እንኳን ለ85ኛ ዓመት የአገው ፈረሰኞች በዓል አደረሳችሁ!
-----
በዓሉ ጥር 23 በየዓመቱ በእንጅባራ ከተማ በድምቀት ይከበራል።
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቅርስነት እንዲመዘገብ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል። ከእነዚህም ውስጥ አሰፈላጊ መረጃዎችን አደራጅቶ በመስጠት በቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የአገው ፈረስ ባህል " The Agaw Horse Culture" በሚል ስያሜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ቅርስ ሆኖ በ2015 ዓ.ም ተመዝግቧል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በ UNESCO እንዲመዘገብ ከተለያዩ ተቋማት እና ምሁራን ጋር በመሆን አስፈላጊ መረጃዎችን በማደራጀት ላይ ይገኛል። በተጨማሪም በዓሉ በየዓመቱ በድምቀት እንዲከበር በማድረግ አውደ ጥናቶችንና የተለያዩ የባህል ፌስቲቫሎችን እያካሄደ ይገኛል።
በዚህ ዓመትም ጥር 22/2017 ዓ.ም የአገው ባህላዊ ቅርሶች በሆኑት "አሱሪቴ" ባህላዊ ትውን ጥበብ እና "ባኩሳ" ብሔራዊ ፓርክ ላይ በአገው ጥናት ኢንሲቲትዩት አማካኝነት ሲምፖዚየም ተዘጋጅቷል።
በድጋሚ መልካም በዓል!
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ!