የመጀመሪያው ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት ሊካሄድ ነው ‼️
“የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት” (Ethiopian National Students' Award) በትምህርቱ ዘርፍ በአዋጅ የተቋቋመ በሀገራችን ብቸኛው እና የመጀመሪያው ብሔራዊ የትምህርት የሽልማት ድርጅት ነው። ድርጅታችን በትምህርት ላይ መስራት የተቋቋመለት ዋና ዓላማ ሲሆን በሀገራችን ብቸኛ እና የመጀመሪያ የሆነውን “የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት” ዓመታዊ ፕሮግራም በወርሃ ታህሳስ 2017 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በይፋ ብቁ ተማሪዎችን በመሸለም የሚጀመር ይሆናል፡፡
የዚህ ሽልማት ትልቁ ዓላማ ውጤታማ ተማሪዎችን እና ምስጉን መምህራንን መሸለም፣ በመማር ማስተማሩ ምሳሌ የሆኑ የመንግስትና የግል የትምህርት ተቋማትን እውቅና መስጠት፣ ለሀገራችን የትምህርት ልማት ሁለንተናዊ ለውጥ አስተዋጽኦ በማድረግ ለትውልድ አርኣያ መሆን የቻሉ ተቋማት፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች እውቅና የሚያገኙበት ዝግጅት ነው፡፡
ስለሆነም በሚዲያው ዘርፍ ውስጥ ላላችሁ ሁሉ ዕረቡ ታህሳስ 2/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገነተ ልዑል አዳራሽ ዝግጅቱን በተመለከተ ለሚዲያ አካላት ከጠዋቱ 3፡30 በምንሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በተጠቀሰው ቦታ ተገኝታችሁ የዜና እና የፕሮግራም ሽፋን ትሰጡልን ዘንድ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡ (የሽልማት ድርጅቱ)
https://t.me/fresh_handouts