✍
አነጋገርህ ከተበላሸ: የያዝከው እውነታ ያደበዝዘዋል!!
ንጉሱ ህልም ያይና ወደ አስፈቺ ይሄዳል።
መጀመሪያ ላገኘው ህልም ፈቺ………
"እንቅልፌ በተኛሁ ጊዜ እንዲህ ዐይነት ህልም አየሁኝ: ሁሉም ጥርሶቼ ረግፈው ወደቁ: ደንግጬ ስነቃ ግን ምንም የሆንኩት ነገር የለም"
ህልም ፈቺው፦
"ሁሉም ቤተሰቦችህ እያየኻቸው ሊሞቱ ነው።" አለው።
ንጉሱ በጣም ተናዶ ለወታደሮቹ "ይህ ሟርተኛ በፍጥነት ወደ እስር ቤቱ አስገቡልኝ" አላቸው።
ወደ ሌላ ህልም ፈቺ ሄደ………
"ማታ ማታ ስተኛ ሁሉም ጥርሶቼ ከድዴ ረግፈው እየወደቁ ይታየኛል። ፍቺው ምንድን ነው?" አለው
ህልም ፈቺው…………
"ሁሉም ቤተሰቦችህ ዐይንህ እያየ ሊሞቱብህ ነው" አለው።
ንጉሱ "ይህንንም ከቅድሙ ጋ ቀላቅሉልኝ" አላቸው።
ንጉሱ ህልሙ በጥሩ እንዲፈታለት ስለፈለገ አሁንም ወደ ሌላ ህልም ፈቺ ሄደ……
"በህልሜ ሁሉም ጥርሶቼ እየረገፉ ይታየኛል: ፍቺው ምንድን ነው?" አለ
ህልም ፈቺው…………
"ማሻ አላህ!! ትልቅ የሆነ ብስራት ላበስርህ ነው" አለው።
ንጉሱ በጣም ጓጉቶ እና ተደስቶ………
"በምንድን ነው የምታበስረኝ?" አለው።
ህልም ፈቺው…………
"ከሁሉም ቤተሰቦችህ ረዥም እድሜ የሚኖረው አንተ ነህ!!" አለው።
ንጉሱ በጣም ደስስስ ብሎት ለዚህ ህልም ፈቺ ውድ የሆነ ስጦታ ሰጥቶ ህዝቡ ዘንድ ዕውቅና እንዲያገኝ አደረገው።
የሦሥቱም ህልም ፈቺዎች ንግግር ተመሳሳይ ትርጉም ያለው ነው; አነጋገራቸው እና የቃላት አመራረጣቸው የፈጠረው ልዩነት እና ተቀባይነት ግን እጅግ በጣም የተራራቀ ነበር።
ወዳጄ!!
ንግግርህ, እምነትህ, መንሓጅህ ትክክል ሊሆን ይችላል፤ ምላስህ ላይ መርዛማነት ካለ ግን እውነት እያወራህ እንኳ ሰዎች ይሸሹሃል: አጋዥም ይሁን አጋር ታጣለህ።
https://t.me/hamdquante