነው ጭቆና ፊታችሁ ላይ የሚመጣላችሁ? ቤት እናታችሁን አባታችሁ ይጨቁናት ነበር ነው? እና የእናንተ አባት ስርዓት የለውም … የባለጌ ልጆች ናችሁና ምን ይሁን? ማነው የእናንተን አባት የሁሉም አባቶች ወኪል ያደረገው? አዝናለሁ አባታችሁ ጥሩ ሰው ባለመሆኑ … ግን ይህ ሁሉንም ባሎች ለመኮነን መብት አይሰጣችሁም፡፡››
‹‹አሁን የኛ አባት ጋ ምን አስኬደህ? አሁን የኔ አባት ከመልዓክ ትንሽ ነው ዝቅ የሚለው … ››
‹‹ታዲያ ማን ላይ ያየሽውን ነው?››
‹‹በቃ ብዙ ወንዶች ጨቋኝ ናቸው፡፡ ይኼ የአደባባይ ሚስጥር ነውኮ!››
‹‹ሲባል ስለሰማሽ እንደ ገደል ማሚቱ ማስተጋባት እውቀት አይፈልግም፡፡ አንቺ ተምረሻል … እንደ ትቦ የሰሙትን ሁሉ ሳይመረምሩ ማስተጋባት ደግሞ ካንቺ አይጠበቅም፡፡››
‹‹ታዲያ ባይበደል ነው ይኼ ሁሉ ሴት የሚያለቅሰው?››
‹‹የሚያለቅሰው ሰው ድምፅ የተሰመማሽ እኮ የተመቸው ስለማይጮህ ነው፡፡ የገረመሽ ደግሞ ብርቅ ነገር ስለሆነ ነው፡፡ ሁሉም እየሞከረ ነው ያለው … ወንዱም ኢኮኖሚው በቴስታ እየገባለት ነው ለሚስቱና ልጆቹ ዳቦ ይዞ ለመግባት የሚታገለው! እንደናንተ አይነቱ ነው ሰዉን ባለው ነገር እንዳይረካ የሚያደርገው! እናንተ ማግባት ካልፈለጋችሁ ግዴታ አይደለም! ግን just shut your mouth!››
ሲሀም ሰላሀዲን ሲያወራ አፏን ከፍታ እንደሰማች ነው፡፡ ምህረትና ቤቲ የማያሳይዋትን ዓለም ስለሚጠቁማት ትወደዋለች፡፡ አፏን ከፍታ እየሰማች ስልኳ ጮኸ! አብደላህ ነበር!

ይቀጥላል!
.


