አንድ ሰው በአስተሳሰቡና የእምነት ስርአቱ ውስጥ ከሚያስፈልጉት ወሳኝ ነገሮች አንዱ ወጥ የሆነ የተስተካከለ እምነቶችን መያዝ ነው። ይህን ስንል ምን ማለታችን ነው? አረፍተ ነገሩን አንድ በአንድ ተንትነን እንመልከት።
በመጀመሪያ የእምነት ስርአት ስንል ምን ማለታችን ነው? ይህ ማለት አንድ ሰው የሚያምናቸውና የሚቀበላቸው ሀሳቦች እምነቶች ስብስብ ነው። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ግለሰቡ ያለው እምነት ወይም አቋም በአጠቃላይ ሲሰበሰብ የግለሰቡ እምነት ስርአት ይሆናል።
ታዲያ ይህ የእምነት ስርአት ወጥ ነው ስንል ደግሞ የሚያምናቸው ሀሳቦችና እምነቶች የማይጣረሱ፣ የማይምታቱ፣ የተስማሙ ናቸው ማለታችን ነው። ለምሳሌ ሰዎች እግዚአብሔር ዓለምን ፈጠረ ብለው ያምኑና መልሰው ደግሞ በኢቮሉሽን እናምናለን ይላሉ። ይህ የእምነት ስርአታቸው ወጥ አለመሆኑን ያሳያል።
በሌላ መልኩ ካየነው ደግሞ አንዳንዴ አንድን ሀሳብ እንደ እውነት ከተቀበልን በኋላ፣ የእምነት ስርአታችን ወጥ ይሆን ዘንድ የዛን ሀሳብ ድምዳሜም መቀበል አለብን። ማለትም ያንን ሀሳብ ተከትሎት የሚመጣውን ምክንያታዊ ድሞዳሜም ትክክል መሆኑን ማመን አለብን። ለምሳሌ ሰዎች ሁሉ መጥፎ ናቸው ብለን የምናምን ከሆነና አንድ መልካም ሰው ካጋጠመን፣ ይህ ሰው መልካም ነው ካልን አስተሳሰባችን ወጥ አልሆነም፣ የእሳቤያችንን ምክንያታዊ ድምዳሜም አንቀበልም ማለት ነው።
ማለትም "ሰው ሁሉ መጥፎ ነው" የሚለውን ሃሰብ እንደ እውነት ከተቀበልን፣ "ይህም ሰው መጥፎ ነው" የሚለው የርሱ ምክንያታዊ ድምዳሜ ነው። ስለዚህ ምክንያታዊ ድምዳሜውን መቀበል አለብን ማለት ነው።
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሰዎች የተሳሳቱ ሀሳቦችን እንደ እውነተኛ ይቀበላሉ። ከዚያም ቀጥሎ ያለው የሀሳቡ ድምዳሜ ይበልጥ የተሳሳተ መሆኑን ሲያዩ እሱን ሳይቀበሉ ይቀራሉ። ነገር ግን አስተሳሰባቸው ወጥ እንዲሆን ሁለቱንም መቀበል አለባቸው። ወጥ ካልሆነ ትልቅ ችግር ያጋጥማቸዋል። ለምሳሌ አስተሳሰባቸው ወይም የእምነት ስርአታቸው ወጥ አለመሆኑን ያስተዋለ ሰው በክርክር ወቅት የሀሳባቸው ድምዳሜ የሆነውን የተሳሳተ ሀሳብ እንዲቀበሉ ሊገፋፋቸው ይችላል። የተሳሳተ ሀሳብ የሆነው ድምዳሜ በትክክል የመጀመሪያ የተቀበሉት ሀሳብ ምክንያታዊ ድምዳሜ መሆኑን በትክክል አሳይቶ እንዲቀበሉ ሊገፋፋቸው ይችላል። ያኔም መቀበል ግድ ይሆንባቸዋል። ይህን በምሳሌ ለማስረዳት ያህል፣ "ሀሉም እንስሳት አራት እግር አላቸው" የሚለውን ሀሳብ እንደ እውነት የተቀበለ ሰው፣ "ዶሮ አራት እግር አላት" የሚለውን የሀሳቡን ድምዳሜም እንደ እውነት መቀበል ይኖርበታል። ምክንያቱም እንስሳት ሁሉ አራት እግር ካላቸው ዶሮም አራት እግር ሊኖራት ይገባል። ምክንያቱም ዶሮ እንስሳ ናት።
ስለዚህ ይህ ሰው ሁለት ምርጫ አለው። ወይ ድምዳሜውን መቀበል፣ አልያም መነሻውን ሀሳብ ከነ አካቴው መተው።
