Ghion Maleda


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


እንኳን ደህና መጡ !
ማስታወቂያ ለማሰራት 👉 @GhionMaleda13
ቴሌግራም ቻናሉን ለመቀላቀል👉@GhionMaleda
ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/GhionMaleda
ደግና ቅን እንሁን ❤🙏

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


ድምፃዊት ሄለን በርሄ በቅርቡ የተሰራጨውን ቪዲዮ እና በድምጿ ላይ የተነሱ ወሬዎችን አስተባበለች

ታዋቂዋ ድምፃዊት ሄለን በርሄ በ«Seifu on EBS» የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ ቀርባ በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን የመድረክ ስራ ቪዲዮ እና ስለ ድምጿ የተነሱ ሀሜቶችን አስመልከቶ ማብራሪያ ሰጥታለች።

ድምፃዊቷ በቃለመጠየቋ ወቅት እንደተናገረችው፦ በድምጿ ላይ ምንም አይነት ችግር እንደሌለባት እና በቀጥታ የመድረክ ትርኢትም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች ላይ በሙሉ ብቃት መዘመር እንደምትችል ገልጻለች።

የጉንፋን ወይም የጉሮሮ መዘጋት አጋጣሚዎች ቢኖሩ እንኳ ለየት ያለ ድምፅ ሊፈጥር ይችላል እንጂ ድምፅ የሚያጣ ብቃት የለኝም ብላለች።

ከላይ በምታዩት ቪዲዮ ላይ የተሰማው ድምፅ የተወሰደው በሙዚቃ ትርኢት ወቅት ከሞኒተር ስፒከር በተወሰደ የድምፅ ቅንብር መሆኑን ጠቅሳለች።

ይህንንም የድምፅ ቅንብር በማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) ላይ ያሰራጩት ሰዎች የራሳቸውን ዓላማ ለማሳካት ያደረጉት እንደሆነ እና ድምጿን አዛብተው ለማቅረብ እንደሞከሩ መናገሯን ግዮን ማለዳ ተመልክቷል ።

ድምፃዊቷ ድርጊቱን አስመልከታ ወዲያውኑ ምላሽ ለመስጠት አለመምረጧን ገልጻለች። ህዝቡ እና አድናቂዎቿ የራሷን ትክክለኛ የሙዚቃ ስራዎች እንደሚያውቁ በመተማመን ዝምታን መምረጧን አስረድታለች።

በቪዲዮው ዙሪያ ለቀረበላት ጥያቄ ሲመልስ፣ ከዮኒ ማኛ ጋር በቤተሰብ ደረጃ የተቀረበ እውቅና እና አክብሮት እንዳላቸው ገልጻለች። ቪዲዮው በእሱ ዘንድ የደረሰው በሰዎች መካከል በነበረ አለመግባባት ምክንያት እንደሆነ ጠቁማለች።

በአጠቃላይ ድምፃዊት ሄለን በርሄ በሙዚቃ ስራዋ ላይ ሙሉ ዝግጅት እና ብቃት እንዳላት በመግለጽ፣ በአድናቂዎቿ ዘንድ የተፈጠረውን ብዥታ ለማጥራት ሞክራለች።

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ልጆቻችሁን ከእንደዚህ አይነት ጭራቅች ጠብቋቸው ። ለህግ ይቅረብ እየተባለ እስከመቼ ነው ህፃናት በዚህ መልኩ የሚቀጥሉት ?

Joined ቴሌግራም 👉 T.me/GhionMaleda


የውጭ ሰላዮችና ሀገር  ውስጥ ተባባሪዎቻቸው የሞት ቅጣት ይጠብቃቸዋል ። -ኢብራሂም ትራኦሬ

የቡርኪና ፋሶ መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ፣ በአገሪቱ ላይ የስለላ ተግባር የሚፈጽሙ የውጭ ወኪሎችና ከእነሱ ጋር የሚተባበሩ የአገር ውስጥ አካላት ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቀዋል።

ትራኦሬ በዋና ከተማዋ ኡጋዱጉ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ በቡርኪና ፋሶ ላይ ስለላ ሲያካሂድ የተያዘ የውጭ ሰላይ ወይም ከውጭ ኃይሎች ጋር የሚተባበር የአገር ውስጥ አካል ከባድ የሕግ እርምጃ እንደሚጠብቀው መግለፃቸውን ግዮን ማለዳ ከመግለጫው ተመልክቷል ።

መሪው ቀደም ሲል የውጭ ወኪሎችን ከአገር ማባረር ብቻ የሚያበቃውን አሰራር «የበፊት ስህተት» በማለት ገልጸው፣ ይህ አሰራር እንደማይደገም አሳስበዋል። «የምህረት ዘመን አብቅቷል» ሲሉም ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ትራኦሬ አንዳንድ የውጭ የስለላ መረቦች በዲፕሎማሲያዊ ሽፋን በአገሪቱ ውስጥ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆነም ከሰዋል። በተለይም ፈረንሳይን በመጥቀስ፣ ፓሪስ በቡርኪና ፋሶ የሚንቀሳቀሱ አገርን ለማወክ የሚሹ ቡድኖችን ትደግፋለች ሲሉ ከሰዋል።

