Fetan Sport - ፈጣን ስፖርት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


ፈጣን ስፖርት የአውሮፓን ከፍተኛ የእግር ኳስ ሊጎች የሚሸፍን የኢትዮጵያ የዜና ቻናል ነው። ይዘቱም የቡድን ዜናዎችን፣ የጨዋታ ውጤቶችን፣ የተጫዋቾች ዝውውሮችን እና ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያካትታል።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


🚨 ዩናይትድ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ! 💔

ማንችስተር ዩናይትድ ከዎልቭስ ጋር ባደረገው ጨዋታ 2-0 ተሸንፏል። ግቦቹን ህዋንግ እና ኩንሀ አስቆጥረዋል። ⚽️

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በዚህ ዓመት 3ኛ ቀይ ካርዱን ተመልክቶ ከ19 ዓመታት በኋላ በአንድ ውድድር ዘመን 3 ቀይ ካርድ የተመለከተ የመጀመሪያው ዩናይትድ ተጨዋች ሆኗል። 🟥

አሞሪም 5ኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል። 📉

ደረጃ፡
1️⃣4️⃣ ማንችስተር ዩናይትድ - 22 ነጥብ
1️⃣7️⃣ ዎልቭስ - 15 ነጥብ

ቀጣይ፡ ሰኞ - ማንችስተር ዩናይትድ vs ኒውካስል 📅


🗣️ "የተጫወትነው ጥሩ ጨዋታ ነበር" - ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ቡድናቸው በዛሬው ጨዋታ ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረጉን ገልጸዋል። 🔵

"ቡድኑ በጥሩ ሁኔታ ተጫውቷል፣ ነገር ግን የሚያስፈልጉንን ጎሎች እያስቆጠርን አይደለም" ሲሉ፣ "በውጤቱ ደስተኛ አይደለንም፣ ነገር ግን አቋማችን የሚያስከፋ አይደለም" ብለዋል። ⚽️


🗣️ "ተጨዋች እናስፈርማለን" - ፔፕ ጋርዲዮላ 🔵

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ በጥር የዝውውር መስኮት ቡድናቸውን እንደሚያጠናክሩ አረጋግጠዋል። 📝

"በጥር የዝውውር መስኮት ተጨዋቾች ማስፈረም ከቻልን በእርግጠኝነት እናደርገዋለን" ሲሉ፣ የተከላካይ መስመር እና መሐል ሜዳ ማጠናከር ቅድሚያ እንደሚሰጡ ጠቁመዋል። ⚽️

አዲስ ተጨዋቾች የማስፈረም ሀሳቡን ነባር ተጨዋቾችም እንደሚደግፉት ገልጸዋል። 🤝


🚨 ሲቲ በዝውውር ገበያው ይሳተፋል! 💰

ማንችስተር ሲቲ በጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል። 🔵

በጉዳት ወሳኝ ተጨዋቾቹን እያጣ የሚገኘው ክለቡ የተከላካይ ክፍሉን ለማጠናከር ሲሆን፣ የሮድሪን ክፍተት የሚሞላ አማካይ እና የፊት መስመር ተጨዋች ለማስፈረም እያሰበ ነው። 📝

ክለቡ አሁን ላይ ከክለቦች እና የተጨያቾች ወኪሎች ጋር ንግግር ጀምሯል። 🤝


🗣️ "የቡድኑን ችግር እፈታዋለሁ" - ጋርዲዮላ 👊

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ያለበትን ችግር እንደሚፈቱ ሙሉ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። 🔵

"የተወሰኑ ጥርጣሬዎች ቢኖሩኝም እንደምፈታው ተስፋ አለኝ" ሲሉ፣ "ባለፉት 12 አመታት በሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፈናል፣ አሁን ግን አደጋ ላይ ነን" ብለዋል። ⚽️


🚨 ሲቲ ተጨዋቾቹን በልምምድ ማዕከሉ አሳድሯል! 🏟️

ውጤት ማጣት ውስጥ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ፣ ዛሬ በበዓል ሰሞን ከኤቨርተን ጋር ይጫወታል። ⚽️

ፔፕ ጋርዲዮላ ተጨዋቾቹ ትላንት ምሽት በክለቡ አካዳሚ ካምፕ እንዲተኙ መጠየቃቸውን ዴይሊ ሜል ዘግቧል። 🔵

ጨዋታው ዛሬ ቀን 9:30 በኢትሀድ ስታዲየም ይካሄዳል። ⏰


🗣️ "ዋንጫ ማሸነፍ እፈልጋለሁ" - ዳኒ ኦልሞ 🏆

ስፔናዊው የፊት መስመር ተጨዋች 2024 ለእሱ የተለየ አመት እንደነበር ገልጿል። ⚽️

"ከስፔን ጋር ዋንጫ የማሳካት እና በባርሴሎና ማለያ የመጫወት ትልቅ ህልሜን ያሳካሁበት ነበር" ሲል፣ በቀጣይ ከባርሴሎና እና ስፔን ጋር ዋንጫ ማሸነፍ እንደሚፈልግ ተናግሯል። 🔵🔴


