በአላህ መንገድ ሲታገል ከርሞ ወደ ኮርዶቫ ሲዘልቅ ዕለቱ ዒድ አል አድሀ ጠዋት ነበር። ሙጃሂዶቹ በፈረሶቻቸው ጀርባ ላይ ተፈናጠዋል። በድካም የሚንጠፈጠፈውን ላባቸውን ከግንባራቸው ላይ እየጠራረጉ አቧራና ደም ባጨማለቀው ልብሳቸው ወደ ኢድ መስገጃው ሜዳ በማቅናት ላይ ሳሉ እድሜዋ የገፋች አዛውንት ከሡልጣን መንሱር ፊት ቆማ የፈረሱን ልጓም ይዛ ከመንገዱ በማስተጓጎል እንዲህ ያለችው:-
"በዛሬው የዒድ ቀን ከእኔ በቀር ሁሉም ሙስሊሞች ደስተኞች ናቸው"
ሐጂብ መንሱር ንግግሯን ሲሰማ ደነገጠ "ለምን?" ሲልም ጠየቀ።
ዕንባ ባቀረረው ዓይኗ እየተመለከተችው እንዲህ አለችው "በረባህ ምሽግ ከመስቀል ጦረኞች ጋር ሲፋለም የተማረከ አንድ ፍሬ ሙጃሂድ ልጅ አለኝ እሱ በጠላት እስር ቤት ውስጥ ሆኖ እንዴት መደሰት ይቻለኛል?"
ሐጂብ ንግግሯን ሲሰማ ፊቱን ወደሠራዊቱ አዞረ። የፈረሱን ልጓም አጥብቆ ያዘና በጂሃድ ሜዳ የአፈር ትቢያውን ገና ላላራገፈው ሙጃሂድ፣ ከድካም ጀርባውን ላላሳረፈው ሠራዊት "ከፈረሳችሁ ላይ እንዳትወርዱ" በማለት ትዕዛዝ አስተላለፈ።
የፈረሱን ልጓም እየጎተተ ጀርባው ላይ እንደተፈናጠጠ ወደ ረባህ ምሽግ ሰራዊቱን ይዞ ገሰገሰ። የአሮጊቷን ልጅ ጨምሮ ሙስሊም እስረኞችን አስፈትቶ ከተማዋን በድል ከፍቶ ተመለሰ።
ዒዱኩም ሙባረክ
@heppymuslim29