የሰሞኑ መሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ያለው ስምጥ ሸለቆ ጠቦ ወደ አንድ የሚመጣበት ቦታ ላይ ነው። ማለትም የአፋር ትሪያንግል የሚባለው ከላይ በቀኝ በኩል የሚታየው የርሱ አንዱ ጫፍ ላይ ነው። ይህም ማለት በዚሁ ከቀጠለ እዛ አከባቢ ያለው መሬት ሁለት ሳይሆን 3 ቦታ የመሰንጠቅ እድሉ ሰፊ ነው ማለት ነው። ይህም ስንጥቅ እስከ ጅቡቲ ሄዶ አንዱ እስከ ኢርትራ አንዱ ደግሞ እስከ ጅቡቲ ሊደርሱ ይችላሉ፣ በዚህም ምክንያት በሚፈጠረው ክስተት ወይ ከመሃል ያለው የአፋር ክፍል ተከፍቶ በሁለት በኩል ውሃ ያስገባና ደሴት ይሆናል፣ አልያም ደግሞ ሙሉ በሙሉ ሰምጦ በሱ ቦታ ሰፊ ባህር ይሆናል።