በተያያዘም፣ ቡርኪና ፋሶ በ2018 ያስወገደችውን የሞት ቅጣት ለከፍተኛ ክህደት፣ ሽብርተኝነትና ስለላ ወንጀሎች መልሳ ለመተግበር የሚያስችል የሕግ ማሻሻያ ረቂቅ በመንግሥት ደረጃ መንገድ ላይ መሆኑ ተገልጿል።

የትራኦሬ ይህ አቋም ለቡርኪና ፋሶ የደህንነት ሁኔታ ምን ያመጣል? እርስዎስ የሞት ቅጣት መመለስን ይደግፋሉ?

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda


የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ልመናችንን ይስማን፤ምልጃ እና ረድኤቱም አይለየን🙏

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል፡፡ ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አምነው ለሚጠሩት ረዳት ነው፡፡ በመዝሙር 33÷7 እደተጻፈው ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፡፡ እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል እንደተናገረው ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው፡፡ ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ ይህንን ድንቅ ተአምር መስከረም ዘጠኝ ቀን መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን ትመሰክራለች፡፡ በቀድሞው የሮም ግዛት 'ሩፍምያ' የምትባል ከተማ ነበረች፡፡

ይህች ከተማ በእምነታቸው ጠንካሮች የሆኑ ጥቂት ክርስቲያኖችና በርካታ ኢአማንያን ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት፡፡ በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ፍጹም የእምነት ሰው ነበር፡፡ በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረግ ስለነበር ተበለጥን የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ “ዮናናውያን”ይሕንን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ፡፡ በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን መከሩና ወሰኑ፡፡ በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ አለ፡፡ በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር፡፡ ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን መንገድ ዘግተው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅጣጫ መንገድ ከፈቱለት ከቀናት በኋላ ከባድ ዝናብ በዚህች ቀን ጣለ፡፡
ወንዙ ትልቅ ነውና ያገኘውን ሁሉ እያገላበጠ ደረሰ፡፡ በወቅቱ በቅዱሱ መልአክ ቤተ መቅደስ ውስጥ ከመጋቢው በስተቀር ሰው አልነበረምና አስፈሪ ድምጽ ሰምቶ ሲወጣ ወንዙ እየደነፋ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየመጣ ነው፡፡ ከደቂቃዎች በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳልነበረ እንደሚሆን የተረዳው መጋቢ በታላቅ ድንግጤ ውስጥ ወደቀ፡፡ እርሱ አንድ ተስፋ ነበረውና ወደ ውስጥ ገብቶ በመላዕክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ምስለ ስዕል ፊት ወድቆ ተማጸነ፡፡ ታላቁ ወንዝ ቤተ ክርስቲያኑን ጠርጎ የሚወወስደው ከሆነም የሚሆነውን ነገር ለመቀበልና ከዚያም ላለመውጣትም ወሰነ፡፡ ትንሽ ቆይቶ በታላቅ ኃይል ወንዙ ደረሰ፡፡ በዚህ ጊዜ የመላዕክት ሁሉ አለቃቸው ለጠራውም ፈጥኖ የሚደርሰው ቅዱስ ሚካኤል በግርማ ከሰማይ ወርዶ በወንዙ ፊት ቆመ፡፡

መጋቢውንም "ጽና አትፍራ፣ እኔ ካንተ ጋር ነኝና" ብሎት በያዘው የብርሃን በትረ-መስቀል መሬትን አንድ ጊዜ መታት፡፡ በዚያች ቅጽበትም ትልቅ ሸለቆ ተፈጠረ፡፡ በአስፈሪ ሁኔታ ሲመጣ የነበረው ወንዝም በሸለቆው ውስጥ አልፎ ሔደ፡፡ የሚገርመው ነገር የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሸለቆው የተፈጠረው ከቤተ ክርስቲያኑ በታች መሆኑ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ ግን ጸንቶ ቆመ፡፡ መጋቢውም እግዚአብሔርንና ቅዱስ ሚካኤልን አመሰገነ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል መጋቢውን ባርኮት በክብር ዐረገ፡፡ በማግስቱ ክርስቲያኖቹ ይህንን አይተው ደስ አላቸው፣ መልአኩንም አከበሩት፣ አሕዛብ ግን አፈሩ፡፡

ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያስገዙ ገዳማውያንና ቅዱሳን ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




የ2026 የ"ማክአርተር ፈሎውሺፕ" በማሸነፍ ደራሲ መዓዛ መንግሥቴ የ 131ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ሆነች
 
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዝና እና እውቅና ባገኘው የ2026 የ‘ማክአርተር ፈሎውሺፕ’ (MacArthur Fellowship) ሽልማት ከተመረጡ...