ይህንን ሀሳብ በሌላ ወሳኝ ምሳሌ እንመልከተው። አንድ ክርስቲያን ሰውን እንውሰድ። ይህ ሰው ክርስቲያን ነኝ ብሎ ካሰበ፣ ፈጣሪ ምድርን በስድስት ቀን ፈጠራት የሚለውን ሀሳብም መቀበል አለበት። ካልሆነ የእምነት ስርአቱ ወጥ አይደለም ማለት ነው። ሀሳቡን አንድ እርምጃ ወደፊት ብንወስደው፣ ብዙ ክርስቲያኖች በግሎብ ምድር ያምናሉ። ስለዚህ የምንኖርባት ምድር በትልቅ ድቡልቡል ፀሐይ ዙርያ የምትሄድ ድቡልቡል ፕላኔት ናት ብለው ያምናሉ። ይህም ሰው ያንን ያምናል እንበል።
ይህ ሰው ከላይ በጠቀስነው ካመነ፣ በቢግ ባንግም ማመን አለበት። ለምን? ምክንያቱም በግሎብ ቲዮሪ መሠረት ዓለም የተፈጠረችው በዚያ መልኩ ስለሆነ። ያንን ብቻ አይደለም። ይህ ሰው በኢቮሉሽን ማመን አለበት። ምክንያቱም ሳይንሱ እንደሚለው በግሎብ ምድር ላይ ህይወት የተገኘው በመቶ ሚሊዮን ዓመታት ሂደት ውስጥ ነው። በውቂያኖስ ውስጥ ኬሚካሎች ተቀላቅለው ባክቴሪያ፣ ከባክቴሪያ አሜባ መሰል ነገሮች ተገኙ፣ ከሱም የባህር ውስጥ ትል ተገኘ፣ ከትሉም ሄዶ ሄዶ አሳ፣ አሳም ከባህር ወጥቶ አዞ፣ አዞም በሂደት ወደ አጥቢ እንስሳ አይነት፣ ያም ተቀይሮ ወደ ተለያዩ ዝርያዎች ተቀየረ፣ ከርሱም ዝንጀሮ መሰል እንስሳት ተገኙ ሰውም ከነሱ ከአንዱ ተገኘ ይላል።
ስለዚህ፣ ምድር ከቢሊዮን ዓመታት በፊት በድንገተኛ ክስተት የተገኘች ፕላኔት ናት የሚለውን ከተቀበልን። እኛም በሷ ላይ በሚሊዮን ዓመታት ድንገተኛ ሂደት ውስጥ ነን የተገኘነው የሚለው የሱ ምክንያታዊ ድምዳሜ ይሆናል።
ስለዚህ የመጀመሪያውን ሀሳብ የተቀበለ ሰው ሁለተኛውንም መቀበል ግድ ይሆንበታል። ነገር ግን ያንን የተቀበለ ሰው ተመልሶ ፈጣሪ በስድስት ቀን ዓለምን ፈጠራት የሚለውን ሊቀበል ይችላል?
መልሱ አይችልም ነው። ለራሱ ሀቀኛ የሆነ ሰው ያንን ማድረግ እንደማይችል ያምናል። ለዚያ ነው ብዙ ሳይንስ የገባቸው ሰዎች የፈጣሪን መኖር የሚክዱት። ምክንያቱም ሁለቱ ሀሳቦች መሠረታዊ ቅራኔ እና መጣረስ በመካከላቸው እንዳለ እውቅና ስለሚሰጡ።
የዚህ ጽሑፍ ዓላማ በፈጣሪ መኖር እንዳታምኑ ማድረግ አይደለም። ይልቁንም፥ አማራጩን ሀሳብ መስጠት እንጂ። አማራጩ ምንድን ነው?
ቀድሞውኑ መነሻ ሀሳቡን አለመቀበል።
"ምድር በቢሊዮን ዓመታት ድንገተኛ ክስተቶች ሂደት የተፈጠረች ዱቡልቡል አካል ናት" የሚለውን በሙሉ ወደጎን መተው ነው።
ያንን ካደረግን፣ የእምነት ስርአታችን ያልተጣረሰ ወጥ ይሆናል። ምክንያቱም አንደኛ፣ ፈጣሪ በእቅድና በዓላማ ፈጠረን ከሚለው እምነታችን ጋር አይጋጭም። ሁለተኛ፣ "ምድር በቢሊዮን ዓመት ድንገቴ ክስተቶች የተፈጠረች ግሎብ ናት" የሚለውን የተሳሳተ ሀሳብ ሳንቀበል ከተውን፣ "አስቦና አቅዶ ዓለምን የፈጠረ አካል የለም" የሚለውን የተሳሳተ፣ ግን የዛኛው ምክንያታዊ ድምዳሜ የሆነውን ሀሳብም መቀበል አይኖርብንም።
ስለዚህ ወጥ የእምነት ስርአት ካለን ምን ብለን እናምናለን? ፈጣሪ በእቅድና በዓላማ ዓለምን ፈጠረ፣ ምድርም በርሱ የተፈጠረች ዝርግ አድርጎ ላይዋን በሰማይ ጉልላት ከድኖ ፈጥሯታል፣ እኛንም የሚያስፈልገንን ሁሉ ሰጥቶ በርሷ ውስጥ አኑሮናል።
ብለን እናምናለን።