ማለፊያ
(ፉአድ ሙና)
ክፍል ሰባት
***
ሲሀም ደፋሯ … ትዕግስት አጣች፡፡ ካላገባች ቂያማ የሚቆም አስመሰለችው፡፡ አሁን ገና በሀያዎቹ መጀመሪያ ላለች ታዳጊ ትዳር የሞት መድሀኒት ነው የተባለ ያህል እንዲህ መክለፍለፍ ምንድነው? ወይ አስረግዟት ይሆናል ነውሯን ለመሸፈን ነው እንጂ እንዲሁ ለማግባት ብቻ ብላ አይሆንም፡፡ የሚያውቋት ሁሉ የሚሰጡት መላ ምት ነው፡፡ በእርግጥ አብደላህ የሲሀምን ህግ የነካው ያገባት ምሽት ላይ ነው፡፡ ያጣደፋት እርግዝናም አልነበረም፡፡ ምናልባት ገና እንደሆነች … እሷ እንደምትለውም ህይወት እንደማያመልጣት ማሰብ አልቻለችም፡፡ ለዚህ ደግሞ የአብደላህ ስብከት ጥሩ አስተዋፅዖ አበርክቷል፡፡ ካገባች ሶስተኛ ቀን ተቆጥሯል፡፡ ከመጀመሪያው ቀን በኋላ ወዲያው ወደ ቤታቸው ገብተዋል፡፡ ዶርም ማደር የሚባለው ነገር እግር እግር ብሏታል፡፡ ከዚህ በኋላ ዶርም ላለማደር ወስናለች፡፡ የራሷ ቤተ-መንግስት ላላት ሴት ዶርም ምንድነው? ለሴት ልጅ ቤቷ ቤተ-መንግስቷም አይደል? ባሏ እሱ ወጣ ብሎ እስኪመለስ ንባቧ ላይ እንድታተኩር እያበረታታት … ከባሏ ጋር ያለመችውን አይነት ጊዜ እያሳለፈች ነው፡፡ በውሳኔዋ እጅጉን ተደስታለች፡፡ ፍርሀቷ ሁሉ እንኳን አደረግኩት በሚል ስሜት ተተክቷል፡፡ ዛሬ ባሏ በጠዋት ስራ ብሎ ሄዷል፡፡ ዛሬ አብረው እንዲያሳልፉ ብትለምነውም ከትምህርትሽ ትሳነፊያለሽ ብሎ በራሷ አመካኝቷል፡፡ አንብባ ደከም ሲላት እስከዛሬ ያልደወለችላቸው ቤተሰቦቿ ጋር ለመደወል አሰበች፡፡ ጓደኞቿ ጋር ደዋውላለች … የቀራት ቤተሰቦቿን መጋፈጥ ነው፡፡ በእርግጥ ምህረትና ቤቲ በልጅነቷ እንደተቀጨች ተሰምቷቸዋል፡፡ ገና ላይፍን ሳታጣጥም ወይም በአማርኛ ሲብራራ ሳትሸረሙጥ፣ ከወንድ ወንድ እየዘለለች ሳታድር፣ በየክለቡ እየዞረች ሳትጨብስ፣ ገላዋን ለቡዳ ሳታስጎበኝ፣ ወንድ ሳታደባድብበት ማግባቷ በእነሱ የሸርሙጦሎጂ እውቀት መሰረት በአጭሩ መቀጨት ነው፡፡ ከብዙ ፈራ ተባ በኋላ በየቀኑ ሲቀጠቅጥ ወደነበረው ወንድሟ ደወለች፡፡
‹‹ሲሁ …››
‹‹ጀም …››
‹‹ምን ሆነሽ ነው በአላህ?››
‹‹ምኑን?››
‹‹እሺ አገባሽ … ታዲያ ቤተሰብ ይቆረጣል እንዴ?››
‹‹ምታናግረኝ አልመሰለኝም! … ለመቆጣት የደወልክ መስሎኝ ነው፡፡›› አለቀሰች፡፡
‹‹ባይሆን ደስ ይለኝ ነበር … ሁላችንም ደስ ብሎን … እኔ እንዳገባሁት ተደግሶ ዘመድ አዝማድ ተሰብስቦ … ባባና ማማም ተደስተው ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር … ግን ከሆነ በኋላ ምን ይደረጋል?››
‹‹እኔም እንደሱ በክብር ባገባ ምኞቴ ነበር፡፡ ባባ እንቢ አለ፡፡ ቤተሰብ እንደሌለው ሰው ለብቻዬ አገባሁ፡፡›› ተንሰቀሰቀች፡፡
‹‹አይዞሽ በቃ … እኔማ መልስ ልጠራሽ ነበር የደወልኩት!››
‹‹ወላሂ?››
‹‹አዎ መች ይሻላል? ባልሽም የሚመቸውን ቀን መርጠን እራት እኛ ቤት እንድንበላ አስበን ነው፡፡››
‹‹አባ መልስ እንደጠራኸኝ ከሰማ ምንም አይልህም?››
‹‹ይገለኛል እንጂ ጭራሽ! ማንም ሳይሰማ እንድናደርገው ነው ያሰብኩት!››
ሲሀም ከጎኗ ሰው እንዳላት ተሰማት፡፡ በወንድሟ እንደዚህ ተደስታ አታውቅም፡፡ እውነት ለመናገር ግን መጀመሪያ ማግባቷን ሲሰማ እንደ እብድ አድርጎት ነበር፡፡ እንዲህ የለዘበው ሚስቱ አረጋግታውና ብዙ መክራው ነው፡፡ ‹‹ሰው እንደሌላት ከተሰማው ባሏም ይንቃታል፡፡›› የሚለው የሚስቱ ንግግር ቢያንስ በባሏ እንዳትናቅ ማቅረቡ ይሻላል ብሎ እንዲወስን አደረገው፡፡
‹‹እወድሀለሁ፡፡›› እንደ ህፃን ተንሰቀሰቀች፡፡
ባሏ ሲመጣ እንደ ህፃን ልጅ እየተፍለቀለቀች ወንድሟ ያላትን ነገረችው፡፡
‹‹ተይ ግን ይኼ ነገር ወጥመድ እንዳይሆን!››
‹‹የምን ወጥመድ?››
‹‹ይዘውሽ ቤት ምናምን ሊቆልፉብሽ ቢሆንስ?››
‹‹ከዚህ በኋላ በጭራሽ … ደግሞ ወንድሜን አውቀዋለሁ የሴራ ሰው አይደለም፡፡››
‹‹ለክፉም ለደጉም … ጓደኞቼን ይዤ እንሄዳለን፡፡››
‹‹እንደሱም ማድረግ ይቻላል፡፡›› ትልቅ ሸክም የወረደላት መሰላት፡፡ ሌላው ቢቀር ዘመዴ ብላ የምትሄድበት ቦታ መኖሩ አረጋጋት፡፡
ቀናት ገፍተው የመልሱ ቀን ደረሰ፡፡ አብደላህ ጓደኞቹን ሰብስቦ ወደ ወንድሟ ቤት አመሩ፡፡ በእርግጥ ልቡ በጣም ፈርቷል፡፡ ወንድሟን ከዚህ ቀደም ያገኘው ቀን ያደረገለት አቀባበል እንዲፈራውና መጥፎ መጥፎውን እንዲያስብ አድርጎታል፡፡ በር ላይ ሲደርሱ ጀማል ወጥቶ ተቀበላቸው፡፡ እህቱን ሲያያት ሆድ ባሰው! አይኖቹን ከመርጠብ ታገላቸው፡፡ ዓመታት የናፈቀውን ሰው እንዳገኘ ጎትቶ ደረቱ ላይ ለጠፋት፡፡ ሲረጋጋ ወንዶቹን በየተራ ሰላም ማለት ጀመረ፡፡ ሁኔታውን ሲመለከት አብደላህ ተረጋጋ፡፡ ጀማል ከዚህ ቀደም ያገኘው ሰው አልመስል አለው፡፡ በጣም ተጫዋችና ቀለል ያለ ሰው ሆነበት፡፡ ለመልሱ የተዘጋጀው ምግብ መለስተኛ ሰርግ ይመስላል፡፡ ጀማል ሰው መጥራት ስለማይችል እንጂ ቢደግስና ሰው እንዳላት ቢያሳይ ደስ ባለው ነበር፡፡
‹‹እና እንዴት ነው ሙሽርነት?›› ከሪማ እየተፍለቀለቀች ጠየቀቻቸው፡፡
‹‹ቆንጆ ነው፡፡›› ሲሀም ተሸኮረመመች፡፡
አብደላህ በጀማል ማንነት በጣም ተደንቋል፡፡ እንዲህ ፈታ ያለ ሰው ይሆናል ብሎ አልገመተም፡፡ በልተው ሲጨርሱ አብደላህ ከመቀመጫው ተነስቶ ቆመ፡፡
‹‹ኧረ ገና ነው ሰዓት …››
‹‹አይ ለመሄድ አይደለም … ስጦታ ነበረን፡፡›› ጓደኞቹ ያመጡትን ስጦታ ማውጣት ጀመሩ፡፡ በባህሉ መሰረት ለአባቷና እናቷ ስጦታ መስጠት ስላልቻሉ ወንድሟና ሚስቱን አለበሱ፡፡
ጀማልና ከሪማም ያልጠበቁት ስለነበር ክብር ተሰማቸው፡፡ ተደሰቱ፡፡ እንግዶቻቸውን ከሸኙ በኋላ አልጋቸው ላይ አረፍ ብለው ማውጋት ጀመሩ፡፡  
‹‹አንተ ጥሩ ልጅ ይመስላል ባሏ!››
‹‹አዎ ብዙም አይከብድም!››
‹‹አንተ ደግሞ በቃ ምንም አያስደስትህማ!››
‹‹አይ ደስ ብሎኛል … እንዲህ አጋኖ መግለፅ ስለማይገራልኝ ነውኮ!››
‹‹መርዙን የእሱ ሳህን ላይ በደንብ አድርጌያለሁ፡፡››
‹‹ምን?››
‹‹መርዙን ነዋ በደንብ አድርጊበት አላልከኝም?››
‹‹መች ነው ያልኩት?››
‹‹ቢሞት አሪፍ አይደል እንዴ!››
‹‹ለምንድነው የሚሞተው? የእህቴ ባል እኮ ነው!››
‹‹ያው በግድ ነዋ የወሰዳት! መች ፈቅደህ ሰጠኸው?››
‹‹እየቀለድሽ ነው አይደል?››
‹‹የምን ቀልድ ነው? እኔ ደስ የሚልህ መስሎኝ ነው ያደረግኩት!››
‹‹ግድያ?››
‹‹ሀሀሀሀሀ … አየሀ ትወደዋለህ አላልኩህም?››
‹‹ማንን?››
‹‹ባሏን ነዋ! የእህትህ ባል ነው ከዚህ በኋላ!››
‹‹እና እየቀለድሽ ነዋ!››
‹‹ምኔ ነው ነብሰ ገዳይ የሚመስልህ … ኧረ ቀልዴን ነው፡፡››
‹‹እኮ! እንኳንም ጠራናቸው ባይሆን አሪፍ ሀሳብ ነው ያመጣሽው! እህቴ እንዲህ ስትፍለቀለቅ ካየሁ ቆየሁ!››          
ደስ ብሏቸው ወደ እንቅልፋቸው ሰጠሙ፡፡
***
‹‹ሲጀመር በጣም ቆንጆ ስራ ነው ይኼ!››
‹‹አንተ እኛን መቃረን ስለምትወድ ነው እንጂ ማርገዝ የሚባል ነገር አለ እኮ!››
‹‹ለማርገዙ የወሊድ መቆጣጠሪያውስ?››
‹‹እሱ መች ይቻላል በናንተ ሃይማኖት?››
ሲሀም ምልልሳቸውን ታደምጣለች፡፡ አስተማሪ ወጥቶ ከክላስ ከመውጣታቸው በፊት ቁጭ ብለው እያወጉ ነው፡፡


.

​በጀነት ውብ መደብ ላይ፣ አየሩ ሁሉ በምስክ ሽታ በተሞላበት ታላቅ ስፍራ ከነቢዩ ﷺ ጋር ተቀማምጠሃል...
​ውዱ ነቢያችን ﷺ በአይኖቻቸው በፍቅር እያዩህ፣ በዱንያ ሳለህ በሳቸው ላይ ታወርድ የነበረውን እያንዳንዱን #ሰለዋት እያስታወሱህ...