20 የጥበብ፣ የልቦለድ፣ የምሁራን እና የሳይንስ ባለሙያዎች መካከል ታዋቂዋ ኢትዮ-አሜሪካዊት ደራሲ መዓዛ መንግሥቴ አንዷ በመሆን የ800 ሺህ ዶላር የገንዘብ ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።
 
ይህ ታላቅ ሽልማት በየዓመቱ ልዩ የፈጠራ ችሎታ ለሚያሳዩ፣ ለሕብረተሰብ አስተዋጽኦ ላበረከቱ እና ለወደፊት ትልቅ እቅም ላላቸው ተመረጡ ግለሰቦች የሚሰጥ ሲሆን....

ደራሲ መዓዛ መንግሥቴ የታሪክን ሕመም፣ የሰብዓዊነትን ጥልቀት እና የፖለቲካ ግጭቶች በሰው ልጅ ላይ የሚያደርሱትን ሞራላዊ ጠባሳ በብዕሯ በጥበብ በመቅረጿ ለዚህ ከፍተኛ ክብር በቅታለች።
 
የማክአርተር ፋውንዴሽን (MacArthur Foundation) እንደገለጸው፣ መዓዛ መንግሥቴ ለሽልማት የበቃችው የታሪክን፣ የትውስታንና የተስፋን ጥምረት በመጠቀም የፖለቲካ ጥቃቶች በሰዎች ሕይወት ላይ የሚያሳድሩትን ከባድ ዋጋ በጽሑፎቿ በጥልቀት በማሳየቷ ነው።
 
ደራሲ መዓዛ መንግሥቴ በዓለም አቀፍ የሥነ-ጽሑፍ መድረክ ስሟ በጉልህ እንዲነሳ ካደረጉ አበይት ሥራዎቿ መካከል፦‘የጣሊያን ወረራ ወቅት የነበሩትን ሴት አርበኞች ታሪክ የሚያወሳውና ለታዋቂው የቡከር ሽልማት (Booker Prize) እጩ የነበረው "The Shadow King" እና የደርግን ሥርዓት መጀመሪያ የሚያሳየው "Beneath the Lion's Gaze" የተባሉት ልብወለድ መጽሐፎቿ ይጠቀሳሉ።
 
ከእነዚህ ጥራዝ መጻሕፍት በተጨማሪ በርካታ አጫጭር ታሪኮችን፣ ድርሰቶችን እና ምርምራዊ መጣጥፎችን ለዓለም አንባቢዎች በማቅረብ ትታወቃለች።
 
ደራሲ መዓዛ መንግሥቴ  ታሪክን፣ ትዝታን እና የፈጠራ ጥበብን በማዋሃድ ታላቅ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ታሪኮቻችንን ለዓለም በስራዋ አስተዋውቃለች፡፡
 
በአሁኑ ወቅት በኮነቲከት በሚገኘው ዌስሊያን ዩኒቨርሲቲ (Wesleyan University) የእንግሊዝኛ ፕሮፌሰር ሆና በማስተማር ላይ ትገኛለች።
 
    Via፦ Ethio fm 107.8
            ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda

 




በአዲስ አበባ እንኳን ቦንብ ረችትም አልፈነዳም ማስቲካም አልፈነዳም!" -ጋዜጠኛ እንዳልካቸው ዘነበ

የቀድሞው የArts TV ጋዜጠኛ እንዳልካቸው ዘነበ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ከዲያስፖራዎች ጋር ባደረገው ውይይት በአገር ውስጥ ስላለው እውነታ የሚተላለፉ መረጃዎችን በተመለከተ ጠንከር ያለ ሀሳብ ማንሳቱን ግዮን ማለዳ ተመልክቷል ።

"በአዲስ አበባ እንኳን ቦንብ፤ ረችት አልፈነዳም፤ ማስቲካ አልፈነዳም" በማለት በከተማዋ ያለውን ዕለታዊ ሁኔታ ከሩቅ ሆነው በሚገልጹ ወይም በሚተርኩ መረጃዎች ላይ ጥያቄ አንስቷል።

ጋዜጠኛ እንዳልካቸው ዘነበ፣ "ከባህር ማዶ ሆናችሁ ስላለንበት ከተማ አትንገሩን" በማለትም በአዲስ አበባ በየዕለቱ የሚኖሩ ሰዎች የሚያዩትንና የሚያጋጥማቸውን እውነታ በቀጥታ እንደሚያውቁ ገልጿል።


