ቤርያ ሰዎች


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


☞ How to touched by Holy spirit
☞ How to known the will of God
☞ How increase from faith to faith

Tamrat. @Lijtame

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций








Репост из: GOSPEL TV ETHIOPIA
💎Church እንዴት ነበር?💒

✍️ "ከመስመር ስተሃል የሚባለው መስመር ውስጥ ላለ እንጂ ከመስመር ውጭ ላለ አይደለም ... ስለዚህ በጌታ ያልሆኑትን ዳግም ተወለድ በጌታ ሆኖ የሳተውን ተመለስ በማለት የምናምነው..." ስለዚህ ለጻድቅ ንስሃ አለ! "እግዚአብሔርን መውደድ" በሚል የተጀመረው ት/ት በእርሱ ስር ደግሞ ሁለንተናችን ምንድን ነው? (What is our whole being?) የሚለው ንዑስ ርዕስ ቀጠለ...

◈ God is love and He become a man named Jesus Christ. When we receive Jesus Christ we receive all that He is into our spirit.

እግዚአብሔር በሁለንተናችን እንድንወደው የነገረን ሲሆን ስለሁለንተናችን በሚገባ መረዳት አስፈላጊ ነው።

❤️ስለመንፈሳችን

◍ መፅሐፍ ቅዱስ "ልብ" ብሎ ሲያወራ ስለ መንፈሳችን እያወራ እንደሆነ መረዳት አለብን። ሁልጊዜ የክርስትና ድንቅ ነገሩ ደግሞ ልብን ወደ እግዚአብሔር መመለሳችን ነው። ልባችን ከጌታ በዞረ ጊዜ የጌታን ክብር ማብለጭለጭ አንችልም ልባችንን ወደ ጌታ ስንመልስ ግን የጌታ ክብር በእኛ ይገለጣል። ለዛም ነው ልባችን ወደ ጌታ በቀረበ መጠን እኛ ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር እየጨመረ ይሄዳል።

#ልባችን እንዴት ይቀርባል?
📌 በፀሎት ወደ ጌታ ስንመለስ
📌 ስሙን ስንጠራ
📌 ስንናዘዝ
📌 ደሙን ስንጠራ
📌 ከቃሉ ጋር ጊዜ ስናሳልፍ ይህ ነገር መጋረጃን ከልባችን ላይ ይወስደዋል።

💎 ተሐድሶ በግል ካልመጣ እንደብዙ መጠበቅ ዘበት ነው!

❤ስለ አእምሮአችን

◍ Our mind is the leading part of our soul, directing the rest of our being. It can be set on many things but God wants it be set on the spirit, where Christ is.

◍ አእምሮአችን የነፍሳችን ወሳኝ ክፍል ከሆነች ልንጠይቅ የሚያስፈልገው ጥያቄ "አእምሮዬ የት ነው ያለው? ትኩረቱንና አቅጣጫው ምን ላይ ነው ያደረገው?" የሚለውን ነው። ምክንያቱም አእምሮአችን ትኩረት ያደረገው ወደ ህይወታችን መተርጎሙ የማይቀር ነው።

በመጨረሻም የምንጠቀመው ነገር ሁሉ "Setting" ያለው ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ "Mind setting" የሚባልም ነገር አለ ስለዚህ መንፈስ ላይ ትኩረት ያደረገ አእምሮ የተቃኘበት ቅኝትና መተግበሪያ ያለው ሲሆን እርሱም የስኬትና የአልቆምም ቅኝት ነው።

▣ በትምህርቱ የተነሱ ጥቅሶች፦ 2ቆሮ 3፥16፣ ያዕ2፥፣ 1ነገ 8፥58፣ 2ተሰ 3፥5፣ መዝ 44፥18፣ ዕብ 10፥22፣ ኢሳ 26፥3

Church አይቀርም😂!

❤ሬቨ. ተዘራ ያሬድ (DADDY)
የትም. ርዕስ፦ እግዚአብሔርን መውደድ
(Loving God)
ክፍል 3


ክርስትና ምንድነው?