«በዱንያ ሳለህ ያወረድከው ሰለዋት ሁሉ ይደርሰኝ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ውጤቱን በአይኖችህ እይ!» ብለው ፈገግ ብለው ሲያበስሩህ imagen 🥹🤍

ሶሉ አለነብይ..
​إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمً ۞



.


አሁንማ አድገናል ከማማረር
ከማኩረፍ  ከግጭት አልፈናል፤
አሁን ለይ ሁሉንም ነገር በዝምታ እና
በፈገግታ ነው የምናልፈው ❤️‍🩹





.


U know ይሄን story ደጋግሜ እያነበብኩት ነው ግን እንደአዲስ ባነበብኩት ቁጥር እነደአዲስ surprise እየሆንኩ ነው
    i really appreciate ለጓደኛው የሄደበትን ርቀት...የፍቅር አገላለፁ...
በቃልም አይደለም በተግባር መግለፁ... ከዱንያውም አልፎ ስለአኺራው ማሠቡ...∞🤌
   እና ነገርየውን ወደኛ አመጣሁት እና አሠብኩት... ስንቶቻችን ነን ለጓደኛችን
this type of ርቀት የምንጓዘው??የጓደኛችንን ጉዳይ ከጉዳያችን ምንቆጥረው?? ቆይ አሡን ተውትና ስንቶቻችን ነን የጓደኛን ትርጉም በውል የተረዳነው  ???
  firstly, ከስሙ ስንነሳ  ጓደኛ - ጓዳ -ኛ (ጓዳችንን የሚያውቅ) ማለት ነው
  ማወቅ ብቻ አይደለም(ቅንነት ከጎደለው ማወቅ አለማወቅ ይሻላል)..መቼም ጓዳችን ውስጥ እንከን አይጠፋም እናም ከነእንከናችን የሚወደን ገመናችንን ገመናው የሚያረግ ...∞
   ለናንተስ ጓደኛ ማለት ምን ማለት ነው¿


✍️shruq


#from fyp
ስለ ሴት ልጅ ጥቃት ስለቀን መጨለም
profile እንጂ የቀየርነው የለም


#ከሠማሁት

....አቡበክር ሲዲቅ  በጭራሽ ቀድመው ለኡመር ሰላምታ አያቀርቡም ነበር
ነገር ግን ኡመር ሰላምታውን ሲያቀርቡ ይመልሳል

ይሄንንም ነገር ኡመር ለ ሰይዲ ይናገራሉ

ሰይዲም አቡበከርን ጠየቁት
እሱም እንዲ ሲል መለሰ:-
'በወንድሙ ላይ ቀድሞ ሰላምታ የሰጠ ሰው በጀነት ቤት አለው' ስትሉ ሰምቻለው እና ያ ቤትም ለ ኡመር እንዲሆን ወደድኩኝ
ያ allah
እንዴት ያለ አስተሣሠብ፣ፍቅር፣ጓደኝነት... ነው 🥹🥹

shruq🌷


‹‹በል እንዳገባ ተጠንቀቅ …››
‹‹ያልተነካ ነው አይወድቅም ….››
ጓደኛዋ አዘገጃጅታት ቦርሳዋን ይዛ ወረደች፡፡ አብደላህ አንዱ ጓደኛውን የሲሀምን ጓደኛ ቤቷ እንዲያደርሳት አደራ ብሎ ከብዙ ትግል በኋላ ወደተሳካለት … ከወላጆቿ ነጥቆ ከእጁ ወዳስገባት ሚስቱ በሊፍት ተስፈነጠረ፡፡ ልቡ የሮጠ ይመስል በፍጥነት እየመታ ነው፡፡
ልክ ወደ ክፍሉ ሲገባ ሚስቱ ተዘገጃጅታ እየጠበቀችው ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ የሆነውን በውብ ቃላት መግለፅ ባይጠናም … ለላጤ ስነ-ልቦና ሲባል … ውሀ ለሌለባቸው ሰፈሮች በማዘን … ተፈታኝን ከፈተና ለመጠበቅ ስንል ዘለነዋል፡፡
መቼስ ሲነጋ ፀሀይ መውጣቷ የዱንያ ሱና ነው፡፡ ፀሀይ በክፍላቸው መስታወት በኩል ለዚያራ ነው መሰል ዘለቀች፡፡ የሲሀም ልብ ውስጥ ፍራቻ ጨምሯል፡፡ ከልጅነቷ ጀምሮ ያሳደጓትን ቤተሰቦቿን ትታ ከአመት በፊት ለማታውቀው ሰው ህጓን አስረክባለች … ህይወቷን ልትሰጥ መንገድ ጀምራለች፡፡
ቁርስ ከበሉ በኋላ ስልኳን አንስታ ተመለከተችው፡፡ ድምፁን አጥፍታው ስለነበር በርካታ ያልተመለሱ ጥሪዎች ተጠራቅመው ቆይዋት፡፡ ወንድሟ ከሀያ ጊዜ በላይ ደውሏል፡፡ ከሪማ ስምንት ጊዜ ደውላለች፡፡ እናቷ አስር ጊዜ ደውለዋል፡፡ ቤቲ … ምህረት … ሌሎችም የግቢ ልጆች … ብዙ ጥሪ ነበራት፡፡ ማን ጋ ቀድማ እንደምትደውል ግራ ተጋባች፡፡ የእናቷና የወንድሟ ቁጣ እንደሆነ ስለጠረጠረች ወደ ከሪማ ደወለች፡፡ አንዴ እንደጠራ ተነሳ፡፡
‹‹አንቺ … ምን ሆነሽ ነው በአላህ?››
‹‹ምነው?››
‹‹ስልክ ስደውል የማታነሺው ነዋ! ወንድምሽ ራሱ ሲያብድ ነው ያደረው!››
‹‹ምነው አለ?››
‹‹ፋዘር ነግረውት ነዋ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እንደከሰስሻቸው!››
‹‹ኧረ እኔ አልከሰስኩትም፡፡ ላገባ ሄጄ ዳኛው ነው ያስጠራው፡፡››
‹‹ምን? ላገባ? እንዴ … ሳትነግሪኝ?››
‹‹ያው ብነግርሽ ለጀማል መናገርሽ አይቀርም ብዬ ነዋ!››
‹‹እና እንዴት ሆንሽ ታዲያ?››
‹‹እናማ … በሸሪዓ ፍርድ ቤት ኒካህ አሰርኩ … ከባልየው ጋር ሀኒሙን ላይ ነኝ!››
‹‹አታደርጊውም!››
‹‹አደረግኩት! እንግዲህ ለምኜ ተከለከልኩ … እስከ መች በልምምጥ ይዘለቃል?››
‹‹እና አደርሽ አደርሽ?››
‹‹አዎ … አንቺ ግን እንደዚህ እንደሚያም ለምን አልነገርሽኝም?››
‹‹ያ ረቢ … የምርሽን ነው ከወንድ ጋር ተኛሽ?››
‹‹ከወንድ ጋር ሳይሆን ከሀላል ባሌ ጋር ተኛሁ!››
‹‹እብድ ነሽ ወላሂ … እብድ! አሁን ቤተሰቡ ምንድነው የሚልሽ?››
‹‹አባ መቃብሬ ላይ እንዳትቆሚ ብሎኛል፡፡ የሌሎቻችሁን እየጠበቅኩ ነው፡፡›› ድምፅዋ በሳግ ታፈነ፡፡
‹‹እኔማ እህትሽ ነኝ ምን እልሻለሁ? ብታማክሪኝ ነበር ጥሩ …››
‹‹ባክሽ ባማክርሽ ከማቃጠር የዘለለ ምንም አትፈጥሪም፡፡ ደግሞ እኔም እንደዚህ ነገሮች ይፈጥናሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር፡፡››
‹‹እና አሁን የት ነሽ?››
‹‹ሆቴል ነው ያረፍነው … ቦታው ይቅርብሽ … ከሆቴል ስንወጣ እደውልልሻለሁ፡፡ ባልሽ አለ አብሮሽ?››
‹‹ኧረ በጠዋት ነው የወጣው …››
ከከሪማ ጋር ተሰነባብታ ስልኩ ተዘጋ፡፡ ወንድሟ ጋር ለመደወል አሰበች፡፡ ልቧ ደግሞ ፈራ፡፡ ወደ ባለቤቷ እቅፍ ተመለሰች፡፡ እያለች … ትንሽዋ ልጅ አሸነፈች!