ሰላም ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda


የአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ረድኤት እና ምልጃ አይለየን🙏

በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡

አባታቸው ጸጋ ዘአብና እናታቸው እግዚእ ኃረያ ፍሥሐ ጽዮን ብለው ሰየሟቸው፡፡ በአንድ ወቅት ታዳጊው ፍሥሐ ጽዮን ወደ ጫካ ለአደን በሔዱበት ጌታችን ተገልጦ ጸጋ መንፈስ ቅዱን አሳደረባቸው፡፡ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ለስብከተ ወንጌል እንደሚልካቸውም አስረዳቸው፡፡ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው መዓርገ ዲቊናን፣ በ22 ዓመታቸው ደግሞ መዓርገ ቅስናን ከግብጻዊው ጳጳስ አባ ቄርሎስ ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ስማቸውም ተክለ ሃይማኖት እንደሚባል፣ ትርጓሜውም ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት እንደሆነ አበሠራቸው፡፡

ወላጆቻቸው ካረፉ በኋላም ንብረታቸውን ሁሉ ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ሰጥተው ቤታቸውን ትተው ወንጌልን ለማስተማር ወጡ፡፡ በደብረ ዳሞ ገዳም ለ12 ዓመታት ተቀምጠው ሲወርዱ ገመዱ ቢበጠስ ስድስት ክንፍ አውጥተው በረዋል፡፡ በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ በርካታ አሕዛብን አጥምቀዋል፤ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳንጸዋል፡፡ በደብረ ሊባኖስ ገዳም አስቦ ዋሻ በዙሪያቸው ስምንት ጦሮች ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት በማሰብ ሌሊትና ቀን ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ፤ ከመቆም ብዛት አንድ እግራቸው ተሰብራል፡፡

ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ በኋላም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ለሰው ዘር ሁሉ ድኅነትን ለምነዋል፡፡ ከዚህ ዓለም ድካም በሚያርፉበት ነሐሴ 24 ቀንም ጌታችን ከእናቱ ከቅዱሳን መላእክት፣ ከወዳጆቹ ጋር መጥቶ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡

የጻድቁን ቃል ኪዳን ያመኑ ገዳማውያን እንደሳቸው ሁሉ ዓለምን ንቀው በተጋድሎ ይኖራሉና ከበረከታቸው እንድንሳተፍ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
 




በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ40-50 አመት የሚጫወቱ ተጫዋቾች ይበዛሉ። ጋዜጠኛ ኤርሚያስ በላይነህ

ጋዜጠኛ ኤርሚያስ በላይነህ በቆየው ከአንድ ሰዓት በላይ ባለው ቃለ-መጠይቅ በኢትዮጵያ እግርኳስ ውስጥ ስለተስፋፋው የእድሜ ማጭበርበር ከባድ ስጋቱን ገልጿል።

ኤርሚያስ በተለይ ዋናው ጉዳይ አንድ ተጫዋች ስንት ዓመት እንዳለው ብቻ ሳይሆን፣ በሀገሪቱ እግርኳስ ውስጥ የእድሜ ማጭበርበር በስፋት መኖሩ እና ይህም ወጣት ተጫዋቾችን እድል እያሳጣ መሆኑ እንደሆነ ማስገንዘቡን ግዮን ማለዳ ተመልክቷል ።

በቃለ-መጠይቁ ወቅት የአንድን ተጫዋች እድሜ በተመለከተ ቁጥር በስህተት እንደጠቀሰ የገለጸው ኤርሚያስ፣ ለዚህም ይቅርታ ጠይቋል። ነገር ግን ይህ አንድ ስህተት የእርሱን ዋና መልዕክት ሊያሸፍነው እንደማይገባ ተናግሯል።

እንደ ኤርሚያስ ገለጻ፣ በአሁኑ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ከ35 እስከ 45 ዓመት የሚገመት እድሜ ያላቸው ተጫዋቾች ቁጥር እጅግ አሳሳቢ ነው። በሊጉም ከ40 እስከ 50 ዓመት የሚደርሱ ተጫዋቾች እየተጫወቱ መሆኑን ጠቁሟል።

“ታዳጊና ወጣት ላይ እንስራ” ከማለት በፊት፣ በእድሜ ላይ የሚፈጸመውን ማጭበርበር ማስቆም እንደሚገባ ኤርሚያስ አስገንዝቧል። እንዲህ ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ወጣት ተጫዋቾች በትክክለኛው የእድሜ ወቅታቸው ቦታ እንዳያገኙ እና የሊጉ የተጫዋቾች ትውልድ መተካካት (turnover) እንዲዛባ እንደሚያደርግ ገልጿል።

ኤርሚያስ በተጨማሪም የእድሜ ማጭበርበር ችግር አሁን እንደ 4 ወይም 5 ዓመት የእድሜ ልዩነት ብቻ ሳይሆን፣ 10 እና 15 ዓመት ድረስ የሚደርስ ችግር መሆኑን በአጽንኦት ተናግሯል።

“የልጆቹ እድል እንዲጠፋ አይደለም ፍላጎቴ፤ ችግሩ እንዲፈታና እግርኳሳችን ከዚህ ከባድ ችግር እንዲላቀቅ ነው” በማለት ዓላማውን አስረድቷል።

