“ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።”
— ማቴዎስ 2፥1-2
እንኳን ለንጉሡ ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በሠላም አደረሳችሁ !!
የንጉሣችን መወለድ ለምን ስንል:-
እንድህ ባለ መልኩ ይገልጠዋል :-
"ጊዜን ሁሉ የፈጠረበት የአብ ቃል ሥጋ ሆነ፤ በጊዜም ውስጥ ለእኛ ተወለደልን። የየትኛውም ቀን ክንውን ያለ እርሱ መለኮታዊ ፈቃድ የማይጠናቀቅ ሆኖ ሳለ፣ ሰው ሆኖ የሚወለድበት ቀን እንዲለይ ፈለገ። የዓመታት ዑደት ሳይፈጠሩ በፊት እርሱ በአባቱ ዕቅፍ ነበር፤ ከምድራዊም እናት በመወለድ በዓመታት ሂደት መካከል በዚህ ቀን ተገለጠ።
ከእናቱ ጡት ይጠባ ዘንድ፣ የከዋክብት ገዢ የሆነው የሰው ፈጣሪ ሰው ሆነ።
እንጀራ የሆነው፣ ይራብ ዘንድ
ምንጭ የሆነው፣ ይጠማ ዘንድ
ብርሃን የሆነው፣ ያንቀላፋ ዘንድ
መንገድ የሆነው፣ በጉዞ ይዝል ዘንድ
እውነት የሆነው፣ በሐሰት ይከሰስ ዘንድ
በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈርደው፣ በመዋቲ ዳኛ ፊት ለችሎት ይቀርብ ዘንድ
ፍትሕ የሆነው፣ በኢፍትሐውያን ይኮነን ዘንድ
[በጽድቅ] የሚገሥጸው፣ በጅራፍ ይገረፍ ዘንድ
የሁሉ ነገር መሠረት የሆነው፣ በመስቀል ላይ ይንጠለጠል ዘንድ
ብርቱው የሆነው፣ ደካማ ይሆን ዘንድ
ፈዋሹ፣ ይቈስል ዘንድ
ሕያው የሆነው፣ ይሞት ዘንድ - ሰው ሆነ
ከንቱ የሆነውን እኛን ፍጥረቱን ነጻ ሊያወጣ፣ ውርደትን በጽኑ ታገሠ። ከዘመናት በፊት፣ ያለጅማሬ ለዘላለም የእግዚአብሔር ሕያው ልጅ ሆኖ የኖረው፣ የሰው ልጅ ለመሆን በዘመናት መካከል ራሱን ዝቅ አደረገ። ይህን ሁሉ ያደረገውና ለታታላቅ ክፋቶች ራሱን ያስገዛው ስለ እኛ ሲል እንጂ ፈጽሞውኑ ክፋት አድርጐ አይደለም፤ የተትረፈረፈ መልካምነትን ከእጁ የተቀበልነው እኛም፣ ቸርነቱን ለመቀበል የሚያስችል ምንም በጐነት የለንም።"
ንጉሡ የአብ ስጦታ ነው ...ስጦታው ግን የተቅበዝባዡ ዓለም ቤዛ ነው !!
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!!
❤My beloved Chanel's Family 🥰🥰🥰
@gitim_alem @gitim_alem
— ማቴዎስ 2፥1-2
እንኳን ለንጉሡ ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በሠላም አደረሳችሁ !!
የንጉሣችን መወለድ ለምን ስንል:-
ቅዱስ አውግስጢኖስ