👉ክርስትና  ማለት ሀይማኖት ሳይሆን ሂወት ነው ።
• 👉 ይህ ሂወት ደሞ የክርስቶስ ሂወት ሲሆን የሚጀምረው  ራስን ከመካድ ነው።
☝️እሺ ይሄን ሀሳብ እንመልኸት።     
          1.   በ (ማቴ 16: 24)እና በ(ሉቃ 9: 23)

     "  ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።"
        2. (ገላ 1: 15-16)
" ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ
በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥"
      3(ገላ 2: 20)
" ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።"

ብሩካን ናችሁ!


Репост из: GOSPEL TV ETHIOPIA
“በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።”
— ሮሜ 1፥16

🎶 በወንጌል አላፍርምና
◇ የ22 ሰዓት mp3 🎧
💎 በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ

Get Your Copy!

📞 +251 96 101 4444
+251 92 866 7676
+251 92 866 7979

☆ ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ አንድ ቃል ሕይወትዎ ለዘላለም ይለወጣል።


Репост из: Tamrat lēsoūs
አዲስ ፍጥረት || ክፍል ሶስት ✍

ኢየሱስ ከመስቀል እስከ ዙፋን ድረስ ባለው ጉዞ ምን አገኘን?
1. የምትክነት ስራ ነው የሠራው (Substitution)
☆ ኢየሱስ ያደረገውን ሁሉ ያደረገው እኛን በመወከል ነው።
1.1 እርሱ ስለ እኛ ቆሰለ እኛ ተፈወስን [ኢሳይያስ 53፥1]
1.2 እርሱ ስለ እኛ ኃጢአት ሆነ እኛ የእርሱ ፅድቅ ሆንን [2 ቆሮንቶስ 5፥21]
1.3 እርሱ ስለ እኛ ደሀ ሆነ እኛ ባለጠጋ ሆንን [2 ቆሮንቶስ 8፥9]
1.4 እርሱ ስለ እኛ እርግማን ሆነ እኛ በረከትን አገኘን [ገላትያ 3፥11-14]

2. ማንነታችን በክርስቶስ ሲታወቅ (Identification)
☆ ማንነት መታወቂያ ሲሆን ስለ አንተ ማንነት የሚናገረው አለው። ጌታን ስንቀበል ደግሞ የማንነት ለውጥ አድርገናል።

2.1 ከክርስቶስ ጋር ተሰቀልን
☆ ከክርስቶስ ጋር መሰቀል ማለት የእኔን በሽታ፣ ድህነት፣ እርግማን፣ ኃጢአት ሁሉ ከእርሱ ጋር በመስቀል ላይ ተሰቅሏል ማለት ነው።
ሀ. ከክርስቶስ ጋር ሞቻለው [ገላትያ 2፥20]
ለ. ከክርስቶስ ጋር ተነስተን በአብ ቀኝ ከክርስቶስ ጋር ተቀምጠናል [ኤፌሶን 2፥4]
ሐ. ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነናል [1 ቆሮንቶስ 6፥17]
__________________

“ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።”
— 2ኛ ቆሮ 5፥17

🎶 አዲስ ፍጥረት 🌼
◇ የ24 ሰዓት mp3 🎧
💎 በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ


ዕብራውያን 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁵ እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ።

³⁶ የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።


ሊደመጥ የሚገባው የወቅቱ መልዕክት!

💎 በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ

👉 @AgapeGLC
@AgapeGLC


ሊደመጥ የሚገባው የወቅቱ መልዕክት!

💎 በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ

👉 @AgapeGLC
@AgapeGLC


ሊደመጥ የሚገባው የወቅቱ መልዕክት!

💎 በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ

👉 @AgapeGLC
@AgapeGLC


Репост из: AGAPE GLC
🦅 እንደ ንስር 🦅

፨ አንድ ሲደመር አንድ የትም ሆነን ብንደምረው ውጤቱ ሁለት መሆኑ እውን ነው። አማኝም ውጤቱ ያማረ እንዲሆን የሚያስገባው የእግዚአብሔርን ቃል መሆን አለበት። እግዚአብሔርን በመተማመን መጠበቅ በሚል ርዕስ ከንስር ህይወት ጋር በማነፃፀር የአማኝ ህይወት በከፍታ እንዲኖር የሚያደርገው ይህ እንደ ንስር የተሰኘው አስደናቂ ትምህርት በአጭሩ እነሆ.....