💔 ዋልያዎች ከቻን አፍሪካ ተሰናብተዋል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን ጋር ባደረገው የቻን አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ 2-1 ተሸንፏል። ⚽️

የዋልያዎቹን ብቸኛ ግብ ብርሀኑ በቀለ ማስቆጠር ቢችልም፣ በአጠቃላይ በደርሶ መልስ ጨዋታ 4-1 በመሸነፍ ከውድድሩ ተሰናብተዋል። 🇪🇹

ሱዳን በ2025 በኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ በጣምራ በሚካሄደው ቻን አፍሪካ የሚሳተፍ ሆኗል። 🏆


🗣️ "መሐመድ ሳላህ እንደ ማሽን ነው" - ሉዊስ ዲያዝ 🔥

የሊቨርፑሉ ተጨዋች ሉዊስ ዲያዝ፣ ሳላህ በየቀኑ ራሱን ማሻሻል ለሚፈልግ ተጨዋች ትልቅ ምሳሌ መሆኑን ገልጿል። 👑

"ሳላህ ሁለት ወይም ሶስት ግቦችን ቢያስቅጥርም እንኳን በቀጣይ ቀን ስለ ሚቀጥለው ጨያታ ነው የሚያስበው" ⚽️

"እሱ በየቀኑ መሻሻል ለሚፈልግ ሰው ትልቅ ምሳሌ የሆነ ተጨዋች ነው፣ ከእሱ ብዙ መማር ይቻላል" 🔴


ክርስቲያኖ ሮናልዶ ገናን በማክበር ላይ 🎄❄️


🚨 ቫርዲ ለሊቨርፑል ጨዋታ ላይደርስ ይችላል! 🏥

ሌስተር ሲቲ ሐሙስ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ የጄሚ ቫርዲን ግልጋሎት ላያገኙ እንደሚችሉ አሰልጣኝ ቫን ኔስትሮይ አረጋግጠዋል። ⚽️

በውድድር አመቱ 6 የሊግ ግቦችን ያስቆጠረው ቫርዲ በጉዳት ምክንያት መድረሱ አጠራጣሪ ሆኗል። 🔵

ግብ ጠባቂው ማድስ ሄርማንሰንም በጨዋታው እንደማይሳተፍ ተገልጿል። 🧤


🗣️ "ሲቲ ወደ ዋንጫ ፉክክሩ ይመጣል" - ማሬስካ 🏆

የሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ስለ ዋንጫ ፉክክር ያለማሰባቸው "ጫና ሳይሆን እውነት ነው" ብለዋል። 🔵

"እንደዚህ አይነት ጫናዎች መቋቋም እንፈልጋለን። ነገርግን የተናገርነው እውነታ ነው" ሲሉ፣ "ማንችስተር ሲቲ በመጨረሻ ሰዓት ወደ ፉክክሩ ይመጣል" ብለዋል። ⚽️

"ሲቲ ከዚህ በፊት ገጥሟቸው በማያውቅ ችግር ውስጥ እያለፉ ነው፣ በየጨዋታው ጉዳት እያጋጠማቸው ነው" 💭


🗣️ "ትኩረቴ ራሽፎርድን ማሻሻል ላይ ነው" - አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የራሽፎርድን ቃለምልልስ ወደ ጎን በመተው አቋሙ ላይ ብቻ እያተኮሩ መሆኑን ገልጸዋል። 🔴

"እንደሱ አይነት ተሰጥኦ ያለው ተጨዋች ያስፈልገናል። እሱ ያደረገውን ቃለምልልስ ረስቼ ሜዳ ላይ የማየውን ብቻ እየተመለከትኩ ነው" ብለዋል። ⚽️

"እንደዚህ አይነት ተጨዋቾች በዙሪያቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ እረዳለሁ፣ አንዳንድ ጊዜ የራሳቸው ሀሳብ ያልሆነ ውሳኔም ይወስናሉ" 💭


🚨 በኦልድትራፎርድ አይጦች ማስቸገራቸው ተገለጸ! 🏟️

በማንችስተር ዩናይትዱ ኦልድትራፎርድ ስታዲየም አይጦች ማስቸገራቸውን ዴይሊ ሜይል ዘግቧል። 🐀

የአካባቢው የንፅህና ተቆጣጣሪዎች በስታዲየሙ አይጥ ማግኘታቸውን ተከትሎ፣ ክለቡ ከነበረው 5 ኮከብ የንፅህና ደረጃ 2 ደረጃዎች ቀንሷል። ⭐️

