ታላቁ ሌባ በሚል ስያሜው ድፍን ሃገር የሚያውቀው አንድ ሌባ ነበር። ታዲያ ታላቁ ሌባ የሌብነት ተግባሩን ሊፈፅም አንድ ቤት በር ላይ ደርሷል፣ አዩኝ አላዩኝ በሚል ዙሪያ ገባውን አማተረና ማንም እንዳላየው ሲያረጋግጥ ወደ ዛ ቤት ዝው ብሎ ገባ። ዳሩ ቤቱ ኦና ነው። ሚዘረፍ አንጡር ሃብት ይቅርና ሚላስ ሚቀመስ ያለበት እንኳን አይመስልም።
«ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል » እንዲሉ ሌባው ላመል ልሸው የምወጣው ባገኝ ብሎ ቤቱን ሲመነቃቅር የቤቱ ማዕዘን አቅራቢያ ሆነው ሲሰግዱ የነበሩት የቤቱ ባለቤት ሶላታቸውን ሲጨርሱ ሌባው የሚሰረቅ አንዳች ነገር አጥቶ ባዶ እጁን ሊወጣ ሲሰናዳ ያዩታል። በእድሉ ያዘነው ሌባ ለመውጣት ወደ በሩ ሲያመራ። «ባዶ እጅህን ከምትወጣ ይልቅ አንዴ በነቢዩ ላይ ሶለዋት አውርድና አስር ሀሰናት (ምንዳ)ይዘህ ውጣ»የሚልን ድምፅ ሰማ። ሌባው ድምፁን ወደ ሰማበት አቅጣጫ ሲዞር አንድ ግርማ ሞገስ የተላበሱ ሰው ያያል። የቤቱ ጌታ ናቸው። ይህ ክስተት ለታላቁ ሌባ ፍፁም እንግዳ ነው። ሊሰርቅ የመጣንና እጅ ከፍንጅ የተያዘን ሌባ ጠፍረው ወደ ህግ በሚገትሩበት አሊያም እዛው ቀጥቅጠው አፈር ድሜ በሚያስግጡበት ሀገር። ባዶ እጅህን ከምትወጣ ይልቅ እንዲህ ያለ መልካም ስራ ስራና ሰዋብ(ምንዳ) ይዘህ ሂድ» የሚልን ሰው ማግኘት የሰራቂውን ልብ ሰረቀው። በንግግራቸው የተማረከው ሌባም በሃፍረት አንገቱን አቀርቅሮ ካጠገባቸው ተቀመጠ። የቤቱ ባለቤት ታላቁ ታቢኢን ማሊክ ኢብኑ ዲናር ረዲየሏሁዓንሁ ናቸው።
እንደሚታወቀው « ማሊክ ኢብኑ ዲናር» ደግሞ የሀገሩ ታላቅ አሊም ናቸው። ከዚያም ሌባው ኢማም ሆይ! ምከሩኝ? አላቸው። እሳቸውም በዛች ንግግር አንዴ ልቡን ሰርቀውታልና ምርኮኛቸውን ይመክሩት ያዙ።
በዚህ መካከል የሶላት ወቅት ደረሰና ኢማሙ ሌባው ጋር ሆነው ወደ መስጊድ ሊሄዱ የቤቱን በር ሲከፍቱ ኢማሙን አጅበው ወደ መስጊድ ሊሄዱ የተዘጋጁት ጎረቤቶቻቸው ነበርና አይናቸው ጉድን አስተዋለ « የሀገራችን ታላቅ አሊም ከሀገራችን ታላቅ ሌባ ጋር! » ሲል አንደበታቸው ገለፀው። ኢማሙም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው « ሊሰርቀን ሲመጣ ሰረቅነው! » ታዲያ ያ ታላቅ ሌባ ከኢማሙ ስር በመክረም ታላቅ ደረሳቸው ለመሆን በቃ።
@heppymuslim29