ዋ... ወንድነት!
(ፉአድ ሙና)
.
የኔ ቆንጆ... ለሁላችንም ያላቸውን ጥላቻ ባንቺ በኩል ለማስተንፈስ ሲሞክሩ እያየሽ ነው አይደል? የኔ ያልሻቸው ደም የተጋራሻቸው ሰዎች... እንወድሻለን ያሉሽ ቁሸቶች ጊዜ ጠብቀው ምን እንደሚደግሱልሽ ተረዳሽ? «ድህረ ሰላም... እስላም!» ብለው ከመጀመሪያው ዝተውልሽ ነበር አሉ!
ገና ከፌደራል መንግስቱ ጋር የያዙት ጦርነት ሳያልቅ የበቀል ክንዳቸውን እንዴት አንቺ ላይ እንደሚያሳርፉ ሲጎነጉኑ የነበሩ የፍጥረት አተላዎች ናቸው። ቀን በቀን የአላህን ንግግር እውነታነት ቢያስረግጡልሽ አትገረሚ!
የሚያስመልጥሽ ክንድ የለም። ይጋፋበት ክንድ ያለው አንድ እንኳን ሙስሊም ወንድ የለሽም። ሁሉም የበታች ነው። ሁሉም ወራዳ ባሪያ ነው። ርካሽ ነን የኔ አለም። አንቺን እናድንበት ድምፃችን ሰሏል። እንደቁስበት ክንዳችን ዝሏል። በፍርሀት ተሸብበን ሁኑ ያሉንን እየሆንን ነው የኔ ንግስት!
ጌታሽ ቀድሞ እነዚህ ጠላቶችሽ በደም አይደለም በስጋ አካል እንኳን ብትጋሩ እንደማይመለሱልሽ ነግሮሽ ነበር።
«وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللَّهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ
አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡» (በቀራ፣ 120)
ድረስልኝ አትበይኝ የኔ ፍቅር! በስሜቴ የተተበተብኩ ርካሽ ነኝ! እንደ ሙዕተሲም አዘምትልሽ ጦር፤ እቆጣልሽ ወንድነት የለኝም። ሲልኩኝ ወዴት ሲጠሩኝ አቤት የምል ወራዳ ነኝና ወደኔ አትጣሪ። ወደ አላህ ጩሂ የኔ ውድ! ወደማይነጥፈው ንግስና ተጣሪ! የእርሱ ክንድ አይዝልም። እርሱ ይደርስልሻል ውዴ!
«فَفِرُّوا إِلَى اللَّهِ ۖ
«ወደ አላህም ሽሹ፤» (ዛሪያት፣ 50)
እኔ ግን ለራሴ ብቻ ሳይሆን ላልመለስኳቸው የድረስልኝ ጩኸቶችሽም አነባለሁ! ለራቀኝ ወንድነት... ለተሸከምኩት ወራዳነት እንሰቀሰቃለሁ። አንድ ቀን ጭንቅላቴ ቀና ይላል። ሲነኩሽ አይሆንም ብዬ አስቆምበት ክብር አገኛለሁ ብዬ ከጌታዬ እከጅላለሁ። እስከዛው ግን ውዴ ወደ ጌታሽ ጩሂ.... እኔ ወራዳ ሆኛለሁ።
በበዳዮች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ!
.
@Fuadmu