የአሥራ ሰባት ዓመት ወጣቱ ሶሓባ ሓሪሣ አንድ ቀን ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ መጣና ‘ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ዛሬ ትክክለኛ ሙዕሚን / አማኝ/ ሆኞ አደርኩኝ ’ አላቸው፡፡
ታላቁ ነቢይ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ‘ እንዴት ባክህ ያ ሓሪሣ ! እንዴት እንዲህ ልትል ቻልክ ?’ በማለት ጠየቁት ፡፡ ወጣቱም ሁኔታዉን ሲያብራራ እንዲህ አለ ‘ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! ለሊቱን የአላህ ዐርሽ ቀርቦ የታየኝ መሰለኝ፡፡ የጀነት ሰዎች በጀነት ኒዕማዎች ( ፀጋና ድሎቶች ) ሲደሰቱ፤ የጀሀነም ሰዎች ደግሞ ከጀሀነም አሰቃቂ ቅጣት ሲጯጯሁና ሲያለቅሱ እሪታቸዉን ሲያቀልጡ የታየኝ መሠለኝ፡፡ እናም በዚህን ጊዜ አንድ ነገር ወሰንኩኝ፡፡ ለሊቱን በቂያም ( በሰላትና በዱዓዕ በመቆም ) ቀኑን ደግሞ በሲያም (በፆም) ማሣለፍ እንዳለብኝ ተሰማኝ ። ’
ነቢያችንም ሶልለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ‘ሓሪሣ ሆይ ! ለሌሎች ሰዎች ያልታየ ነገር በርግጥ ታይቶሃል፡፡ ሌሎች ሰዎች ያልተረዱትንም ነገር ተረድተሃል፡፡ በዚሁ አቋምህ እንድትፀናና እንድትዘወትር እመክርሃለሁ ፡፡ ’ አሉት
ሓሪሣ ለራሱና ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይህ ወሰለም በገባው ቃል ላይ ረግቶ የዱንያ ሕይወቱን ቀጠለ፡፡ ከእውነተኛና ጠንካራ የአላህ ባሪያዎች መካከልም ሆነ፡፡ በበድር ዘመቻ ጊዜ ሙስሊሞች ትንሹን ቁጥራቸዉን ከመጥፋት ለማዳን ብለው ከመካ ሙሽሪኮች ጋር ፍልሚያ ሲገጥሙ ሓሪሣ ገና በአሥራ ስምንት አመቱ የጦርነቱ ተካፋይ ለመሆን ቻለ። በፍልሚያው ላይ እያለም ከየት እንደተላከች ያልታወቀች አንዲት ቀስት እየበረረች መጥታ ሓሪሣ አንገት ሥር ተሰነቀረች፡፡ ሓሪሣም በዚሁ ሸሂድ ሆነ ። የሰማእትነትን ክብር ተጎናፀፈ፡፡”
የበድር ጦርነት በሙስሊሞች የበላይነት ተጠናቀቀ፡፡ የልጇን ሰማእትነት የሰማችው የሓሪሣ እናት ከፍልሚያዉ ማብቂያ በኋላ ወደ ነቢዩ እየገሰገሰች መጣችና ‘ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! ልጄ የት ነዉ ያለው?! ’ ስትል አስጨንቃ ያዘቻቸው፡፡ ‘ ያ ረሱለላህ ! የት እንደሆነ ይንገሩኝ የጀነት እንደሆነ ልደሰት የጀሀነምም ከሆነ መርዶዬን ልስማ ! ’ አለቻቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ ሰላላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሓሪሣ እናት ሁኔታ በመገረም ‘ የሓሪሣ እናት ሆይ ምን ነካሽ? ምነው ምን አገኘሽ? በጤና አይደለሽም እንዴ ! ’ ካሏት በኋላ ‘ የሓሪሣ እናት ሆይ ! ሓሪሣ ያገኘው ጀነት ብቻ አይደለም ጀነቶችን እንጂ፡፡ ሓሪሣ ያገኘው ከጀነት በደረጃ ትልቅ የሆነዉን ጀነት አል-ፊርደዉስን ነው፡፡ ’ አሏት ።
ሸይኽ ኻሊድ አር-ራሺድ እንደተረኩት
@heppymuslim29