የክርስቶስ ልደት በቅዱስ ኤፍሬም
እመቤታችን በቤተልሔም ርሱን እየደባበሰች ዘመረችለት ስትስመውም ርሷን ለማግኘት ዞረላት፣ ወደ ርሷም ተመልክቶ በርሷ ላይ ዐርፎ እንደ ሕፃናት ፈገግ አለ፤ በጨርቅም ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኛ (ሉቃ ፪፥፯)፤ ማልቀስ ሲዠምር ተነሥታ ወተት ሰጠችው፤ ስትዘምርለት ዐቀፈችው፤ እስክታቅፈው ድረስም በጉልበቶቿ ተንበረከከች፡፡
የአንተ ዘር የኾነ ዳዊት ከመምጣትኽ በፊት በረጅም ግጥም ይዘምርልኻል፣ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለኽ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ በሳባ ወርቅ ትንቢት ውስጥ የዘመረልኽ ፣ - እና አኹን መዝሙሩ እውነት ኾኗል (መዝ ፸፩፥፲፭)፣ እነዚኽ ወርቆች፣ እጣንና ከርቤ ለአንተ ለጌታ ለኀያሉ ልጅ ቀርበውልኻል፣ ወርቅ ለንጉሥነትኽ፣ ዕጣን ለመለኮታዊነትኽ፣ ከርቤም ሥጋን ስለ መዋሐድኽ (ማቴ ፪፥፲፩)፡፡
አንተ በአባትኽ ዕሪና፣ በማርያም ውስጥም ነኽ እና በሠረገላውም ላይና በበረት ውስጥ በኹሉም ቦታ ነኽ! በእውነት በአባትኽ ዕሪና ውስጥ ነኽ፣ ያለምንም ጥርጥር በማርያም ውስጥ ነኽ፣ በሠረገላው ላይ እና በተናቀው በረትም ውስጥና በኹሉም ቦታዎች፤ አንተ የኹሉ ፈጣሪ ምሉእ በኲለሄ የኹሉ ሠሪ፤ አንተ ከአባትኽ ነኽ፣ ቢኾንም ግን ከማርያምም ነኽ፤ አንተ አንድ ነኽ፣ አንተ የመጣውና የሚመጣው ነኽ (ዕብ ፲፫፥፰)፡፡
የአንተን መለኮታዊነት በጥልቀት በመመራመር ለሚፈልገውና ለሚመረምረው ወዮለት፤ አንተን የማያምን ወዮለት፣ ለአንተ ፍቅሩን የማያሳይ ወዮለት፣ በአንተ እምነት የሌለው ወዮለት፣ አንተን ችግር (ሕጸጽ) አለብኽ ብሎ የሚያስበው ወዮለት፣ የአንተን ስም እግዚአብሔር እንደኾንኽ የሚጽፈው የተባረከ ነው፤ የአባትኽ በረከት፣ የፍቅርኽ በረከት የመንፈስኽ በረከት በአንተ ልደት በሚደሰት ላይ ኹሉ ላይ ይኹን!፡፡
የባሕርይ አምላክ ለኾንኸው ብላቴና እሳታሞች የሚካኤል ነገድ ይርዳሉ! ኪሩቤሎችና ሌሎቹ እንስሳት ተቀናጅተው ሠረገላኽን ይሸከማሉ፤ የኤልሻዳይ ልጅ ሆይ ርቱዕ የኾኑት መንኰራኲሮች ላንተ በቂ አይደሉም (ራእ ፬፥፮)፤ ግን የማርያም ንጹሕ ዕቅፏ አንተን ይዟል፣ ይኽ እንዲኾን ቸርነትኽ ፈቅዷልና፤ የማትወሰን ስትኾን ተወሰንኽ የምሕረትኽ ባሕር የማይወሰን ሲኾን፡፡
የአንተ ዕይታ አስደሳች ነው፤ መዐዛኽ ጣፋጭ ነው፣ አፎችኽ ቅዱስ ናቸው፤ ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ ከአንተ ሕይወት ኹሉ ይመጣል፤ የአንተ ኅብስትነት ቤተ ኅብስት ለተባለችው ቤተልሔም ሕይወት ነው፤ ለሚኖሩት ኹሉ ሕይወታቸው ነኽ፤ እስትንፋስኽ እንዴት ጣፋጭ ነው? ሕፃንነትኽ እንዴት ተፈቃሪ ነው፤ አንተ ለምግብነት በጣም የምትፈለግ ሩህሩህ ሆይ የሰማያት ምግብ የኾንኽ ለአዕዋፍም ሕይወትን የሰጠኽ ነኽ፤ ከድንግል የተወለድኽ ብላቴና ሆይ የአንተን ደም የናፈቀ የተባረከ ነው (፩ኛ ዮሐ ፩፥፯)፡፡