አብዛኞቹ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች 5 ኮከብ የንፅህና ጥራት ደረጃ እንዳላቸው ሲገለጽ፣ ዩናይትድ ችግሩን ለማስተካከል እየሰራ ነው። 🧹


🚨 አርሰናል ተጨዋቹ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል! 🏥

የአርሰናል ተጨዋች ቡካዩ ሳካ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ለበርካታ ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ አርቴታ አረጋግጠዋል። ⚪️

"ሳካ ያጋጠመው ጉዳት ጥሩ አይመስልም፣ ከታሰበው የከፋ ሊሆንም ይችላል" ሲሉ አርቴታ ገልጸዋል። 😔

ራሂም ስተርሊንግም በተመሳሳይ በጉዳት ምክንያት ለሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተጠቁሟል። 🔴


🚨 አንቾሎቲ ተጨዋች ማስፈረም ይፈልጋሉ! 📝

የሪያል ማድሪዱ ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በጥር የዝውውር መስኮት አዲስ ተጨዋች ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተገልጿል። ⚪️

የክለቡ ቦርድ በበኩሉ በጥር ወር ተጨዋች የማስፈረም ፍላጎት እንደሌላቸው ዘ አትሌቲክ ዘግቧል። 👀

በጉዳት ምክንያት በርካታ ተጨዋቾቹን ያጣው ሪያል ማድሪድ ቡድኑን ለማጠናከር ወደ ዝውውር ገበያው እንደሚወጣ ይጠበቃል። 🔄


🗣️ "በሌላ አቅጣጫ ሪከርድ እያስመዘገብን ነው" - ጋርዲዮላ 📉

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ጋርዲዮላ "ይሄ ጥሩ ነው የሚባል ነገር የለውም" ሲሉ ተናግረዋል። 🔵

"ውጤቱ የለም እንጂ ጥሩ እየተጫወትን ነው ብዬ የምናገረው ነገር የለኝም። ሁሉም ቁጥሮች መጥፎ ናቸው" ብለዋል።

"እስካሁን በርካታ ሪከርዶችን ስንሰብር ቆይተናል። አሁን ደግሞ በተቃራኒ አቅጣጫ ሌሎች ሪከርዶችን መስበር ጀምረናል" 💭


🚨 ሊቨርፑል መሪነቱን አጠናክሯል! 🏆

በ17ኛው ሳምንት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሊቨርፑል ቶተንሀምን 6-3 አሸንፏል። ⚽️

ግቦቹን፡ ሳላህ(2)፣ ዲያዝ(2)፣ ስቦዝላይ እና ማክ አሊስተር ሲያስቆጥሩ፣ ለቶተንሀም ሶላንኬ፣ ኩሉሴቭስኪ እና ማዲሰን መልሰዋል። 🔥

ሳላህ በዚህ ዓመት 25 የግብ ተሳትፎዎችን በማድረግ ቀዳሚ ሲሆን፣ 15 ግቦችን በማስቆጠር የሊቨርፑል 4ኛው ከፍተኛ ግብ አግቢ ሆኗል። 👑

ደረጃ፡
1️⃣ ሊቨርፑል - 39 ነጥብ
1️⃣1️⃣ ቶተንሀም - 23 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ፡
📅 ሐሙስ፡ ሊቨርፑል vs ሌስተር | ቶተንሀም vs ፎረስት


🗣️ "ክፍት ጨዋታ እንደሚሆን እናውቅ ነበር" - ሳላህ

የሊቨርፑሉ ኮከብ መሐመድ ሳላህ የቡድናቸው የተከላካይ ክፍል መሻሻል እንዳለበት ገልጿል። ⚽️

"ቡድናችን የተከላካይ ክፍሉ መሻሻል አለበት፣ ሶስት ግቦች ተቆጥረውብናል" ሲል ተናግሯል። 🔴

የኮንትራት ማራዘሚያ ጥያቄውን በተመለከተ ግን አስተያየት ለመስጠት አልፈለገም። 📝


🚨 ሪያል ማድሪድ ድል አድርጓል! 🏆

በስፔን ላሊጋ የአስራ ስምንተኛ ሳምንት ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ሲቪያን 4-2 አሸንፏል። ⚽️

የሎስ ብላንኮዎቹን ግቦች ኪሊያን ምባፔ፣ ቫልቬርዴ፣ ሮድሪጎ እና ብራሂም ዲያዝ ሲያስቆጥሩ፣ ለሲቪያ ሮሜሮ እና ሉኬባክዮ መላሽ ሰጥተዋል። 🔥

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ፡
2️⃣ ሪያል ማድሪድ - 40 ነጥብ
1️⃣2️⃣ ሲቪያ - 22 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ፡
📅 አርብ - ቫሌንሽያ Vs ሪያል ማድሪድ
📅 ቅዳሜ - ሲቪያ Vs ቫሌንሽያ

Показано 20 последних публикаций.