ይቀጥላል!
.


ማለፊያ
(ፉአድ ሙና)
ክፍል ስድስት
***
ሲሀም ስላረፈደች የምሳ ቀጠሮው ተትቶ በቀጥታ ፍርድ ቤት ለመገናኘት ተስማምተዋል፡፡ የሸሪዓ ፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ ስትደርስ አብዱላህን ከብዙ ሰዎች ጋር ተቀምጦ አገኘችው፡፡ መምጣቷን ሲመለከት ከሰዎቹ ተነጥሎ ወደሷ ቀረበ፡፡
‹‹ሲሁዬ …››
‹‹አብዱዬ …››
‹‹አረፈድሽ እኮ!››
‹‹ምንድናቸው ሰዎቹ?››
‹‹እዚህ ለምስክርነትም ምናምን ያስፈልጋል ያሉኝን ሰው ነው ይዤ የመጣሁት! አንቺ ለቃዲው በደንብ አስረጂ በተደጋጋሚ ለማግባት ፈልገሽ እንደተከለከልሽ … ትኩረት አድርገሽ ማስረዳት አለብሽ!››
‹‹እሺ …››
ተራቸው እየደረሰ መሆኑን ልብ ስትል ልቧ በፍርሀት ተናጠ፡፡ ሩጪ አምልጪ የሚል ስሜት ነፍሷን አስጨነቀው፡፡ የአባቷ ፊት ዓይኗ ላይ ተመላለሰባት፡፡ የእናቷ ቁጣ ትዝ አላት፡፡ ራሷን ለማጀገን ሞከረች፡፡ የአብዱላህን ክንድ ጭምቅ አደረገችው፡፡ አለሁልሽ እንዲላት ፈልጋለች፡፡ መውደቂያዋ ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ ሽታለች፡፡ ጣቶቿ ይንቀጠቀጣሉ፡፡ ስማቸው ተጠራ፡፡ ወደ ቃዲው ቢሮ ዘለቁ፡፡
‹‹ምንድነው ፍቺ ነው?›› ቃዲው ጠየቁ፡፡ ግቢው ውስጥ ከሚጋባው ይልቅ የሚፋታው ስለሚበዛ አይፈረድባቸውም፡፡
‹‹አይ ጋብቻ ነው፡፡›› አብደላህ ቀደም ብሎ መለሰ፡፡
‹‹አባቷ የታሉ?››
‹‹እሳቸው እምቢ ስላሉ ነው ወደዚህ የመጣነው!››
‹‹ለምንድነው እንቢ ያሉት?››
‹‹ትምህርቴን ትዳር እንደሚያቋርጠኝ ያስባል … እኔ ደግሞ ሀራም ላይ እንዳልወድቅ ስጋት ላይ ነኝ፡፡ ከዚህ በፊትም ሁለት ትዳር አበላሽቶብኛል … ይኼ ሶስተኛ ነው፡፡››
‹‹እስኪ የአባትሽን ስልክ ስጪኝ!›› ነገረቻቸው፡፡ ሊደውሉ መሆኑ ምቾት ነስቷታል፡፡ ስልኩ ተነሳ፡፡
‹‹የሲሀም አባት ነዎት?››
‹‹አዎ!››
‹‹ከሸሪዓ ፍርድ ቤት ነው የምደውልልዎ …›› ራሳቸውን አስተዋወቁ!
‹‹ምንድነው?››
‹‹ልጅዎን አልድርም ብለዋል?››
‹‹አዎን ብያለሁ!››
‹‹መልካም አሁን ሸሪዓ ፍርድ ቤት መምጣት ይችላሉ ወይስ ለነገ ቀጠሮ ልስጥ?››
‹‹ኧረ አሁን እመጣለሁ!››
አባቷ እስኪመጡ ድረስ ውጪ እንዲቆዩ ተነገራቸው፡፡ ሲሀም ልቧን ልትተፋው ደረሰች፡፡ አባቷ መጥተው አንገቷን የሚያንቋት የሚያንቋት መሰላት! አብዱላህን ተደግፋ አለቀሰች፡፡ አብዱላህም ልቡ ፈርቷል፡፡ ግን ከዚህ በኋላ ወደ ኋላ መመለስ ከብዶታል፡፡ አብረውት የመጡ ብዙ ጓደኞቹ መኖራቸው ጥንካሬ ሆኖታል፡፡ ከሰላሳ ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አባቷ ወደ ፍርድ ቤቱ ደረሱ፡፡ ሲሀም የአባቷን መኪና ስትመለከት የምትገባበት ጠፋት፡፡ አባቷ ወደ ቃዲው ቢሮ ሲገቡ ከጎረምሳ ጋር ተቀምጣ ተመለከቷት፡፡ ምንም ሳይናገሩ አንገታቸውን በአሉታ ነቅንቀው ወደ ውስጥ ገቡ፡፡ ከልጅነቷ ጀምረው አቀማጥለው ያሳደጓት አባቷ ላይ ዛሬ ለመጣ ጎረምሳ ብላ ክስ መመስረቷ ልባቸውን ሰብሮታል፡፡ እሷ እሳቸው ላይ በቀጥታ ክስ ባትመሰርትም የሳቸው አረዳድ የተከሰሱ ያህል ነው፡፡ በእርግጥ በቀጥታ አይሁን እንጂ በተዘዋዋሪ ተከሰዋል፡፡ ውስጥ የነበሩት ተፋቾች ሲወጡ አባትየው የፀሀፊዋን ቢሮ አልፈው ገቡ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ፀሀፊዋ አብደላህና ሲሀምን ወደ ውስጥ እንዲገቡ ጠራቻቸው፡፡ አባትየው እጃቸው ይንቀጠቀጣል፡፡ ንዴታቸውን ለመቆጣጠር እየሞከሩ መሆኑ ያስታውቃል፡፡
‹‹እርስዎ ነዎት አባቷ?››
‹‹አዎን … ነበርኩ፡፡››
‹‹ለምንድነው እንድታገባ ያልፈለጉት?››
‹‹አባት ነኝ፡፡ ለልጄ የማስብላት ህይወት አለኝ፡፡ ትምህርቷን ተምራ ስትመረቅ ከፈለገች በምርቃቷ ቀን ድል አድርጌ እድራታለሁ፡፡››
‹‹ጋብቻ ከሀራም መጠበቂያም ጭምር ነው፡፡ ልጅዎ ሀራም ላይ ከምትወድቅብዎ አግብታ መማር የምትችልበትን ሁኔታ ማመቻቸት አይሻልም?››
‹‹አግብቶ መማር የሚባለው ነገር ቀላል አይደለም፡፡ የሷ ትምህርት ደግሞ ትኩረት ይፈልጋል፡፡ ካገባች ትኩረቷ ይበተናል፡፡ ውጤታማ አትሆንም!››
‹‹እንግዲህ እሷ ለማግባት ቀርባለች እዚህ … እርስዎ ያቀረቡት ምክንያት ደግሞ ተቀባይነት የለውም፡፡ ሌላ ወይ ሙሽራው ላይ የሚያቀርቡት ምክንያት ካለ ያቅርቡ፡፡››
‹‹የት አውቀውና ብለው ነው!››
‹‹መልካም እንደዚህ ከሆነ የእርስዎ ተቃውሞ ተቀባይነት የለውም፡፡ ግን ለህይወታችሁም ለእሷም ለእርሶም ክብር እንዲመጥን ሀሳብዎን ቢቀይሩና እርስዎ በአግባቡ ደግሰው ልጅዎትን ቢድሩ መልካም ነው፡፡››
‹‹ተገድጄ ከሰጠሁ ምኑን ሰጠሁት ብለው ነው … ተቀማሁ እንጂ! እኔ በፍፁም አልድርምም ጋብቻውንም እውቅና አልሰጥም፡፡ ካገባችም ከእንግዲህ ልጄ አይደለችም፡፡ መቃብሬ ላይ እንዳትቆም፡፡››
‹‹መልካም መሄድ ይችላሉ፡፡››
ከመቀመጫቸው ተነስተው ልጃቸውን አተኩረው ከተመለከቱ በኋላ ክፍሉን ለቀው ወጡ፡፡ ሲሀም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አንገቷን እንዳቀረቀረች ነበር፡፡ ልቧ በፍርሀት ተንጧል፡፡ እንዳለው ጨክኖ ከቆረጠኝ ምን ይበጀኛል የሚለው አሳስቧታል፡፡ ግን ደግሞ ከወለደች በኋላ ቁጣው በርዶ ይቅር ማለቱ እንደማይቀር ስታስበው ትረጋጋለች፡፡ ብዙ ሰው ከወለደ በኋላ መልሶ ከቤተሰቦቹ ጋር ይስማማል መባልን ሰምታለች፡፡
‹‹እሺ የማስተዳደር አቅም አለህ?››
‹‹በደንብ!››
‹‹ምስክሮች ይዘሀል?››
‹‹አዎ!›› ጓደኞቹን ጠራ፡፡ ማስተዳደር የሚችል መሆኑን መሰከሩ፡፡
‹‹መህርሽ ስንት ነው?›› ያላሰበችበት ጥያቄ ነበር፡፡
‹‹አምስት ሺህ ብር!›› አፏ ላይ የመጣላትን ጠራች፡፡
‹‹አሁን ትከፍላለህ?››
‹‹ኧረ አዎ! ከኪሱ ውስጥ የታሸገ ብር አውጥቶ ፈታና ቀንሶ ሰጣት፡፡›› የጠበቀው መህር ብዙ መሆኑን ከያዛቸው የታሸጉ ብሮች ብዛት መረዳት ይቻላል፡፡ ቃዲው አጠር ያለ ንግግር ካደረጉ በኋላ ወረቀቱን አዙረው አፈራረሟቸው፡፡ እነሆ ሀላሉ ሆነች፡፡ ግን ልቧ ደስተኛ አልሆነም፡፡ አባቷ ሲወጡ ያሳይዋት የመከፋት ፊት ረብሽዋታል፡፡ አሁን ወደ ቤት ሄዳ ልብሷን እንኳን ለመውሰድ የሚያስችል ድፍረት የላትም፡፡
‹‹አብሽሪ አለሁልሽ ውዴ … ሲውል ሲያድር እሳቸውም ልባቸው ይለዝባል፡፡›› እቅፍ አደረጋት … ልጥፍ አለችበት፡፡ ስልኳን አውጥታ ወደ አንድ የሰፈር ጓደኛዋ ደወለች፡፡ በአስቸኳይ እንድትመጣ ነግራት ስልኩን ዘጋችው፡፡
‹‹ሙሽሪት … ዛሬ ራት ወጪ በኔ ነው፡፡ ቸስ ቸስ በሉ፡፡›› አንድ አፉን ወደ ስልጥኛ ያዝ የሚያደርገው ጓደኛው ግብዣ አቀረበ፡፡ ጓደኛዋ እንደመጣች የእራት ሰዓት እስኪደርስ የምትፈልገውን ልብስ ለመግዛት በየሞሉ ዞሩ፡፡ ሁለት ሻንጣ ሙሉ ልብስ ተሸመተ፡፡ አመሻሹ ላይ ጓደኞቹ ወዳዘጋጁት ሆቴል ሄደው ኮተታቸውን አስቀምጠው ወጡ፡፡ ጉዞ ወደ እራት!
‹‹ራት የት ነን? ሙሽሪት ምን ትወዳለች?›› ጓደኛው ጠየቀ፡፡
‹‹ስጋ ያለበት እንሂድ እንጂ ዛሬማ …›› ሌላኛው ጓደኛው እየሳቀ መለሰ፡፡
ቦሌ መንገድ ላይ ወዳለ አንድ መንዲ ቤት ሄደው እራታቸውን በሉ፡፡ ሲጨራርሱ ከጓደኛዋ ጋር ቀድመው ወደ ሆቴል ገቡ፡፡ ጓደኞቹና ሙሽራው ሪሰፕሽን ቆዩ፡፡
‹‹ዛሬ ማታ ልታርሰው ነዋ … ሀሀሀሀ››  ጓደኞቹ ለሱ ተደስተዋል፡፡
‹‹እንዲህ ቶሎ ሲገኝማ በስካቫተር ነዋ ጭራሽ …››
‹‹አይ አብዱዬ ጨዋታ … አላህ አላህ …››