ፍጥረታትን ሁሌጊዜ ስንመለከት እግዚአብሔር ግልፅ ሆኖ ይታያል። የንስርም ህይወት በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የክርስትያንን ህይወት ወክሎ ቀርቧል።

🦅 ንስር አስገራሚ ፍጡር ሲሆን በዕብራይስጥ 'ነሽር' ማለት ሲሆን ትርጓሜውም አፉ ላይ ባለው መንቁር የሚበጣጥስ፣ የሚዘለዝል ማለት ነው። ንስር በመላው አለም የጥንካሬ፣ የነፃነት፣ የውበት እና የሥልጣን ምሳሌ ተደር ይወሰዳል።
ንስር በአዕዋፋት አለም ላይ ንጉስ ነው። ነገር ግን 40ዓመት ሲሆነው ከባድ የሆነን ውሳኔ ይወስናል። ውሳኔውም ለ150 ቀን የሚፈጅ ነው። ይህ ውሳኔ ለቀጣዩ 30 አመት ለመኖር መሰረት ነው።
ከባዱም ውሳኔ የአፉን ጥፍር (መንቁር)፣ የእግሩን ጥፍር ከአለት ጋር በማጋጨት ያወልቀዋል። በመቀጠልም ከጊዜ በኋላ የሰውነቱን ላባ በሙሉ በመንቀል እና በማስወገድ እራሱን በከባድ ለውጥ ውስጥ ያስገባል።

ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ

በተመሳሳይ መልኩ አማኝ ህይወቱ ላይ ያለውን የማይጠቅመውን እና የተጣበቀውን ነገር በእግዚአብሔር ቃል ማስወገድ ይችላል።

🦅 የንስር አስደናቂ ማንነት ከአማኝ ጋር ሲነጻጸር፦

1. ክንፉን ሳያወዛውዝ መብረር ይችላል
- ንስር የነፋስን ፍሰት በመጠበቅ ያለምንም ችግር ይበራል። አማኝም የመንፈስን ፍሰት ጠብቆ ያለ ትግል መኖር ይችላል።

2. ንስር ከሌሎች አእዋፋት ጋር አይቀላቀልም
- ንስር ከሌሎች ወፎች ጋር አብሮ አይበርም፤ አይኖርም። አማኝም በክርስቶስ ምርጥ፣ ንጉስ፣ ካህን፣ ቅዱስ ህዝብ መሆኑን በመረዳት በከፍታ እንዲኖር ማሳያ ነው።

3. ንስር ከተወለደ በኋላ ከፍተኛ ረሀብ ይዞ ነው የሚወለደው
- ንስር በጣም የሚበላ ሲሆን አማኝም ከተወለደ በኋላ ንፁህ የሆነውን የቃሉን ወተት መመገብ አለበት። ንስር የሞተ ነገር አይበላም። አማኝም ለአይናችን እና ለጆሮአችን የምንመግበውን ነገር መምረጥ አለብን።

4. ንስር ከ3ኪ.ሜ ርቀት ያለውን ነገር ያያል
- አይኑ አጥርቶ የሚያይ ሲሆን ሁለት የአይን ብሌን አለው። አንዱ ፀሀይን ትኩር ብሎ ሲመለከት በተመሳሳይ መልኩ የሚያድነውን ያያል። አማኝም የስጋ አይኑ ግዑዙን ዓለም እንዲያይ፣ መንፈሳዊ አይኑ ደግሞ እግዚአብሔርን እና በቃሉ ውሰጥ ያለውን መገለጥ ትኩር ብሎ እንዲያይ ተሰጥቶታል።

5. የንስር የጋብቻ ህይወት
- ሴቷ ንስር ወንዱን ለጋብቻ ከመቀበሏ በፊት ቅድመ ሁኔታዎች አሏት። አማኝ በተመሳሳይ መልኩ ምን ያህል ጌታን መዉደድ፣ ቃሉን መውደድ፣ ህይወት ላይ ያለ ዓላማ፣ መስጠት፣ ታማኝነት እና በመንፈስ መመራት ለጋብቻ ትልቁ ቅድመ ሁኔታ መሆን አለበት።

6. ንስር ማዕበልን ይወዳል
- የአውሎ ነፋሱ ማዕበል ንስርን ሁሌም ወደተለየ ከፍታ ያወጣዋል። ለአማኝ ችግር መውደቂያው ሳይሆን ማድመቂያውና የዕድገቱ ምክንያት ነው።

ለችግር እንዴት ምላሽ እንስጥ?

