🔔በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት እየተደረገ ነው ተባለ። 😒
ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወርቁ ደስታ ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ " በሁለተኛው ምዕራፍ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት በመኪና ማቆሚያዎች የኃይል መሙያ እየተሠራ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ዴዔታ በርኦ ሀሰን፥ ደግሞ " ከዚህ በኃላ የተሽከርካሪ አስመጪና የሚገጣጥሙ ድርጅቶች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ሳይተክሉ በሥራ ላይ መሰማራት አይችሉም " ብለዋል።
" አሁን ላይ ከ400 በላይ ተቋማት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ እያስመጡና እየገጣጠሙ ናቸው " ያሉ ሲሆን ሁሉም የኃይል መሙያ አላቸው " ሲሉ ገልጸዋል።
የመረጃው ባለቤት ኤፍኤምሲ ነው።
@hawassacityfuel #Hawassa
https://t.me/hawassacityfuel ✅