ስለ ሶማሊላንድ።
ከቅርብ ጊዜያት እየተካሄዱ ካሉ ክስተቶች አንጻር እና ከአንዳንዶቻችሁ ጥያቄም አንጻር ይህን ርዕስ አንስተን ማውራት ተገቢ ስለሆነ እንዳስሰው። ሶማሊላንድ ማነች? ታሪኳ ምንድን ነው? በሷ ምክንያት ኢትዮጵያና ሶማልያ ወደ ጦርነት የመግባት እድል የደረሰባቸውስ ለምንድን ነው?
ታሪኩን ለመረዳት መጀመሪያ ስለ ሶማሊ ህዝብ ማንሳት ይጠበቅብናል። ይህ ህዝብ ሰፊና ውስብስብ ታሪክ ያለው በመሆኑ በዚህ በአንድ ፖስት የምጨርሰው አይደለም። ግን በጥቂቱ እንመልከት። የሶማሊ ህዝብ የተለያዩ ጎሳዎች አሉት። ከነዚህ ጎሳዎች ደግሞ ዲር የሚባለው አንዱ ነው። ይህ ጎሳ የድሬደዋ ከተማ ስም በርሱ የተሰየመ ነው። ከሃረር እስከ ዘይላና በርበራ ማለትም የህንድ ውቅያኖስ ድረስ የተዘረጋ በሶማሊያም በኢትዮጵያም የተንሰራፋ ጎሳ ነው። ይህ ጎሳም ሆነ ሶማሊዎች በአጠቃላይ የተለያዩ ሱልጣኔቶች እና ግዛቶችን አስተናግደዋል። ከነዚህም የአዳል ሱልጣኔት አንዱ ነበር። አዳል ሱልጣኔት፣ ከፊል ሶማሊላንድን፣ የዛሬዎቹን ሃረርና ድሬደዋ አከባቢ ጨምሮ ይገዛ ነበር። በኋላ ይህ መንግስት ከወደቀ በኋላ የኢሳቅ ሱልጣኔት የሚባለው በ18ኛው ክፍለ ዘመን በርሱ ቦታ ተነስቶ ነበር። ይህንንም የመሠረቱት የሶማሊ ጎሳዎች ኢሳቅ የሚባል ከሳኡዲ አረቢያ የመጣ ሰው ከርሱ ተገኝተናል ብለው የሚያምኑ ሲሆኑ የኢሳቅ ጎሳ ተብለው ይታወቃሉ።
ወደ ኋላ ትንሽ መለስ እንበልና፣ የዲር ጎሳ፣ ኦሮሞዎች ወደ ቦታው ሲመጡ ወደ ራሳቸው አሲሚሌት ስላደረጓቸው ይህ ቅልቅል ዛሬ ላይ ሃረርጌ የምንለው ክፍለ ሀገር ውስጥ ያሉትን ህዝብ አስገኝቷል። በሌላ ስማቸውም "አፍረን ቀሎ" በመባል ይታወቃሉ። ታድያ እነዚህ የዲር ጎሳዎች በኦሮሞ አሲሚሌት የሆኑት ብቻ ሳይሆኑ በመላው የዛሬዋ ሶማሊያ፣ የኛዋ ሶማሊ ክልል፣ እንዲሁም በከፊል ጅቡቲ ውስጥም ይገኛሉ። በስራቸውም ብዙ ንኡስ ጎሳዎች አሏቸው። ከነዚህ ውስጥም የኢሳ ንኡስ ጎሳ ይገኝበታል። ይህኛው ኢሳ ቀደም ብለን ካነሳነው ኢሳቅ ጋር አንድ አይደለም። ግን ሁለቱም ሶማሊላንድ እና በከፊል ጅቡቲ ውስጥም ይገኛሉ። ኢሳዎች አሁንም ኢትዮጵያ ውስጥ አፋሮችን ጎረቤት ሆነው ይገኛሉ። አንዳንዴም በመሃላቸው ግጭት ይነሳል። ምናልባትም በሁለቱ መሃል የሚፈጠር ግጭት ለመላዋ ኢትዮጵያ —— ወረራ በር ሊከፍት ይችላል።
