የሆነ ትልቅ ሰው ገብያ ላይ ተገናኝተን ማውራት ጀመርን።
ሰውየው ጋር ትንሽ ካወራን በኋላ እንዲህ አለ ፡- "እኔ ወደ ሻሸመኔ የሄድኩት በ 67 (1967) ነው። የዛኔ ወታደር ነበርኩ። ለግዳጅ በዛው እንደሄድኩ ኑሮየን መሰረትኩ። ልጆች ወልጃለሁ አካባቢው ላይ ሰላም ነበርን ግን ድንገት ነገሩ ሁላ ተቀያየረ አፈራውት ያልኩት ሀብት እና ንብረቴ ወደመብኝ። ለብዙ ግዜ በእርዳታ መኖር ቻልኩ ግን መዝለቅ አልቻልኩም። አሁን ይሄው እንደምታየኝ እዚህ መጥቼ እንደ አዲስ ኑሮ መስርቼ መኖር ጀምሪያለሁ። ግን ከብዶኛል። አእምሮየ ረፍት አጥቷል። በቃ ጭንቃላቴ ላይ የተቀረፀው ረብሻ እና ማፈናቀሉ። " ሰውየው መቀጠል አቃተው።
እኔም "እኔም ጂማ ነበርኩ ። የጅማ ሰው ጥሩወች ናቸው። አንዴ በብሄር ምክንያት ግቢውን ለቅቈ እንድወጣ ተደርጌ ነበር። እና እሚሰማህ ያለውን ነገር በትንሹም ቢሆን ይገባኛል የሆነው ነገር ያሳዝናል አይዞን ጋሼ!" ብየ ሸኘኋቸው።
ሙሉ ኢትዮጵያ በዘረኝነት የተበከለች ያህል ይሰማኛል። "የተፋዋ ምድር" እየተባለች ስሰማ ያደግኩት ነገር ሁሉ ውሸት እንደሆነ አወቅኩ። አንዳንዴማ "ኢትዮጵያ የተስፋዋ ሳይሆን የክፋት ምድር ናት" እያልኩ አስባለሁ።
@ibnuhasen