የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈጻጻም ሪፖርት አጸደቀ።
የካቲት 7/2017 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርዱ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲን እና የሱታና የንግድ እና የማማከር ስራዎች ድርጅት የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፓርት ገምግሞ አጽድቋል።
የዩኒቨርሲቲውን የግማሽ ዓመት ሪፖርት በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ስትራተጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ በአቶ ልንገረው አትንኩት እንዲሁም የሱታና ንግድ እና ማማከር ሥራዎች ሪፓርት በኢንተርፕራይዝ ስራ አስኪያጅ በአቶ ሀብታሙ አበራ የቀረቡ ሲሆን በሪፓርቱ በዩኒቨርሲቲው እና በንግድ ድርጅቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ክንውኖች፣ በአፈጻጸም የታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ተዳስሰዋል። የቀረበውን ሪፓርት ተለትሎ ከቦርድ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የእንጅባራ ዪኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና የሰራ አመራር ቦርድ ጸሐፊ ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ መልስ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ቢቂላ ሁሬሳ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በተሰጡት ተልዕኮዎች ላይ ተመስርቶ በግማሽ ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራትን አድንቀው ስራዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መደገፍ፣ የማህበረሰቡን ችግር በምርምር መፍታት እና ከሀገር ውስጥና ከውጭ አጋር አካላት ጋር ጠንካራና ውጤታማ ግንኙነት መመስረት፣ የምርምር ጣቢያዎችን ማስፋፋት በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ቦርዱ የቀረበውን የ2017 ግማሽ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሞ አጽድቋል።