ብቻ የሆነ ሆኖ፣ የኢሳቅ ጎሳዎች በአሁኗ ሶማሊላንድ ውስጥ የራሳቸው ሱልጣኔት መስርተው ሳሉ ኢንግሊዞች በመምጣት ይወጓቸዋል። መጀመርያ ላይ ቢሸነፉም ያው እንደተለመደው መጨረሻ ላይ ያሸንፉና ከአከባቢው የጎሳ መሪዎች ጋር ስምምነት ተፈራርመው በኢንግሊዝ የበላይ ጠባቂነት ለመመራት ይስማማሉ። ይህ ከመሆኑ በፊት ንጉስ ምኒሊክ ቦታውን ለመቆጣጠር፤ ዘይላን እና በርበራንም በኢትዮጵያ ስር ለማድረግ ትልቅ ህልም ነበራቸው። ኢንግሊዞች ግን ይህንን በፍጹም ሊፈቅዱ አይችሉም። ለዚህ ነው አስቀድመው ቦታውን የያዙት። ከዚያም በኋላ ምኒልክ ትኩረታቸው እንዲወሰድ በቀይ ባህር በኩል ጦርነት ያስነሱት ለዚያ ነው።
ይህ በንዲህ ሳለ ከሶማሊላንድ ውጪ ያለው የሶማልያው ግዛት ከፊሉ ዛሬ ኦጋዴን የሚባለው በስምምነት ለምኒሊክ ሲሰጥ ሌላው የህንድ ውቅያኖስ ዙርያ ያለው በሙሉ ደግሞ በጣልያን እጅ ነበር። በኋላም የአፍሪካ ሃገራት "ነፃነታቸው" ሲታወጅ፣ ሶማሊላንዶች ከሶማልያ ጋር አንድ ለመሆን ተስማምተው የሶማልያ ሪፐብሊክን መሰረቱ። ነገር ግን ከደቡቡ ሶማልያ ጋር ወድያው ነበር አለመግባባቶች የተፈጠሩት። በኋላም ዚያድ ባሬ በሶማሊላንድ የኢሳቅ ጎሳዎች ላይ ከፍተኛ ጄኖሳይድ እንዳካሄደና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን እንደገደለ ይነገራል። ይህም ሶማሊላንዶች ከሶማልያ ጋር እስከዛሬም የማይስማሙበት አንዱ ምክንያት ነው። ከዚያም አስር አመት የፈጀ ጦርነት አድርገው ግዛታቸውን ነጻ አወጡ። ግን ማንም የዓለም ሀገር እውቅና ሊሰጣቸው ስላልቻለ አሁንም ድረስ በሶማልያ ስር ይቆጠራሉ። ነገር ግን የራሳቸው ፕሬዝዳንት፣ የራሳቸው ኢኮኖሚ፣ የራሳቸው መከላከያም ጭምር አላቸው።
አሁን ካለው የጂኦ-ፖለቲካ ሁኔታ ጋር ካየነው ደግሞ እነሱ እጅግ እስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ ናቸው። በቅርቡ እስራኤል የነሱን ሉዓላዊነት እንደምትቀበል አሳውቃለች። ይህ ለምን ሆነ? ስንል የመን ውስጥ ሁቲዎች እስራኤልን ፋታ ነስተዋታል። ቀይ ባህር ላይ የሚያልፉ መርከቦቿን፣ የአሜሪካ መርከቦችን ጨምሮ፣ ሁቲዎች ከኢራን ባገኙት መሳርያዎችና ሚሳኤሎች ተጠቅመው እያወደሙባት ነው። ኢስራኤል ተደጋጋሚ አየር ድብደባ ብትፈጽምባቸውም በመርከቦቿ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መታደግ አልቻለችም። እነሱም ለይተው የሷን እና የአሜሪካን መርከቦች ብቻ ይመታሉ። ስለዚህ እስራኤል አንዱ መፍትሄዋ፣ የመን ባለችበት የቀይ ባሕር መግብያ፣ ማለትም የኤደን ባሕረ ሰላጤ በሚባለው፣ ቅርብ ቦታ ላይ ጦሯን ማስፈር ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ አንዱ መልካም መፍትሄ ዘይላ ወይም በርበራ ላይ መስፈር ነው። ያ ማለት