የመውጫ ፈተና - Exit Exam
የትምህርት ሚኒስቴር ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የመውጫ ፈተና በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የመውጫ ፈተና በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ መሰጠት እንዳለበት የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ቁጥር 919/2014 ይደነግጋል።
ስለሆነም በጥር ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ እንዲቻል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ማለትም፡
1. ከዚህ ቀደም በሀገር አቀፍ ደረጃ የመውጫ ፈተና ያልተሰጠባቸው አዲስ ፕሮግራሞች ዝርዝር፤
2. በጥር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በተቋማችሁ የሚፈተኑ እጩ ምሩቃን ያለበት ፕሮግራሞች ዝርዝር፤
3. በጥር 2017 ዓ.ም በመደበኛ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን አጠናቀው ፈተናውን ለመውሰድ የተዘጋጁ እ ምሩቃን በቁጥር(ወ----ሴ---ድ---)
4. በጥር 2017 ዓ.ም መደበኛ ባልሆኑ (በክረምት፣ በርቀት፣ የማታ፣በበይነ መረብ ...) መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን አጠናቀው ፈተናውን ለመውሰድ የተዘጋጁ እጩ ምሩቃን በቁጥር
እስከ 25/03/2017 ዓ.ም ድረስ የምርምር፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና የአፕላይድ ዩኒቨርሲቲዎች በኢሜይል እና ኮምፕሪሄንሲቭ ዩኒቨርሲቲዎች በኢሜይል semusisay2007@gmail.com tekljezeleke2009@gmail.com እንዲሁም የግል ዩኒቨርስቲዎች በኢሜይል eyobie2002@yahoo.com እንድታሳውቁን እናሳስባለን።