እጅግ አስተማሪ ታሪክ
አንድ ሰው በባህር ላይ በመጓዝ ሳለ መርከቡ ትገለበጥበታለች። ከዛም ከመስጠም ለመዳን ወደ ባህሩ መሀል በሚገኝ ደሴት ይወጣል። አላህ በዚ ደሴት ላይ ትኩስ ምንጭ ያፈልቅለታል፤ ዛፍንም ያበቅልለታል። ይቺ ዛፍ ጠዋት ማታ ታፈራለች እሷን ይመገባል።እናም ራሱን ለዒባዳ(አምልኮ) ሰጠ። አላህንም ሲያመልክ ኖረ። በሱጁድ እያለ እንዲወስደውም ይማፀነዋል። አላህም ይቀበለዋል በኢባዳ እዚች ደሴት ላይ እድሜውን ጨርሶ ሱጁድ ባደረገበት ወደ ዘላለማዊው ሀገር ይሄዳል። ጌታውንም በተገናኘ ጊዜ, አላህ:-
"ጀነትን በኔ እዝነት ግባ" ይለዋል።
"ኧረ ጌታዬ ስራዬስ" ብሎ ይመልሳል። ያሁላ አመታት እድሜን ሙሉ የተገዛውትስ ማለቱ ነው።
አላህም ለመላኢኮች ሂሳብ አስቡለት ይላቸዋል፤ ይተሳሰባል። የሱ ኢባዳ የዓይንን ፀጋ እንኳ የማትስተካከል ሆኖ አገኙት። ሌሎቹ ፀጋዎቹ ደሞ ሚዛን ደፍተው አላህ ለመላኢኮች ጀሀነም አስገቡት አለ። ያኔ ይህ ባሪያ:-
"ጌታዬ ሆይ! ጀነትን በእዝነትህ አስገባኝ?" ይላል። አላህም "ጀነትን በእዝነቴ ግባ ይለዋል፤ ጀነት ይገባል።
በዚ ታሪክ የሰው ልጅ ስራ ትንሽ መሆኑን እንገነዘባለን። የፈለገ እድሜውን በኢባዳ ቢጨርስም የአላህ እዝነት ከሌለው ባዶ ነው። ለዚህም ሲባል ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ትክክለኛ በሆነ ሀዲስ እንዲህ ይላሉ:-
❝ ከናንተ ውስጥ አንደኛቹም በስራው ጀነት አይገባም! ❞ ሰሃቦችም በመገረም "አንተም ብትሆን!?" ሲሉ ጠየቁ። እሳቸውም:-❝ አዎ እኔም ብሆን ;አላህ በእዝነቱ ችሮታው ቢሸፍነኝ እንጂ ❞ አሉ
🤲አላህ በእዝነቱ ጀነት ያስገባን!🤲🤲
© ሂዳያ መልቲሚዲያ

አሚን በሉ
© ሂዳያ መልቲሚዲያ