ኢኽዋን ስለ 'ያለ ዕድሜ ጋብቻ' ምን ታስባላችተሁ??(ልጅቷ ፈቃደኛ ከሆነች)
መልሣችሁን በኮመንት 🤎


𝐀𝐬𝐞𝐥𝐚𝐦𝐮 𝐚𝐥𝐞𝐲𝐤𝐮𝐦 𝐰𝐞𝐫𝐚𝐡𝐦𝐞𝐭𝐮𝐥𝐚𝐡 𝐟𝐚𝐦🥰


የሚያውቀው እሱ ነው፡፡ ስድስት መፅሀፍ አንብባችሁ ፈጣሪ ላይ ለመንበላጠጥ ያምራችኋል፡፡ ቡሽ*ዎች!››
‹‹ስድቡን ምን አመጣው … ሴት ልጅ ያነሰች ናት ማለት ነዋ ባንተ ፍልስፍና?›› ምህረት ላለመሸነፍ ታገለች፡፡
‹‹ምክንያታዊነቱ ሲያቅትሽ ሌላ ሌላው ላይ ታተኩሪያለሽ! ሲጀመር ወንድና ሴትን ማን አወዳድሩ አላችሁ? የተለያየ ነገር በአንድ ሚዛን ሲለካ አይታችኋል? ከሰውነት በቀር ምን አገናኝቶን ነው? ከፈሳሽና ጠጣር ነገር የበለጠ ልዩነትኮ ነው ያለን፡፡ ለማነስ ምነው ቸኮላችሁ! ፈጣሪ በራሱ የሰጣችሁ ሚና ሰፊ ነው፡፡ ልጅ መውለድ እንኳን ወንድ ብቻውን የሚችለው ነገር አይደለም፡፡ ልጅ በእናንተ ማህፀን ውስጥ ነው የሚያድገው! ይኼኔ የወንድ ስራ ቢሆን ትመቀኙ ነበር፡፡ በሃይማኖቱ የተቀመጡላችሁ መብቶች ራሱ ከጭቆና ነፃ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ እናንተ ግን ለቡ*ቲነታችሁ የሚመች የሚመቸውን ነው የምታነፈንፉት! ከወንድ እንኳን የምትመርጡት የባለጌ ወንድ ስራን ነው፡፡ ከወንድ ጋር እኩል ልሁን ብላችሁ ቤተሰባችሁን በገንዘብ ስለመደገፍ ለምን አታስቡም? ለምን ኤልፓ ሄዳችሁ ከባድ የኤሌክትሪክ መስመር አትቀይሩም? መከራ መከራዋማ አትመቻችሁም! ዱርዬነቱ ነው የሚጥማችሁ! ከወንድ መስከሩ … ማጨሱ … ከሴት ሴት መመላለሱን ነው እንደ ትልቅ ትምህርት የምታዩት! ሲጀመር ሉጢነት ሲጀምራችሁ ነው እንዲህ ያለ ሃሳብ የሚመጣላችሁ! የወንድ ጥላቻ ልባችሁ ይገባና አፋችሁን ታሰፋላችሁ! ስለ አባታችሁ እየነገራችን እንደሆነ አልገባችሁም፡፡ የእናንተ አባት ባለጌ ነውና የኛን ደጋግ አባቶች ለምን እንጥላ? ከዚያ በወንድ ጥላቻ አስታካችሁ ወደ ዋናው ግባችሁ ወደ ሉጢነታችሁ ትሄዳላችሁ፡፡ ቡሽ*ዎች!››
‹‹በቃ ስድብ ነው የምትችለው ድሮም!›› በምክንያት መሞገቱ ሲጠናት ማምለጫዋ ወደሱ ማንነት መሮጥ ነው፡፡
‹‹ተይው ባክሽ አጉል ለሃይማኖት ጥብቅና ሲቆም የሚተገብረው አይመስልም? ሲጋራና ጫቱን ሲያደቅ ነውኮ የሚውለው!››
‹‹እናንተ ምህረትና ቤቲ … ሲጀመር እንዴት ሜዲሲን እንደገባችሁ ነው የሚገርመኝ … ቦዲ ካውንታችሁ ራሱ ከኔ ስልክ ቻርጀር ፓወር ቦክስ ይበልጣል፡፡ እዚህ ግቢ ውስጥ ካሉ ተማሪዎች ውስጥ ካልፈለጉት ውጪ ያልገባባችሁ ወንድ የለም፡፡ አሁን ወንዱን ጨርሳችሁ ወደ ሴት ዞራችሁ መሰለኝ! ሲሀም በጊዜ ተመለሺ! ውዳቂ ሆኖ ከመቅረት ውጪ ምንም አታተርፊም! ደሞ ባለፈው ልጅቷን ጥምብዝ አድርጋችሁ አስክራችሁ በኢመርጀንሲ በኩል እንደ ገባችሁ ሰምቻለሁ፡፡ አሳፋሪ ናችሁ፡፡ አጥፍቶ ጠፊ ሁላ! ሲሁ ሙስሊም ነሽ ተከበሪ! እኔ የፈለገ ብበላሽ የማንም መጠቀሚያ አልሆንም … አንቺ ግን ሴት ነሽ አንዴ መስመር ከለቀቅሽ ገደል ትገቢያለሽ! እወቂ! ከዚህ የሸ*ሙጣ ስብስብ ቶሎ ተላቀቂ! እንግሊዘኛ ሲቀላቅሉ እንዳንቺ አንገታቸውን ሰብረው አጥንተው እዚህ የደረሱ አይምሰልሽ … በየመሀሉ መፅሀፍ ብቻ ሳይሆን ለመምህራን እግራቸውን እየከፈቱ ነው፡፡››
‹‹ከዚህ በኋላ አንድ አፍህን ክፈትና እከስሀለሁ እወቅ!›› ቤቲ ቦግ አለች፡፡
‹‹እስኪ አንቺ ልብ አለሽ ክሰሺኝና ቆመሽ ትሄጃለሽ! ከብት!››
ቁጣዋ ቀዘቀዘ አርፋ ተቀመጠች፡፡ ሲሀም በልቧ ከሃይማኖት መሸሽ የሚባለው አማራጭ ራስን ማጥፋት ሆኖ ተሰማት፡፡ የክለቡ ሁኔታ አይኗ ላይ ድቅን አለባት፡፡ ምናልባት እንደዚህ ልክ ልኳን የሚነግራት ሰው አለመኖሩ በቀላሉ እንድትጠለፍ ሳያደርጋት አልቀረም፡፡ 
‹‹ምነው ታፈቅራታለህ እንዴ? ለምን በቀጥታ አትነግራትም? ወይስ ክርስቲያን ስለሆንን አንዘረዘረህ!››
‹‹ሀሀሀሀሀ ወደ ሃይማኖት ካምፕ ሄዳችሁ ደግሞ! ባፈቅራትም ባላፈቅራትም … ሙስሊም እህቴ ነች፡፡ ይመለከተኛል! ስንት ስርዓት ያለው ክርስቲያን በሞላበት ግቢ ማን ከእናንተ ጋር እንዳጣበቃት ነው ያልገባኝ! ትርኳሽ ሁላ!››
ሲሀም ቃል አልተነፈሰችም፡፡ ዝም ብላ ምልልሳቸውን አደመጠች፡፡ ከመቀመጫዋ ተነሳች፡፡
‹‹ስሚ አሁን የቀጣዩን ኮርስ ፓዎር ፖይንት አንብበሻል? ወይስ ከነዚህ ጋር ስትንዘላዘይ መለቀቁን አልሰማሽም?››
‹‹ተለቀቀ እንዴ?›› ሶስቱም በአንድነት ጠየቁ፡፡
‹‹አያችኋ ወንድ ላይ ስትንጠለጠሉ ትምህርታችሁን ረስታችኋል፡፡ ስለሌላው ከምታወሩ ከወንድ እኩል ዶክተር ለመሆን ያገኛችሁትን ዕድል በአግባቡ ብትጠቀሙ ይሻላል፡፡ ገረባዎች!››
‹‹ባክህ ይኼኔ ብትቅም እንደዚህ አይከነክንህም!››
‹‹ሂዱ አሁን ከዚህ ጥፉ!››
ሶስቱም እየሮጡ ወደ ዶርማቸው ሄዱ፡፡ ሰላሃዲን መርፉዓል ቀለም መሆኑ ስለሚታሰብ ማንም ቢጣላው ቂም የማይዝበት አይነት ሰው ነው፡፡ ዶርም እንደገቡ የሲሀም ስልክ ተንጫረረ፡፡
‹‹ወዬ አብዱ››
‹‹የሸሪዓ ፍርድ ቤቱን … ዛሬ ከሰዓት ኑ ብለዋል!››
‹‹እሺ … እና?››
‹‹እናማ … ነይ በቃ አሁን ምሳ በልተን እንሄዳለን!››
የሲሀም ልብ ውስጥ የነበረው እልህ አሁንም እንደተቀጣጠለ ነው፡፡ ቤተሰቦቿ ጥሳቸው መራመድ ስትጀምር ሀሳቧን እንደሚያከብሩላት አምናለች፡፡
‹‹እሺ መጣሁ … የት ይሻላል?›› ቦታ ተነጋግረው ስልኩ ተዘጋ፡፡

ይቀጥላል!
.