እንደ ኤርሚያስ ገለጻ፣ የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ችግሩን ለመፍታት የሚያደርገውን ሥራ ከጀመረ እርሱ ያለውን መረጃ ለማቅረብ ሙሉ ዝግጁ ነው። ሆኖም ለግለሰቦች ብቻ የሚያቀርበው ማስረጃ እንደሌለው ገልጿል።

በመጨረሻም ኤርሚያስ ተከታዮቹ አንድ የተቆራረጠ ቪዲዮ ወይም አንድ ርዕስ ብቻ ሳይመለከቱ ሙሉውን ፕሮግራም አይተው አስተያየት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

“እድሜ ማጭበርበር የእግርኳስ ነቀርሳ ነው!” በማለትም የችግሩን አሳሳቢነት አጽንኦት ሰጥቶ ገልጿል።

እናንተስ የጋዜጠኛውን ሀሳብ እንዴት አያችሁት ? ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን እስኪ ?

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda




የቅዱስ ገብርኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን፤ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን🙏

“እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” 🙏

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በሉቃስ 1÷19 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” ብሎ መገኛ ስፍራውንና እግዚአብሔር የሰጠውን ክብር በይፋ ያወጀ መልአክ ነው፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ድንቅ መልእክቶችን በማድረስና የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡ ነገደ መላክት በሰማይ አምላካቸው ተሰውሮባቸው ማን ፈጠረን ብለው በተጨነቁ ጊዜ ያረጋጋቸው እርሱ ነው፡፡ በክብሩ ከፍ ብሎ በመፈጠሩ መላዕክትን እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ ብሎ ሊያስት የሞከረውን የሀሰት አባት የያኔው (ሳጥናኤል) ጠላት ዲያብሎስ ተከራክሮ የረታው እርሱ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

መላእክት የሰው ልጆች አፍቃሪና ወዳጅ ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ የአምላክና የሰው ልጆች ወዳጅ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ይህንም ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእሳት ሲያድን አይተነዋል፡፡ ዳግመኛም የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናቡከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱንና ሕዝቡን እንዲያስተዳድር ቢፈቅድለት በትዕቢት ተሞላ፡፡ በዳንኤል 3፥1 እንደተጻፈው “ሁሉን በኃይሌ አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም፤ የሚቃወመኝም የለም” በሚል ትዕቢት ቁመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ስድስት ክንድ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ አቁሞ ያልሰገደለት እንዲገደል አዋጅ አስነገረ፡፡

አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል የተባሉ ሦስት ሕጻናት በንጉሡ ፊት ቆመው “ንጉሥ ሆይ እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፡፡ ከሚነድደው ከእቶኑ እሳት ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድ ዕወቅ” ባሉ ጊዜ ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ ደርሶ ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ናቡከደነጾርም ተገርሞ እነሆ ሰሦስት ሰዎ በእሳቱ ላይ ጥለን ነበር እኔ ግን አራት ሰዎች አያለሁ፣ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን መልክ ይመስላል አለ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የአምላክ ባለሟል ነው፡፡ ለካሕኑ ለቅዱስ ዘካርያስ እንደነገረው በእግዚአብሔር ፊት መቆሙ ታላቅ ባለሟል መሆኑን የሚያሳይ ነውና፡፡

ገዳማውያን እናቶችና አባቶቻችን ሊቀ መላአኩ በእግዚአብሔር ፊት በቆመ ጊዜ እንዲያማልዳቸው በዘወትር በጸሎታቸው ተግተው ይጠሩታል፡፡ ከበረከታቸው እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡  

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ 

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
24 ዓመታት ትውልድን በእውነትና በእውቀት ሲቀርጹና ሀገር ሲያሳድጉ የነበሩት መምህር ዘመናይ በአዲስአበባ ፒያሳ ጎዳናዎች ላይ መኖር ከጀመሩ ከአመታት በኋላ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገናኙ ።

ለሩብ ክፍለ ዘመን ያህል (24 ዓመታት) ትውልድን በእውነትና በእውቀት ሲቀርጹና ሀገር ሲያሳድጉ የነበሩት መምህር ዘመናይ መሸሻ፣ በሕይወት አጋጣሚዎች ከላይ በቪዲዮ እንደምታዩት ምክንያት በአዲስአበባ ፒያሳ ላይ ጎዳና ተዳዳሪ ለመሆን ተገደው እንደነበር የሚያውቃቸው ይናገራሉ ።

መምህር ዘመናይ በቀደመው ሕይወታቸው ከሚኖሩበት አካባቢ በደረሰባቸው መገፋፋትና ምቀኝነት ምክንያት ተሰደደው ወደ ሚዛን በማቅናት በመምህርነት ተቀጥረው ይሠሩ እንደነበር ግዮን ማለዳ ተመልክቷል ።

በኋላም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የሚወዱትን የመምህርነት ሙያ ለመቀጠል በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ቢጠይቁም፣ በተለያዩ የቢሮክራሲ ማነቆዎች ምክንያት ምላሽ ሳያገኙ ቀርተዋል።