የሶማሊላንድን ሀገርነት እውቅና ትሰጣለች ማለት ነው። ታድያ አሁን ባለው አሰላለፍ፣ እስራኤል፣ ቱርክ እና አረብ ኤምሬት አንድ ጎራ ናቸው። ቱርክ ደግሞ በተመሳሳይ የራሷን ጦር ሰፈር ሶማልያ ላይ ማስፈር ትፈልጋለች። ቱርክ በቅርቡ ኢትዮጵያና ሱማልያን አስማማው ብትልም ስምምነቱ እሷና የኢትዮጵያን መንግስት ጠቅሞ፣ ሶማልያን እንደሚጎዳ አሳምራ ታውቃለች።
የእስራኤል ዋና ደጋፊ የሆነችው አሜሪካም ሶማሊላንድን እውቅና መስጠቷ አይቀርም። ትራምፕ ስልጣን ሲይዝ ያንን እንደሚያደርግ ተናግሯል። ያም ማለት፣ የኛው መንግስትም የሶማሊላንዱን ነገር ይገፋበታል ማለት ነው። ያም ማለት ከሶማልያ ጋር ሃይለኛ ጦርነት አይቀርም ማለት ነው። ምክንያቱም፣ ሶማሊላንድን መውሰድ ሲፈልጉ የሚመጣው መዘዝ አለ፣ በዚህ መሃል የኛው መንጌ የነሱን ቆሻሻ ስራ ይሰራላቸዋል፣ እነሱም ቀስ ብለው ቦታ ቦታቸውን ይይዛሉ ማለት ነው። በሶማሊላንድ ተጠቅሞ የውክልና ጦርነት ይከፍታል። ያም ጦርነት ገንፍሎ ወደዚሁ ይመጣል። ከዚያም ሲብስ ደግሞ፣ ኤርትራም ሱዳንም ግብጽም አልሸባብም ኢትዮጵያን ይወጓታል ማለት ነው። የኛ መንግስትም ሁሉም ነገር ከአቅሙ በላይ ሲሆን፣ እርዱኝ ብሎ ጥሪ ያቀርባል፣ እነሱም እሱን ለመርዳት ብለው ጦራቸውን ያመጣሉ፣ እነ ሩስያም የሱን ተቃዋሚዎች ደግፈው ይመጣሉ፣ ከዚያ መላውን የአፍሪካ ቀንድ የሚያካትት ይፈጠራል የለየለት የውክልና ጦርነት ይፈጠራል። ዝርዝሩ እንዴት ይሆናል? አሁን ላይ እንዲህ ብሎ መናገር አይቻለም። በጣም የተወሳሰበ ነገር አለው። ገና ከዚህም በላይ ይወሳሰባል። ያው መጨረሻው ግን የኛ በጦር ጀት መደብደብ፣ በአልሸባብ መወጋት፣ ወዘተ ነው የሚሆነው። ውጊያውም በጎራ በጎራ መሆኑ አይቀርም። ሰሜኑ በራሱ ውጊያ በኤርትራ እና ሱዳን በኩል ይጠመዳል፣ ኦሮሞ፣ ደቡቡ ደግሞ ከሶማሊው ጋር ይዋጋል። ብቻ ዝብርቅርቅ ያለ ነገር መፈጠሩ አይቀርም። በጣም ድብልቅልቅ ከመሆኑ የተነሳ ሁሉም ሰው "ቆይ ምን እየተካሄደ ነው?" ብሎ ይጠይቃል፣ መልስ የሚኖረው ግን የለም።
እኔም ይህን ጽሁፍ አሁን የምጽፈው፣ ቢያንስ ከአሁኑ የተውሰነ ፍንጭ እንዲኖረን ነው። ቢያንስ በጥቂቱ እንኳ አስቀድሞ ማወቅ፣ ንስሃ ገብቶ ለመጠበቅም ቢሆን ይጠቅማል።
ብቻ የሆነ ሆኖ፣ ይህ ክስተት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም እንዲበታተኑ ምክንያት ይሆናል። የአፍሪካ ቀንድን ስሪትም ይቀይራል። ወይ ኢትዮጵያ ከነ አካቴው ፈራርሳ ትጠፋለች፣ ወይም በሆነ መለኮታዊ ተአምር መላውን የአፍሪካ ቀንድ በአንድ ላይ ጠቅልላ ትይዛለች።