ማለፊያ
(ፉአድ ሙና)
ክፍል አምስት
***
ጀማልና ከሪማ ቤታቸው ውስጥ ተቀምጠው እራታቸውን እየበሉ ነው፡፡
‹‹አሁን አጉል መጎርመስ ነው እንጂ … ምን የሚያጣድፍ ነገር አለ?›› መጅሊሱን ተደግፎ ልጁን ታፋው ላይ አስቀምጦ ያበላል፡፡
‹‹እኔ አልፈርድባትም … እኛን ማየቷ የበለጠ ጉጉት የፈጠረባት ይመስለኛል፡፡ ሴት ናት መልካም ቅናትም ሊፈጠርባት ይችላል፡፡››
‹‹በጣም ጋጠወጥ እየሆነች ነው፡፡ አጉል አነበብን ብለው የሚበሻቀጡት ነገር አለ …ካምፓስ ደግሞ!››
‹‹አንተ ምን አሰብክ ግን?››
‹‹እኔ አባን አናግሬው ነበር … አቋሙ ላይ እንደፀና ነው፡፡ ህፃን ስለሆነች ነው ስትበስል ስለከለከልናት ታመሰግነናለች ምናምን አለኝ፡፡ ከሷ ይልቅ እሱ ምክንያታዊ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡››
‹‹ምን ልትላት ነው ታዲያ … ››
‹‹አርፈሽ ተማሪ ነዋ … እሹሩሩም ልክ አለው!››
‹‹ግን አሁን ያለችበት ሁኔታ ትንሽ ማለዘብ የሚፈልግ ይመስለኛል፡፡ በዚሁ ከቀጠለች እንዳታመልጠን እሰጋለሁ፡፡››
‹‹ለቁጣዋ እየተንበረከክን እሺታ ካበዛን … ቁጣዋ የፈለገችውን እንደሚያስደርግላት ታስባለች … የራስሽ ጉዳይ ማለት የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡››
እራታቸውን በልተው ሲጨርሱ ስልኩን አንስቶ ወደ ሲሀም ደወለ፡፡ የአባቱን ምላሽ መደገፉን ስታውቅ ጆሮው ላይ ስልኩን ጠረቀመችው፡፡
***
ሲሀም ጎራዳዋ ቆንጆ … አብደሏህን አንድ የከተማው ቆንጆ ካፌ ውስጥ ቀጥራ እየጠበቀችው ነው፡፡ ካፌው ቡኒ ቀለም ይበዛዋል፡፡ መብራቶቹ ፈዛዛ ናቸው፡፡ ከሚወዱት ጋር ለመመሰጥ ምቹ ቦታ ይመስላል፡፡ አብደሏህ ረፈድ አድርጎ ደረሰ፡፡ ፊቷ ቲማቲም መስሏል፡፡ እንዳለቀሰች ገባው፡፡ ስነ-ልቦናዋን አኝኮ በልቶታል፡፡ የአስራ ሁለት ዓመታት ርቀት አላቸው፡፡ ሰላሳ አምስት ዓመት አካባቢ ይሆነዋል፡፡
‹‹ምን ሆንሽብኝ?›› ግንባሯን ስሞ ተቀመጠ፡፡
‹‹እኔ ቆይ … ስላገባሁ ትምህርቴ ይቋረጣል?››
‹‹ኧረ በጭራሽ! እንደውም ተረጋግተሽ ትማሪያለሽ እንጂ!››
‹‹ሁሉም ትምህርቴን መደበቂያ ያደርጉታል፡፡ አሁን አታገቢም አሉኝ …››
‹‹ምን ይሻላል?›› አብደላህ ሙዱ ውርድ ሲል ተሰማው፡፡
‹‹እኔን ትጠይቀኛለህ እንዴ … አንተ ንገረኝ እንጂ!›› ተቆጣች፡፡
‹‹እሺ ቢሉኮ እኔም በስራ ቢዚ ስለምሆን ሁሌ ቤት አልኖርም በደንብ ነፃ ሆነሽ መማር ትችይ ነበር፡፡››
‹‹አግባኝ! … ቤተሰቦቼ ጉዳያቸው ነው … አግባኝ!››
‹‹አግባኝ?›› ደነገጠ፡፡
‹‹አዎ አግባኝ! ወይስ ትፈራለህ?››
‹‹ኧረ አልፈራም … ለነገሩ ልክ ነሽ … ስታገቢ እነሱም አማራጭ ስለማይኖራቸው ይቀበሉሻል፡፡›› ነፃ ምሳ ማን እንቢ ይላል?
‹‹ልክ ነህ መቼስ ልጃቸው ነኝ … ቆርጠው አይቆርጡኝም! ግን ያለ አባቴ ፈቃድ ማግባት ይቻላል?››
‹‹ቃዲ ጋ እሄዳለን … ሸሪዓ ፍርድ ቤት!››
‹‹ለምን አሁን አንሄድም?››
ቆንጆ የሴት ስሜታዊነት … ወደ ወንዱ ግብ ለመድረስ ሰከንድ አይፈጅበትም፡፡ ከካፌው ወጥተው ወደ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ተክለፈለፉ፡፡ ሆኖም በዕለቱ አገልግሎት ማግኘት ስላልቻሉ በቀጣዩ ሳምንት አስፈላጊ ነገሮችን አሟልተው ለመመለስ አሰቡ፡፡ 
***
‹‹ለምንድነው ሴት ልጅ የማታሰግደው? ሴት ልጅን ለማንቋሸሽ ያላቸው ድፍረት ነው የሚገርመኝኮ!›› ምህረት ስሜታዊ ሆና ታወራለች፡፡ የዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ቁጭ ብለው ያወጋሉ፡፡
‹‹ሴት ልጅ ከፊት ስትሆን … ድምፅዋም … ወንዱን ወደ ስጋዊ ስሜት ስለሚከተው መሰለኝ፡፡›› ሲሀም የምታውቀውን ለመመለስ ትሞክራለች፡፡
‹‹አይደለም፡፡ ሴት ልጅ መሪ ተደርጋ ስለማትሾም ነው፡፡ ኢማምነት መሪነት ነው፡፡ ሴት ደግሞ መሪ መሆን አትችልም፡፡››