በሂደቱም የተሻለ ሥራ አገኛለሁ በማለት በተስፋ ሲጠበቁ ቢቆዩም ነገሮች ሳይሳኩ ቀርተው፣ በቀናት ሂደት ውስጥ ሕይወታቸውን በጎዳና ላይ ለመግፋት ተገደዋል።

ይሁን እንጂ በቅርቡ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችና በዙሪያቸው ያሉ በጎ አድራጊዎች ታሪካቸውንና ያለፉበትን ፈተና ለሕዝብ ይፋ አድርገዋል።

ይህንኑ ታሪክ ሰምተው ሁኔታቸውን ያወቁት ቤተሰቦቻቸውና ልጃቸው፣ መምህር ዘመናይ ያሉበት ድረስ በመምጣት በስሜትና በእንባ በተሞላ ሁኔታ ከዓመታት መለያየት በኋላ ተገናኝተዋቸዋል።

ይህ አጋጣሚ የብዙዎችን ልብ የነካና ለማህበረሰቡ ትልቅ አስተምህሮ ያሳደረ አጋጣሚ ሆኖ አልፏል።

       ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda


በመቐለ ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሚ ጀመረ

ላለፉት 10 ቀናት በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሚ መጀመሩን የከተማይቱ አራት ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።

አገልግሎቱ ወደ ነበረበት የተመለሰው ዛሬ እሁድ መስከረም 24፤ 2019 ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ተኩል ገደማ እንደሆኑ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

አሜሪካ በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር አካባቢ እየጨመረ ያለው ውጥረት ያሳሰባት መሆኑን ገልጻ፣ ሁለቱ ሀገራት ፍጹም ትዕግስት እንዲያደርጉና ወደ ውይይት እንዲመለሱ አሳሰበች።

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ቶሚ ፒጎት ባወጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ቀንድ ተጨማሪ ወታደራዊ ግጭትና ሰብአዊ ቀውስ ሊሸከም እንደማይችል ጠቁመዋል።

አሜሪካ ሁለቱም ሀገራት የጎረቤቶቻቸውን የሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲያከብሩ፣ እንዲሁም በ እ.ኤ.አ. 2018 የሰላም ማዕቀፍ ስምምነታቸው መሰረት ችግሮችን በውይይትና በሁለትዮሽ ትብብር እንዲፈቱ ጥሪ አቅርባለች።

Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda


የሌላ ወንድ ልጅ አርግዛ ሳለች የቀድሞ ባሏ በወሊድ ክፍል ገብቶ ልጁን ተቀበለላት፤ ዛሬ ደግሞ የቀድሞ ባሏ፣ የአሁኑ ባሏ እና ልጆቿ በአንድ ላይ እንደ አንድ ቤተሰብ በፍቅር ይኖራሉ!

በባህላችንና በማህበረሰባችን ፈጽሞ የማይታሰብ፣ ብዙዎችን ያስደነገጠና ያስደመመ እውነተኛ የስደት ታሪክ!

በብዙዎቻችን ማህበረሰብ ውስጥ ፍቺ ማለት ቂም፣ በቀል፣ ፍርድ ቤት መመላለስ እና አንዳንዴም ደም መፋሰስ ነው። ይህች ኢትዮጵያዊት እናት ግን በስዊዘርላንድ ምድር የኖረችው ታሪክ ሁሉንም ማህበራዊ ህግጋት የሰበረ እና የሰው ልጅ ደግነት ምን ያህል ጥግ ሊደርስ እንደሚችል ያሳየ ነው።

ታሪኩ የሚጀምረው ከ26 ዓመታት በፊት ነው። ወደ ስዊዘርላንድ ተሰዳ በስደተኞች ካምፕ ውስጥ በሳምንት በ77 ፍራንክ በችግር ስትኖር፣ የመኖሪያ ፍቃድ ለማግኘትና ከአገር ላለመባረር ቶማስ የተባለውን ደግ ስዊዛዊ ታገባለች።

ነገር ግን ከጋብቻው ማግስት ያልታሰበ ከባድ የመንፈስ እና የስነ-ልቦና ህመም ውስጥ ወደቀች። በፍርሃትና በጭንቀት ተውጣ እንደ ሚስት መሆን፣ አብሮ መተኛትም ሆነ ትዳር መምራት ፈጽሞ አቃታት።

በባህላችን አንድ ወንድ ሚስቱ እንደ ሚስት መሆን ካቃታት የሚያደርገው ግልጽ ነው። ቶማስ ግን ያላሰቡትን ታሪክ ጻፈ።

"አንቺ በሁለት እግርሽ ቆመሽ ሙሉ ጤነኛ እስክትሆኚ ድረስ የትም አልጥልሽም፤ ከዚህ በኋላ እንደ ባል ሳይሆን እንደ አባትሽ ሆኜ አስታምምሻለሁ" አላት። ቃሉንም በተግባር አሳየ። ራስን እስከማጥፋት ያደረሳትን ስቃይ ሁሉ እንደ አባት ታግሶ አስታመማት። በዚያ ወቅት ነበር "ባሌ አባቴ ሆነ... ቀረና ትዳሩ" የሚለውን ዝነኛ ዘፈኗን ለእሱ የጻፈችለት።

