ሚዛን
(ፉአድ ሙና)
.
እየተክለፈለፈ መጥቶ መንገዴን ዘጋብኝ። ወሬ በማመላለስ የታወቀ ነው። የሆነ ወሬ ለመጠየቅ መሆኑ አልጠፋኝም። ቆምኩለት።
«ስማማ!»
«ምን ልስማ?»
«ከምትወዳት ልጅ ጋር ተለያያችሁ የሚባለው እውነት ነው?»
«አዎ!»
«ለምን ተለያያችሁ?»
«የማይታለፍ ነገር ተፈጥሮ!»
«ደሞ አንተ ነህ አይደል የተውካት?»
«አዎ ተውኳት!»
«እንደዚያ ሰማይ ጠበበኝ እንዳላልክ?»
«ብልስ!»
«አትወዳትም ነበር ማለት ነው እንጂ እንዲ በቀላሉ አይቆርጥልህም ነበር!»
«ማነው ያለው?»
«ቀይስን አታየውም እንዴ የሚወደውን ሲያጣ እንዴት እንዳበደ... መጅኑኑ ለይላ ተብሎ እስኪታወቅ!»
«ወላሒ?»
«ማላገጡን ተወውና መልስልኝ!»
«ቀይስ ታዋቂ የሆነው በግጥሞቹ እንጂ በአፈቃቀሩ ትክክለኛነት አይደለም። ልብ ላይ ለአላህ የሚሰጥን ቦታ ሳይቀር ጠቅልሎ ለፍጡር መስጠት... ጭራሽ እስከማበድ መድረስ በፍፁም ልክ ሊሆን አይችልም።»
«እና ያንተ ነው ልኩ?»
«አዎ ልክ ነኝ! በጣም እወዳት ነበር። ላገባት አልሜም ነበር ግን አልሆነም። ስለዚህ ማበድ የለብኝም። ሊከብድ ይችላል እኮ! ሳያመኝ ቀርቶም አይደለም። ግን ዋጥ አድርጌው ነው። በቃ በሂደት ይሽራል። ለፍጡር የሚሰጠው ቦታ እንደዚያ ነው። ሁሉም ነገር የሚሰጠው ለኻሊቁ ብቻ ነው!»
ተነፈስኩ። ደርሶ መካሪዎች ስለማያውቁት ፍቅር ሊሰብኩኝ ሲሞክሩ ይገርመኛል። ትናንት የምንወደውን ሰው ልንለየው አንችልም ማለት አይደለም። ዛሬ ስለተለየነውም ትናንት አንወደውም ማለት አይሆንም። ግን ሚዛንን መጠበቅ ያሻል። ሁሉም ነገር አይሰጥም። በእርግጥ ለማሽሟጠጥ ብለው እንጂ አሳስቧቸው አይደለም። አሽሟጣጭ ሁላ!
.
@Fuadmu