‹‹ኢማም የሚለውን ደግሞ ከየት አወቅሽው?››
‹‹እያነበብኩ ነበር … ሀዲስ ሁሉ አለ ሴት ልጅን መሪ ያደረገ የተረገመ ነው ምናምን የሚል!››
‹‹አዎ ግን ሴት ልጅ ታሰግድ የሚለውን እኔም አላምንበትም … መሪነት የሚለውም ቢሆን ቀለል ያለውን ካልሆነ መግደል መጋደል ያለው ጉዳይ ነው፡፡ ከኛ ስሜታዊነት ጋር አብሮ የሚሄድ አይመስለኝም፡፡ ፔሬድ ላይ ስንሆን ራሱ ሺህ የስሜት መዘበራረቅ ነው የምናሳልፈው!››
‹‹አይደለም እንደዛ እንድታስቢ ያደረገሽ ሃይማኖት ነው፡፡ ሴት ልጅ ከማንም አታንስም፡፡››
ሰላሀዲን ከአቅራቢያቸው ተቀምጦ ምልልሳቸውን እያዳመጠ ነው፡፡
‹‹እሺ በጉልበትም አናንስም ነው?››
‹‹አዎ አናንስም! ከልጅነታችን በደንብ አካላዊ እንቅስቃሴ እያደረግን ስላላደግን ነው፡፡››
‹‹ሌላ ደግሞ ፈጣሪ የወር አበባ ላይ ስንሆን ወደሱ እንዳንቀርብ አዟል፡፡ ይኼ በሁሉም ሃይማኖቶች ነው፡፡ እራሱ ፈጥሮብን ራሱ ይጠየፍብናል፡፡›› ቤቲ ትልቅ ነጥብ እንዳስቆጠረ ሰው ፈገግ አለች፡፡
‹‹ስሙ እስኪ …›› ሰላሀዲን ውይይታቸውን ተቀላቀለ፡፡
‹‹ጀመረህ ደሞ አንተ!›› ምህረት ሰላሀዲን ሲያወራ ምቾት አይሰጣትም፡፡
‹‹ምናባታችሁ ፈጣሪ ላይ ትመፃደቃላችሁ? መጀመሪያ ሃይማኖት ማለትኮ እምነት ነው፡፡ ማመን የሚያስፈልገው ደግሞ የማታውቂውን ነገር ነው፡፡ አይተሽው የማታውቂን ነገር! ሲጀመር ፈጣሪን አይታችሁታል እንዴ? ሳታዩት መኖሩን የምታምኑት ጌታ ምንም አድርጉ ቢል የሚመዘነው በእናንተ አዕምሮ የልክነትና የስህተት ሚዛን አይደለም፡፡ የሚመዘነው በፈጣሪ የአዋቂነትና የመሻት ሚዛን ልክ ነው፡፡ ለምሳሌ በሁሉም ሃይማኖት ስግደት አለ፡፡ ስግደት ምንድነው? ቁጭ ብድግ አይደል እንዴ? ስለሱ ለምን አታወሩም? ፈጣሪ ቁጭ ብድግ ምን ይጨምርለታልና ነው የምንሰግደው? ለኛስ ምን ይጠቅማል? ትዕዛዝ ስለሆነ ነው የምንተገብረው! ለምሳሌ በእስልምና ውዱዕ የሚባል ትጥበት አለ፡፡ የሚበላሸው ፈስ በመፍሳት … በመፀዳዳት ምናምን ነው፡፡ አሁን የውዱዕ የትጥበት ቦታዎችና ፈስ ምንም የሚያገናኛቸው ነገር የለም፡፡ ግን በቃ ትዕዛዝ ነው፡፡ ፈጣሪ ስለፈለገ ይደረጋል፡፡ በምላሹ የፈጣሪን ውዴታ ለማግኘት ማለት ነው፡፡ የሃይማኖት ፅንሰ ሀሳብ ራሱ ስለ ትዕዛዛቱና ክልክላቱ አይደለም፡፡ እነሱን ለመከልከልም ሆነ ለመተግበር በውስጥሽ ስለሚኖረው ታዛዥነት ነው፡፡ ስግደትም ፀሎትም ለጌታሽ ምንም አይጠቅመውም፡፡ አንቺ ትዕዛዙን በመታዘዝሽ ውስጥ … የማይመችሽን ነፍስሽ የማይፈልገውን በመተግበርሽ … ነፍስሽ የሚፈልገውን በመከልከልሽ ውስጥ ነው አምልኮ ያለው፡፡
ታዲያ እዚህ ውስጥ ሴት ወንድ ምናምንን ምን አመጣው? ፈጣሪ ወንድ ከፊት ሆኖ ፀሎቱ እንዲመራ እፈልጋለሁ ካለ ከቁጭ ብድጉ በምን ተለይቶ ነው እንደ ልዩ ነገር አንስታችሁ የምትከራከሩበት? ይኼ የፈጣሪ ፍላጎት ነው፡፡ ጭራሽ ፈጣሪን ለምን እንደዚህ ፈለግክ ማለት እኮ ነው የቀራችሁ! የወር አበባ ላይ ስትሆን ሴት ልጅ አምልኮ አትስራ የሚለው አሁን እዝነት ነው ወይስ ክፋት? አሁን ክላስና ስራ እንኳን እያስፈቀደ አይደል እንዴ ያለው ሴቱ! ደግሞ በተለይ ሲሀም ፔሬድሽ ሲመጣ ስትንደባለይ አይደል እንዴ የምትውይው! ትስገድ ተብሎ ቢሆን ይኼኔ ተበደልን ብላችሁ ታለቃቅሱ ነበር! ኮተታሞች! መሪነት ላይ ደግሞ እስኪ የቷ ሴት ናት ጦርሜዳ ወርዳ ተዋግታ መሪነትን ስትይዝ ያያችሁት? መሪነት የሚሰጥ ነገር ነበር እንዴ? ሀገራችን ውስጥ እየተራረዱ አይደል እንዴ ንግስናን ሲቀባበሉት የነበረው ምነው ተሰጥቷቸው አስመሰላችሁት? ለምን ያኔ አልወሰዳችሁም? አቅማችሁ ስለማይችል ጭካኔ ነፍሳችሁ ውስጥ ስለሌለ አይደል? ወይስ አሁን ሰዉ ጫማውን ወልውሎ ቢሮ ሲቀመጥ ነው መሪነት ያማራችሁ? አፍሪካ ውስጥ አሁንም ሞት አለው … ሱፍ ለብሰው ስታዩ እንደናንተው እንዳይመስሏችሁ! ስለዚህ የመሪነት ሚና በወንድ ይያዝ ካለ ፈጣሪ የሰራውን


