እንዴት ሰለምክ? በማለት ነበር ጋጤዘኛው የጠየቀው። አይኑን ሰበር አንገቱን አጠፍ አድርጎ አቀረቀረና ንግግሩን ጀመረ
"የዘመን ቀመሩ ሲፈተል በ1993 ከዕለታት በአንዱ ቀን ከባለቤቴ ጋር ለመዝናናት ራቅ ብለን ተጓዝን። ዛፍ ቅጠሉን ጋራ ሸንተረሩን እያቆራረጥን አንድ መንደር ስንደርስ መሽቶ ነበርና መመለሻው መንገድ ጠፍቶን እየኳተንን በርሀብ ነደድን። ከአላፊ አግዳሚዎቹ አንዱን የሚበላ ነገር የምናገኝበትን ደህና ሆቴል እንዲጠቁመን ጠጋ ብለን ጠየቅን። አለባበሳችንን ተመለከተና እንግዳ መሆናችንን አስተዋለ"ደህና ሆቴል የለም። ምግብ ቤትም ቢሆን በዚህ ሰዓት ዝግ ነው። ወደ ከተማ ለመመለስ ደግሞ መሽቷል። ሰዓቱ የጅብ ነው። ባይሆን ወደ እኔ ቤት እንሂድና ራታችሁን በልታችሁ ታርፋላችሁ። ጠዋት ሲነጋ መንገዱን አሳያችኋለው" አለን።
ወደ ቤቱ ወሰደን። አንዲት ደሳሳ ጎጆ ውስጥ አስገባን። ጨለማ ነው። ትንሽዬዋ ጠረጴዛ ላይ ያለው ፋኖስ ይንቀለቀላል። አምስት ሕጻናትና ሁለት አዛውንቶችን ከአንድ ጥግ ተቀምጠዋል። ግርግዳ ማገሩን እያየን ቀለል ያለ መጠነኛ እራት አቀረበልን። በልተን ስንጨርስ "አንተና ሚስትህ እዚህ አልጋ ላይ በነፃነት እረፉ። እኔና ቤተሰቤ ሌላ ክፍል ውስጥ እንተኛለን" በማለት ተሰናበተን።
ለሊቱን በበቂ ሁኔታ ተኛን። ማለዳ ጎህ ከመቅደዱ በፊት ነቃን። ላደረገልን መልካም ነገር ልናመሰግነው ከተኛንበት ክፍል ለባብሰን ወጣን። ሌላ ክፍል ግን አላገኘንም። አይኔን ወርውሬ ስመለከት ሰውየው አንዲት ዛፍ ላይ ተሰቅሏል። ከስሩ ደግሞ ቤተሰቦቹ ተጎዝጉዘዋል። ህፃናቶቹም ኩርምት ብለው ሽፋሽፍቶቻቸውን ከድነዋል።
ባለቤቴ በሁኔታው አለቀሰችች። በዚያ ቀዝቃዛ አየር እንዴት ለማያውቁት ሰው ውጪ ማደርን ምርጫቸው ያደርጋሉ። እስልምና ለእንግዳ ያለው ቦታ ገረመን። "ይህ የምናየው እስልምና ከምንሰማው ፍፁም ይለያል" ተባባልን። ወደሰውየው እየተንጠራራሁ እስልምናን እንዴት ማወቅ እችላለሁ በማለት ጠየቅኩት።
"የቁርአን ትርጉምና አንዳንድ መፅሐፎችን ገዝተህ አንብብ" አለኝ የዛፉ ቅርንጫፍ ላይ ተጋድሞ ቁልቁል እየተመለከተኝ።
ወደ ሀገሬ እንደተመለስኩ ስለ እስልምና ለማወቅ በርካታ መፅሐፍትን ሸማመትኩ። ለተከታታይ ሁለት ወራት በጥሞና ተቀምጬ አነበብኩ። ከአላህ ሌላ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን በእውነት መሰከርኩ። እኔን ምክንያት አርጎ ከአንድ ሺህ የሚበልጡ ሰዎች እስልምናን ተቀበሉ። አሁን በሀገረ ሩማንያ እስላማዊ ማዕከል እየገነባሁ ነው። እስልምናን በአለም ላይ ለማስፋፋት ኢንሻ አላህ እተጋለሁ።
በመልካም ስነ ምግባር ዳዕዋ ማድረግ እንዲ ነው።
@heppymuslim29