መፈቀር
(ፉአድ ሙና)
.
ቤብ... እወድሻለሁ ሲልሽ አመንሽው? ንገሪኝ! አፈቅርሻለሁ ሲል ተቀበልሽው ወይ? ለምን? በምን እርግጠኛ ሆንሽ? ባለትዳር ራሱ ብትሆኑ እንደሚወድሽ በምን አወቅሽ?
ይኼኔ የእኔን ፅሁፍ እየላከ ነው አይደል ያሰመጠሽ? በየትኛው ነው የጀነጀነሽ? በልብወለዶቹ ወይስ በግጥሞቼ? እንዳትሸወጂ ቤብ! ቢያገባሽ እንኳን እንደሚወድሽ እርግጠኛ መሆን አትችይም!
እና በምንድነው እርግጠኛ የምሆነው አልሽ? ለምን የእኔዋ ያረጋገጠችበትን መንገድ አላጫውትሽም? እሁድ ጠዋት ነበር። ውዴ ሀይድ ላይ ነበረች። ሀይድ ላይ ስትሆን ድካም ድካም ይላታል። ብርድልብሱን ገፍፋ እግሮቿ ስር ሰብስባው ጭው ያለ እንቅልፍ ጥሏታል። ግንባሯን ስሜ በጠዋቱ ወደ ቀጠርኩት ሰው ለመሄድ መለባበስ ጀመርኩ።
እየለባበስኩ በስስት አየኋት። ታምራለች። ከጀልኩ... ከዛ ግን ሲዝኑ እንደማይፈቅድ ራሴን አስታወስኩት። (ላጤ ሆይ ሴቶች ሰላት በሌላቸው ወቅት ነፃ ፍልሚያ እንደሌለ እወቅ!) በስስት ካየኋት በኋላ ፍቅሬን የምገልፅበት ቆንጆ ስጦታ አሰብኩ።
ከመቅፅበት ስልኬን አውጥቼ የባንክ አካውንት ቁጥር ፃፍኩና ሪዝኑ ላይ For my love ብዬ አስተላለፍኩ። ስክሪን ሾት አድርጌ ከእንቅልፏ እንደነቃች ታየው ዘንድ ላኩላት።
ከሄድኩበት ስመለስ ሚስቴ ፊቷ ተንቆጥቁጧል። እንዳየችኝ እየሮጠች መጥታ ተጠመጠመችብኝ። ምነው ስላት «እስከዛሬ እንደምወድህ አውቅ ነበር፤ ዛሬ ግን እንደምትወደኝ አወቅኩ።» አለች።
እና አሁንም ሪል ነው ሼር የሚያደርግልሽ ቤብ? አንቺስ ብትሆኚ? «ሴት ልጅን ለማስደሰት የሚረዱ ቁልፍ ጥበቦች» የሚል ፅሁፍ ነው የምትልኪለት? በቃ ይሄ ነው ውዴታሽ? ውዴታህ?
አሁን @Fuadmuna ላይ ናና አካውንት ስጠኝ በለኝ። እኔ ደሞ አልሰስትም እሰጥሀለሁ። አንቺም ቢሆን እንደዛው! በምሰጣችሁ አካውንት የጉድጓድ ውሀ ለማስቆፈር የሚውል የአቅማችሁን ገንዘብ በምትወዱት ስም አስገቡ። ሪዝን ላይ For my Love በልና አስገባ። ከዛ ስክሪን ሾት አድርገህ ላክላት። ዘላቂ አጅር ከመሸለም ወዲያ ምን ፍቅርን ይገልፃል ወገን? ካገባህ አዳርህ ይባረካል... ካላገባሽ ትዳርሽ ይፈጥናል ስልሽ!
አንተ ዝም ብለህ ሪል ላክ ሰው ሰደቃ ይልካል 😂😂😂
.
@Fuadmu