by the way ማለት ነው በመደፈር ምናምን ብቻ ሣይሆን in anyway especially እዚ ሀገር ለሴት ቦታ፣ክብር....የለም ተረስቷል
even እንደሁለተኛ ዜጋ የምንቆጠርበት ጊዜም አለ ለምን??
ሲቀጥል ነገሩ ከስር ከመሠረቱ ጀምሮ ቆንጠጥ ቢደረግ ይህ ሁሉ አይፈጠርም (የእንቁላሉ ጊዜ በተቆጣሽኝ በነበር እንዳለው ልጅ)
ለምሳሌ በየመንገዱ ተጎልተው የሚለክፉን ወንዶች 'አንድ' ቢባሉ ...anyone ትንሹ ሲፈቀድለት ነው ወደትልቁ የሚሸጋገረው

ግን ምንድን ነው no one ነው የምላችሁ for such type of thing ቦታ የሚሠጠው ... ልክ somebody ተደፈረች፣ሞተች ሲባል ግር ብሎ profile መቀየር story ማረግ ምናምን but it doesn't do anything for her because she already died...
There is proverb 'አይድረስ አሉ ከደረሠ ወዲያ'
ማለት አንዴ ከተደረገ በኋላ ቢጮህ ባይጮህ ...maybe ለሌሎች መቀጣጫ ይሆን እንጂ ለሷ ምንም አይጠቅማትም
so ምን ለማለት ፈልጌ ነው ነገሩ ከስር ጀምሮ control መደረግ አለበት ትንንሽ ነገራቶችም ቢሆኑ ችላ መባል የለባቸውም ‼️

Показано 20 последних публикаций.