እነሆ ጊዚያችን ጠብቀን ተከስተናል☺️
#Reading_challenge
ዛሬ ደሞ ለየት ያለ መፅሀፍ ነው ምጋብዛችሁ
የመፅሀፉ ስም - ጀነት መግባት ትፈልጋለህ? እና ሌሎች ኢስላማዊ ፅሁፎች
ፀሀፊ - ፀሀፊወቹ ብዙ ስለሆኑ አሳታሚውን ብናገር ይሻላል😂
አሳታሚ- ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የመፅሀፉ ይዘት -
መፅሁፉ ሶስት የተለያዩ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ፤ ሁለቱ የትርጉም ስራወች ሲሆን አንዱ የጥንቅር ስራውን የሰራው ሙሀመድ ሰኢድ(ABX) ነው።
በመጀመሪያ ላይ እምታገኙት "ጀነት መግባት ትፈልጋለህ?" እሚሰኘው በ ማጂድ ኢብን ኸንጀር አልባንካኒ ፤ አቢ አነስ አል ኢራቂይ የተዘጋጀ ሲሆን አብዱልፈታህ ሙሀመድ ወደ አማርኛ መልሶታል። እዚህኛው ክፍል ላይ ጀነት ምን እንደሆነ በማብራራት እሚጀምር ሲሆን ሙስሊሞች ጀነት ውስጥ ቤት ይገነባላችኋል ተብለው የተላለፉትን ሀዲሶች እና ትንተናወችን ሸክፎ የያዘ ነው።
ሁለተኛው ደግሞ ሙሀመ ሰኢድ ያጠናቀረው ሲሆን ፤ ንፁህ ቀልብ ያስፈልገናል ሲል ሰይሞታል። ቀልባችን ንፁህ ለማድረግ እሚጠቅሙ ፅሁፎችን "ፌርማታ" ብሎ በመሰየም አስራ አራት ፌርማታ ፅሁፎችን አቅርቧል።
የመጨረሻው የኢብነል ቀይምን ኪታብ በአቤል ሀይሌ ወደ አማርኛ መልሶ ስሜትን መከተል ብሎ አቅርቦታል። ስሜትህን ለምን መከተል እንደሌለብህ እያብራራ ብዙ ነጥቦችን ያነሳል።
የገፅ ብዛት - 123
ከመፅሀፉ የተወሰደ -
" እንደ አቢ ደምደም መሆን እሚችል ማን ነው?
የሚለው የብዙወቻችን ጥያቄ እንደሆነ እገምታለሁ። ተከተሉኝማ ልንገራችሁ ። አቡዳውድ እና ጦበራኒ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ ረድየሏሁ አንሁ እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) አንድ ቀን ለሰሀቦቻቸው 'ከናንተ መካከል እንደ አቢ ደምደም መሆን እሚችል ማን ነው!' በማለት ጠየቋቸው። ሰሃቦችም 'የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አቢ ደምደም ማን ነው?' በማለት በግርምት ጠየቋቸው 'እሱማ' አሉ ነብያችን 'እሱማ ባነጋ ቁጥር ጧት ላይ በመነሳት የሚል ሰው ሲሆን የሚሰድቡትን መልሶ አይሳደብም፤ የበደሉትን አይበድልም፣ የመቱትንም አይመታም' አሏቸው።" ገፅ ፥55
@ibnuhasen
T.me/ibnuhasen