ከላይኛው የቀጠለ...
በዚህም የመምህርነት ሞያውን በደብረዘይት ከተማ "BCI Academy " ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት በፊዚክስ አስተማሪነት ይጀምራል።
ለ3 ዓመታት በመምህርነት ተቀጥሮ ከሰራ በኋላም በቢሾፍቱ ከተማ "School of My Seed" የሚባል የማጠናከሪያ ትምህርት መስጫ ተቋም አቋቁሞ የፊዚክስ የትምህርትን እያስተማረ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ቪዲዮችን መልቀቅ ጀመረ።
በተለያዩ የማኅበራዊ ገፆች ላይ ያሉት አብዛኞቹ ቪዲዮዎቹ የሚቀረጹት በማጠናከሪያ የትምህርት ፕሮግራም ላይ ሳለ የቀረጻቸው መሆኑን የሚናገረው መምህር ዳኛቸው የዚህን ያህል ተቀባይነት ይኖረዋል ብሎ እንዳላሰበ ይናገራል።
የማጠናከሪያ ትምህርት ተቋሙን ከባለቤቱ ጋር በመመካከርጀመረው 16 ተማሪዎችን በመያዝ ነበረ። ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን የተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ ሌሎች መምህራንንም ቀጥረው ማስተማር ቀጠሉ።
በቢሾፍቱ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ በነፃ 24 ሰዓት የሚያገለግል የተማሪዎች ቤተ-መጽሐፍ ቤት በማዘጋጀትም ማንኛውም ተማሪ በነፃ አገልግሎት እንዲያገኝ አድርጎም እንደነበር አስታውሷል።
መምህር ዳኛቸው ከ2000 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችን ማስተማሩን ይናገራህ። ሆኖም ይህ ጥረቱ ሳያስበው በአጭርተቀጨ። ተቋሙ ተዘግቶ ማስተማር አትችልም የሚል ትዕዛዝ ተሰጠው።
ምን ተፈጠረ ?
በዘንድሮው ዓመት 50 አካባቢ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስተማር አቅድ ማውጣቱን፤ ነገር ግን የተመዝጋቢዎች ቁጥር ግን ከ300 መሻገሩን ይጠቅሳል።
"ሁሉንም የምናስተምርበት አቅሙ ስላልነበረን ግዴታ ተማሪዎቹን መፈተን ነበረብን እና ፈትነን መቶ ተማሪዎችን በውጤታቸው መርጠን ማስተማር ጀመርን'' ሂደቱን ያስረዳል።
ሥራቸውን ከጀመሩ በኋላ ግን ማስተማር አትችልም ተብሎ ተቋሙ እንደተዘጋበት እና በመጀመሪያ የተለያዩ ምክንያቶች ቢቀርቡለትም ኋላ ላይ ግን ነገሩ ሌላ መሆኑን እንደተረዳ ይናገራል።
መምህር ዳኛቸው ገለጻ ሳይመረጡ ከቀሩት ተማሪዎች መካከል አንዷ ተማሪ የከተማው "ከፍተኛ ባለስልጣን " ልጅ እንደነበረችና እና፣ እሷን ባለመምረጣቸው ተቋሙ እንዲዘጋ ትዕዛዝ እንደወጣበት ይናገራል።
በቻለው አቅም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመግባባት ቢሞክርም ሳይሳካ ቀርቶ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በኦንላይን ማስተማር ጀምሯል።
መምህር ዳኛቸው አሁን ላይም ከሀገር ውጭ ያሉ 16 ተማሪዎችን በኦንላይን እያስተማረ ይገኛል።
ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበረው ቆይታ በቢሾፍቱ ከተማ ያቆሙትን የማስተማር ስራቸውን በአዲስአበባ ከተማ ለማስቀጠል ጥረት እያደረገ እንደሆነ ነግሮናል።
በቀጣይስ ?
"አንድ ነገር እፈልጋለሁ፣ ሰርቭ ( serve ) የማደርግበት መንገድ ቢመቻችልኝ፣ ልጆች አንድም ለእናት የለቅሶ ምክንያት፣ ለአባትም የጉስቁልና ምክንያት እንዳይሆኑ ባደርገቸው ነፍሴ ታርፋለች " ይሄን ለማድረግ ጥረት እያደረኩ ነው። የመንግስት አካላም ሆነ የግል ድርጅቶች እድሉን እንዲያመቻቹልኝ እፈልጋለሁ " በማለት ይናገራል።
ተማሪዎቹ ምን ይላሉ ?
እሱ ካስተማራቸው ተማሪዎች አሁን ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ አሉ። ስለቀረቤታቸው ሲናገሩም ''መምህራችን የሚለው ቃል ያርቅብናል፣ ብቻ እሱ ከቤተሰብም በላይ ነው፡፡ እንደተማሪና መምህር ሳይሆን እንደ ልጅ እና አባት ነው፡፡'' ሲሉ ምስክርነት ይሰጣሉ።
የሚያስተምሩበት መንገድ በጣም ቀላል እና ግልፅ ከመሆኑ የተነሳ ሳይገባቸው ያለፉት ነገር እንደሌለ እና የሀገር አቀፍ ፈተና ጥሩ ውጤት ለማምጣታቸውም የመጀመሪያውን ድርሻ የሚወስዱት መምህር ዳኛቸው መሆኑን ይጠቅሳሉ።
አሁን ላይ በቢሾፍቱ ማስተማራቸውን እንዲያቆሙ መደረጉ መጭው ትውልድን መበደል ነው ሲሉም የቀድሞ ተማሪዎቻቸው ይናገራሉ።
@genius_acadamy@genius_acadamy