✍
ነብዩﷺ አላህ መልእክተኛ አድርጎ የላካቸው ትልቁ ዐላማ ሽርክን ገርስሶ ተውሒድ ለማስፈን ነው። እንደሚታወቀው ብዙኃን ሙሽሪኮች አላህ ላይ የሚያጋሯቸው ነብያቶች እና በሆነ ዘመን የነበሩ ደጋግ ሰዎችን ነው። ስለሆነም ነብዩ
ﷺ ነብያቶችን ለአላህ አጋር አድርጎ ከመያዝ አጥብቀው ያወግዛሉ።
ሌሎች ነብያቶች እንዳይመለኩ ከሚያወግዙት በበለጠ ራሳቸው እንዳይመለኩ አስጠንቅቀው ያስተምራሉ። ቀብራቸው እንዳይመለክ ጌታቸውን ይማፀናሉ። ከፊል ሰዎች ቀላል የሚመስላቸው ነገር ላይ ራሱ
"አላህ እና አንተ ከፈለክ" ሲባሉ በቁጣ
«ለአላህ ቢጤ እያደረከኝ ነው??» ብለው ያወግዛሉ። ይህ የሲራጠል ሙስተቂም መንገድ ነው!!
እናም ወዳጄ………
አንድ ሸይኽ ወይም አንድ ኡስታዝ ሰዎችን በጭፍን ከመከተል እያወገዘ የሚያስተምር ከሆነ: ራሱ በሚያስተምረው ትምህርት መሰረት እሱንም ቢሆን ተማሪዎቹ በጭፍን መከተል እንደሌለባቸው እሱና አድማጮቹ ሊገነዘቡ ይገባቸዋል።
የኢስላም ፈርጥ የሆኑ ቀደምት ዑለማዎች ከመሃላቸው አንዱን ነጥሎ ተቅሊድ ማድረግ የማይቻል ነገር ሆኖ: የአንተን ሸይኽ መከተል ግን የምታግራራ ከሆነ ገና መታጠብ ያለበት ነገር ለመኖሩ ማሳያ ነው።
https://t.me/hamdquante