ነገሩ ግን በዚህ ብቻ አላበቃም! በጣም አነጋጋሪው ክፍል የሚጀምረው እዚህ ጋር ነው።
ከጊዜ በኋላ በስምምነት ተለያዩ። እሷም ወደ ኢትዮጵያ መጥታ ከሌላ ሰው ጋር ተዋውቃ አረገዘች።

የፍቺያቸው ጉዳይ ፍርድ ቤት ባለቀበት ቀን የአምስት ወር ነፍሰጡር ነበረች! ይህ ስዊዛዊ የቀድሞ ባሏ ግን ጀርባውን ከመስጠት ይልቅ፦ "የኢትዮጵያን የህክምና ሁኔታ አይቻለሁ፤ የሌላም ሰው ልጅ ቢሆን እዚህ በሰላም በኔ ኢንሹራንስ ሆስፒታል መውለድ አለብሽ" ብሎ ወደ ስዊዘርላንድ አስመጣት።

በወሊድ ሰዓት አብሯት ወደ መውለጃው ክፍል ገባ፤ ልጇን ተቀብሎ አቀፈ፤ የክርስትና አባት ሆኖ በሙሉ ፍቅር አሳደጋት።

ይህም አልበቃ ብሎ፣ ከዓመታት በኋላ እሷ ሌላ አዲስ ባል አግብታ ሁለተኛ ልጅ ስትወልድ፣ አዲሱን ባሏንና ልጆቿን ይዛ ስዊዘርላንድ ስትመጣ የተቀበላቸው ይኸው የቀድሞ ባሏ ቶማስ ነበር! ለሁለት ወራት ያህል በአንድ ቤት ውስጥ አብረው ኖሩ።

ዛሬም ድረስ አዲሱ ባሏ ሄዶ የቶማስን ግቢና አትክልት ያስተካክላል፤ ቶማስ ደግሞ ለልጆቹ ልብስ እየገዛ፣ ዋና እያስተማረ እንደ አያትና እንደ አባት ሆኖ ይንከባከባቸዋል። በማህበረሰባችን ውስጥ ለግድያ የሚፈላለጉ የቀድሞና የአሁን ባሎች፣ እዚህ ጋር እንደ ወንድማማች ተቃቅፈው ይኖራሉ!

ነገር ግን የዚህች እናት ታሪክ ትልቁ እና መራራው አነጋጋሪ ርዕስ ይሄ ብቻ አይደለም፤ የገዛ ቤተሰቦቿ የፈጸሙባት ክህደት እንጂ!

ለቤተሰቦቿ የመጀመሪያ የስደት በር ከፋች ሆና፣ ከኮንቴነር ልብስ እየለበሰች፣ ራሷን ረስታ ገንዘብ ስትልክ ኖራለች። እህትና ወንድሞቿን አውሮፓ ድረስ እንዲመጡ መንገድ ከፍታለች። ነገር ግን እሷ ታማ፣ አእምሮዋ ተጨንቆ፣ ስራ መስራት አቅቷት እጇ ባጠረ ጊዜ የገዛ ደሟ የሆኑት ቤተሰቦቿ ጀርባቸውን ሰጧት።

"ቤተሰብ ለፎቶ የሚሆን መልክ ስታጣ አብሮህ መቆም አይፈልግም! የስደተኛ ዘመዱ ገንዘቡ ብቻ ነው!" ስትል በቁጭት ትናገራለች። "ችለህ ያላደረግከውን ሳይሆን፣ ሳትችል የቀረኸውን ብቻ ይዘው ያኮርፉሃል፤ ያገልሉሃል፤ ስምህን ያጠፋሉ።"
ለዚህም ነው በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የዲያስፖራ ወገኖች እጅግ አከራካሪና ድፍረት የተሞላበትን ይህንን ምክር የሰጠችው

"75% ለራስህ ኑር፤ ለቤተሰብህ የምትሰጠው 25% ብቻ ይሁን! ለቤተሰብ እረዳለሁ ብለህ ሳታገባ፣ ሳትወልድና ራስህን ሳትሰራ እድሜህን አትጨርስ። ካልሰጠህ አትሰደብም፤ ትንሽ ስትሰጥ ግን እንደተከበርክ ትኖራለህ። የስደተኛ ዘመዱ ጤናውና ኪሱ ያለው ገንዘብ ብቻ ነው!"

