የፊዚክስ መምህሩ ማነው ?
#Ethiopia | ከሰሞኑ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይየፊዚክስ መምህሩ የሚያስተምሩበት መንገድ በቪዲዮ ከተለቀቀ በኋላ እንደ አዲስ በበርካቶች ዘንድ አድናቆት እየተቸረው ነው፡፡
ከሰሞኑ በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ የሆነውን የፊዚክስ መምህር ቲክቫህ ኢትዮጵያ አግኝቶ ስለ ልምዱና ስለ አጠቃላይሥራው ጠይቋል።
የፊዚክስ መምህሩ ዳኛቸው ሻምበል ይባላል። ውልደት እና እድገቱ በድሬዳዋ ሲሆን እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርቱን ያጠናቀቀው በድሬደዋ ብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት ነው፡፡
በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲም የሜካኒካል ምህንድስና የትምህርት ክፍል ተቀላቅሎ 1 ዓመት ከ6 ወር ቢማርም በኋላ ባልሆነ ሱስ ተጠምዶ ትምህርቱን ማጠናቀቅ ሳይችል እንደቀረ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበረው ቆይታ ያስታውሳል።
ወደ ቻይና የመሄድ እድል ያገኘው ዳኛቸው፥ ሀንዦ በሚባል ትምህርት ቤት በኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርቱን ተከታትሎ በጥሩ ውጤት አጠናቆ ወደ ሀገር ቢመለስም የነበረበት ሱስ ህይወቱን እጅግ ፈታኝ አደረገበት።
በዚህ ምክንያትም ወደ ጎዳና ህይወት መግባቱን የሚናገረው መምህር ዳኛቸው፤ ኑሮውን በአዲስ አበባ ጎዳኖች ላይያደረገበት የህይወት አጋጣሚም ነበረ።
ታዲያ የመምህሩ ህይወት እንዴት ተቀየረ ?
ከቢሾፍቱ አዲስ አበባ ቅዳሜ እና እሁድ ለሥራ ስትመላለስ የነበረች ነርስ ጋር አጋጣሚ ያስተዋውቃቸውና ታሪኩን እንዳካፈላት፤ ታሪኩን ከሰማች በኋላም በማዘኗ ግንኙነታቸው እንደቀጠለ ያስረዳል።
ይህች ሴት የአሁን ባለቤቱ እንደሆነች የነገረን መምህርዳኛቸው፥ በሷ ድጋፍና እርዳታ የጎዳና ህይወቱ ማብቃቱን አጫውቶናል፡፡
ለአባቱ ልዩ ክብር እንደነበረው የሚናገረው መምህር ዳኛቸው ከጎዳና ህይወት ከወጣ በኋላ ወደ መምህርነት ለመግባቱም አባቱ ለእሱ የከፈለው ውለታ ጉልበት እንደሆነው ይናገራል።