ሕያው የእግዚአብሔር ጠቦት ሆይ እረኞች ለአንተ የሚጠባን ጠቦት በስጦታ አቀረቡልኽ፤ ተንበርክከው አመለኩኽ፣ አንተን ዐውቀውኽ ምስጋናቸውን ለእውነተኛው እረኛ ለአንተ ለጌታ አቀረቡ (ሉቃ ፪፥፳)፡፡ ረቂቃን ከኾኑ ከመላእክት ምስጋና “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይኹን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ” በማለት ምስጋናን ከሚያቀርቡ በግልጽ ከሚያውጁ ረቂቃን ከኾኑ ከመላእክት ክብር የተነሣ ኹሉም በመገረም ተመለሱ (ሉቃ ፪፥፲፬)፡፡
አንተ የአብ ልጅና የማርያም ልጅ ነኽ፡- አንድና ተመሳሳይ ነኽ የእግዚአብሔር ቃሉ ሆይ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ከአብ የተወለድኽ ከተፈጥሮ ውጪም (በላቀ) ከእናቱ ተወልደኽ የመጣኽ … የባሕርይ አምላክ ሆይ አንተ ብቸኛ ልጅ ነኽ፤ ባንተ ውስጥ የማያልቅ የሚነገር ስዉር ጥበብ አለ፤ ስለዚኽም ከዳዊት የራሱ ልጅ ድንግልናዊ ወተትን ተኝተኽ ትጠባለኽ፡፡
ኀያሉ እግዚአብሔር ሆይ ማሕፀኗ ወልዶኻል፣ የከብቶች ግርግም በቅቷል (ሉቃ ፪፥፯) ስምዖን ተሸክሞኻል (ሉቃ ፪፥፳፰)፤ እዚኽ ላይ አንተ ሊነካ እንደሚችል የኾነ ሰው በሰውነት ቅርጽ ተወስነኽና ተይዘኻል፡፡ በጭራሽ ሊወሰን የማይችል ባሕርይ ነኽ ግን በዚኽ ላይ በትንሿ የከብቶች ግርግም ላይ ተወስነኻል! አኗኗርኽን ማን ሊይዘው ይችላል እዚኽ ላይ በተወሰነ ቦታ ውስጥ ነኽ! ምንም እንኳን ልትወሰን የማትችል ወልድ ብትኾንም ግን በተዋሐድከው ሥጋ ለመወሰን ፈቃድኽ ኾኗል፡፡
የምትመስለው ማንን ነው? አባትኽንም እናትኽንም ትመስላለኽ፤ እግዚአብሔር መጠን የለውም ከቀለምኽ ውጪማ በኀያልነትና በባሕርይ በአኗኗርም ጭምርና በሥልጣን አባትኽን ትመስላለኽ (ዮሐ ፲፬፥፱)፡፡ ግን የሰውን ቅርጽ ያገኘኽባት የወለደችኽ ማርያምንም ጭምር ትመስላለኽ፤ አባትኽንም እናትኽንም ራስኽንም ትመስላለኽ፡፡ አርአያ ገብርን ለነሣኸው ለአንተ ምስጋና ይግባኽ (ፊልጵ ፪፥፯)፡፡
አንተ እንዴት ጽኑዕ ነኽ፤ ግን ቅን (ትሑት)ና ኀያልም ጭምር ነኽ! (ማቴ ፲፩፥፳፱) የአንተ ልደት የተሰወረና የተገለጸ ነው፤ እንደ ብላቴና በማንኛውም ሰው ፊት ለፊት ራስኽን ታስጠጋለኽ፡፡
ለሚያጋጥሙኹ በሙሉ ፈገግ ትላለኽ፤ ለሚስሙኽ በሙሉ ዐይኖችኽ በደስታ ይፍለቀለቃሉ፤ ከንፈሮችኽ የሕይወትን በጎ መዐዛ ይመግባሉ (ያስገኛሉ) (መሓ ፬፥፲፩)፤ ከጣቶችኽ ጫፍ በጎ መዐዛ ያለው ከርቤ ይንጠባጠባል (መሓ ፭፥፭)፤ ዐይኖችኽ የአንተን ዕይታ በተራበችው እናትኽ ላይ በፍቅር ተተክለዋል፤ ልክ እንደ ቤተ ክርስቲያኗ የራሷ ልጆች (ምእመናን) በአንተ የተራቡ ናቸው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Source: @ortodoxmezmur