፩. በእግዚአብሔር መታመን/መደገፍ
፪. እግዚአብሔርን ማምለክ
፫. ችግሩ የመጣበት ምክንያት ለእኛ ለመልካም ሊደረግ እንደሆነ በመረዳት
፬. ፈተና ወደ ምስክርነት እንደሚለወጥ በመረዳት

🦅 ንስር ቤቱን የሚሰራው በከፍታ ሲሆን ልጆቹንም ከትልቅ ከፍታ በመወርወር መብረርን ያለማምዳሉ። አማኝም እምነታችንን ተለማምደን መንፈሳዊ ህይወታችንን ማሳደግ ይኖርብናል። ሁልግዜ ቃሉ ላይ ተቀምጠን የመንፈሱን ፍሰት በመጠበቅ ከነገሮች ሁሉ በላይ ሆነን በከፍታ ህይወት እንድንኖር የሚያደርግ ድንቅ ትምህርት ስለሆነ እንደ ንስር የሚለውን ሲዲ በመስማት እና ሙሉ ሀሳቡን (ትምህርቱን) በማግኘት ሕይወትዎን በእግዚአብሔር ቃል እውነት ይለውጡ!
ብሩካን ናችሁ !
_____________

“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”
— ኢሳይያስ 40፥31

🦅 እንደ ንስር 🎧
◇ የ20 ሰዓት mp3
💎በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ

Get Your Copy!

☆ ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ አንድ ቃል ሕይወትዎ ለዘላለም ይለወጣል።

👉 @AgapeGLC
@AgapeGLC


Репост из: Tamrat lēsoūs
“ደቀ መዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም፤ ፈጽሞ የተማረ ሁሉ ግን እንደ መምህሩ ይሆናል።”
ሉቃስ 6፥40

“ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤”
ማቴዎስ 11፥29


“ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው (የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።)”
ራእይ 12፥10


ከማን እየተማርን ነው?

መምህር ቀይሩ?


Репост из: Tamrat lēsoūs
"Man is a spirit beings he have soul & live in a body. "

Kenneth w. Hagin

"Am not a soul, am not a body am a spirit live in a body. "

Pastor Benny Hinn


1ኛ ጴጥሮስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።
²² እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤
²³ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
²⁴ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።
²⁵ እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።


Репост из: ቤርያ ሰዎች
ካህናት እና ነብያት

ብሉይ ኪዳን

👉ካህናት - ህዝቡን ወክለው በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ ናቸው፡፡ በእግዚአብሔር ፊት የህዝብ ድምፅ ናቸው፡፡

👉ነብያት - እግዚአብሔርን ወክለው በህዝቡ ፊት ይቆማሉ፡፡ በሰው ፊት የእግዚአብሔር ድምፅ ናቸው፡፡

አዲስ ኪዳን

👉የዘላለም ሊቀ ካህን ኢየሱስ ሲሆን እኛን ደግሞ ካህናት አርጎናል፣ ሰለዚህ ከእኛ የተሻለ የኛን መልዕክት ይዞ ሚገባ ሌላ ሰው የለም፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለሌሎች ሰውች(ላላመኑት) የምልጃ ኃላፊነታችንን ያሳያል፡፡ እንደ ካህን ያላመኑትን ከአምላክ ጋር የማስታረቅ ስራ ተቀብለናል፡፡

1ኛ ጴጥሮስ 2፥9
“እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ::”

1ኛ ጴጥሮስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


👉ነብያችንም ኢየሱስ ካረገ በኃላ ለቤተክርስቲያን ነብያትን ስጦታ አድርጎ ሰጥቷል፡፡




"ልሳን ከመንፈስ ፍሰት ወደ ክብር ሙላት የምንገባበት መንገድ ነው።"
Reverend Tezera yared


"To see in the prophetic u have to work on your IMAGINATION "
Apostle Tamrat Tarekegn


3 type of people in z world
---------------------------------------------
1.small mind talk about people.

2.middle mind talk about event.

3.super mind talk about idea.

Показано 20 последних публикаций.

124

подписчиков
Статистика канала