የባዳው ፈረንጅ እንደ አባት ሆኖ ሲታደጋት፣ የገዛ ቤተሰቧ ግን የገንዘብ ምንጭነቷ ሲያበቃ ፊታቸውን አዙረውባታል። ከብዙ አመታት የስቃይ መንገድና የጸበል ፈውስ በኋላ፣ ዛሬ ላይ ፈጣሪዋን በዝማሬ እያመሰገነች ከባለቤቷ፣ ከልጆቿ እና ካልተለያት መልካም ሰው ከቶማስ ጋር በሰላም ትኖራለች።

ደም ሁልጊዜ ዘመድ አይሆንም፤ አንዳንዴ እውነተኛው ቤተሰብ በፈጣሪ ልብ ውስጥ የተመረጠ ባዳ ነው!

Via፦ አሀዱ ሚዲያ
ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda




እንኳን ለአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ወርሃዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏

ታኅሣሥ 24 ቀን 1212 ዓ.ም ከካህኑ አባታቸው ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኃረያ በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድና በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ብሥራት ተወለዱ፡፡ 

ወላጆቻቸውም ፍሥሐ ጽዮን ብለው ሰየሟቸው፡፡ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው መዓርገ ዲቊናን፣ በ22 ዓመታቸው ደግሞ መዓርገ ቅስናን ከግብጻዊው ጳጳስ አባ ቄርሎስ ተቀብለዋል፡፡ በአንድ ወቅት ሕፃኑ ፍሥሐ ጽዮን ወደ ጫካ ለአደን በሔዱበት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ ጸጋ መንፈስ ቅዱን አሳደረባቸው፡፡ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወንጌል ወዳልተዳረሰበት ቦታ እንደሚልካቸውም አስረዳቸው፡፡ 

ቅዱስ ሚካኤልም ከአዳኝነት ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመመለስ እንደተመረጡ፣ ስማቸውም ተክለ ሃይማኖት እንደሚባል፣ ትርጓሜውም ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት እንደሆነ አበሠራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ያላቸውን ንብረት ዅሉ ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ሰጥተው “አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደ ተከፈተ ተውኹልህ” በማለት ቤታቸውን ትተው ወንጌልን ለማስተማር ፈጥነው ወጡ፡፡ በደብረ ዳሞ ገዳምም ለ12 ዓመታት ተቀምጠው ከዚያ ሲወርዱ ገመዱ ገመዱ ሲበጠስ ስድስት ክንፍ አውጥተው በረዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምረው በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ በርካታ አሕዛብን ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፤ ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳንጸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ በደብረ ሊባኖስ ገዳመ አስቦ ዋሻ በመግባትም በዙሪያቸው ስምንት ጦሮችን ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማም፣ ሞትና ነገረ መስቀል በማሰብ በተመስጦ ለ22 ሌሊትና ቀን ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት ተወስነው ሲጋደሉ፤ ከመቆም ብዛት የአንድ እግራቸው አገዳ ተሰብራል፡፡ ደቀ መዛሙርቱም የመንፈሳዊ አባታቸውን የዐፅም ስባሪ አክብረው አኑረውታል፡፡ እግራቸው ከተሰበረ በኋላም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ሌሊትና ቀን ጸንተው ለሰው ዘር ሁሉ ድኅነትን ሲለምኑ ጥቂት ውኃ እንኳ የቀመሱት በአራተኛው ዓመት ብቻ እንደ ነበረ መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል፡፡ ጻድቁ አባታችን ምድራዊ ሕይወታቸውን በተጋድሎና በሐዋርያዊ አገልግሎት ከፈጸሙ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም የሚያርፉበት ቀን ሲቃረበ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅዱሳን መላእክት፣ ከወዳጆቹ ጋር መጣ፡፡

በስማቸው መታሰቢያ ለሚያደርጉ፣ ለነዳያን ለሚመጸዉቱ ቤተ ክርስቲያን ለሚያሠሩ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው፣ ስለ ተጋድሏቸው ጽናትም “በሰው እጅ የማይለካውን ይህንን የመንግሥት አዳራሽ ውሰድ” በማለት የጸጋ ልብስ አልብሷቸው፤ በመስቀል ምልክት ያጌጡ ሰባት የሕይወት አክሊላትንም አቀዳጅቷቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም የመንፈስ ልጆቻቸውን ጠርተው ጌታችን የነገራቸውን ዅሉ አስረድተው አባታዊ ምክርና ተግሣፅ ከሰጧቸው በኋላ ነሐሴ 24 ቀን በዘጠና ዘጠኝ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል፡፡ የመንፈስ ልጆቻቸውም በማኅሌት፣ በዝማሬና በምስጋና ቀብረዋቸዋል፡፡ጌታችንም ነፍሳቸውንም በክብር ተቀብሏታል፡፡ የጻድቁን ቃል ኪዳን ያመኑ ገዳማውያን እንደሳቸው ዓለምን ንቀው በተጋድሎ ይኖራሉ፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
 
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
 



Показано 20 последних публикаций.