እናስተነትን ዘንድ
እነሆ ተፈኩር እናድርግ ብለን ሀሳቡን ጀምረን አሁን ማስቀጠልን ወደድጅን። እንደ ሙስሊም አካባቢያችን ያሉ ነገሮችን እንስተነትን ዘንድ የተወደደ ነውና አካባቢያችን ስላሉ ነገሮች እያነሳን እንወያያለን።
ለዛሬ የመረጥንላችሁ አላህ በስሟ አንድ የቁርአን ምእራፍ የሰየመላትን አንድ የነፍሳት ዝርያ የሆነውን ጉንዳንን ነው።
ጉንዳን በጣም ጠንካራ ከሆኑ ነፍሳት እሚመደብ ነው። የክብደቱን 20 እጥፍ መሸከም ይችላል። ይህ ማለት አንድ ወጣት እንደ ጉንዳን ጠንካራ ቢሆን አንድ የቤት መኪናን ሊሸከም ይችላል ማለት ነው።
ጉንዳን በዳይነሶሮች ጊዜ ጀምሮ የነበረ እንደሆነ ሳይንቲስቶች ያትታሉ። ይህም ማለት ከ 100 ሚልዮን አመት በፊት ማለት ነው። ይህ ነፍሳት ከ 12,000 አይነት በላይ ዝርያወች ያሉት ነው ። ምድር ላይ እሚርመሰመሱ ብዙ ጉንዳኖችን አይተው ይሆናል። እስኪ እንጠይቅወ ምድር ላይ እሚሄዱት ጉንዳኖች ሴት ወይስ ወንድ ?!
ብዙ አያስቡ ምድር ላይ እሚያዩኣቸው ተራማጅ ጉንዳኖች በሙሉ ሴቶች ናቸው። ወንድ ጉንዳኖች ሁሉም መብረር እሚችሉ ናቸው።ቤትዎ ቁጭ ብለው ከየት መጣ ሳትሉት አንድ መንጋ ጉንዳን በሰልፍ ቤትወን ሊወሩት ይችላሉ። "ይህ ሁሉ ጉንዳን ከየት መጣ?" ብለው ከተገረሙ እንንገርዎት ። ጉንዳኖች በየቦታው ምግብ እሚፈላልግ ወታደር ይልካሉ። ጉንዳኖች ጣፋጭ ነገርን ይወዳሉ። በርግጥ እማይበሉት ነገር የለም ። ጣፋጭ ነገር ግን ምርጫቸው ነው። ያ ወታደር ቤት ውስጥ ምግብ ካገኘ ሌሎች ወታደሮችንም ይጠራና ወደ ቤትወ ዘመቻ ይከፍትበዎታል ማለት ነው።
እዚህ ምድር ላይ እስከ አስር ኳድሪሊዮን የሚደርሱ ጉንዳኖች አሉ። በቀላሉ መራባት ይችላሉ። ሴቷ ጉንዳን ወይም ንግስቲቱ ብዙ አመት መኖር ስትችል በሚልዮን የሚቆጠር ጉንዳኖችን መፈልፈል ትችላለች።
ከሰወች ጋር በ ratio ስናስቀምጥ ለአንድ ሰው አንድ ሚልዮን ጉንዳን ማለት ነው። ጉንዳኖች ይታመማሉ። ባውቨሪያ ባሲያና የተሰኘውን የፈንገስ ዘር ከነኩት ዘሩ ሰውነታቸው ላይ ተራብቶ ህመም ላይ ይጥላቸዋል። በርግጥ ጉንዳኖች ሀኪም አላቸው። ይህን ፈንገስ ግን ፈንገስን እሚገድል ጥቂት ኬሚካል ከጠጡ ይድናሉ።
ጉንዳኖች በግዛት ጦርነት ይገጥማሉ። በጦርነቱ ወቅት የቆሰሉት ጉንዳኖች የእርዳታ signal (ምልክት) ይልካሉ። ወዲያው ሀኪም ጉንዳኖች ደርሰው ያክሟቸዋል። መዳን እማይችሉ ከሆኑ ግን ሀኪሞች አይረዷቸውም።
እንደ reddit ገለፃ ከሆነ ጉንዳኖች ሲሞቱ የሰው ልጅ ሊሰማው የሚችልን ጩኸት ይጮሀሉ ወይም ድምፅ ያሰማሉ።
ለዛሬ በዚህ እናበቃለን ሌላ ጊዜ በሌላ ፍጥረት እንገናኛለን።
@ibnuhasen
T.me/ibnuhasen