"..ሂጃብ አልከለከልንም ጸጉራቸውን እንዳይሸፈናፈኑ ነው የከለከልነው.."
- የአክሱም አሉሙናይ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ብርሃኔ
በአክሱም ከተማ ሴት ተማሪዎች ፀጉራቸውን እንዳይሸፍኑ የሚከለክል መመሪያ መኖሩን የአክሱም አሉሙናይ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ብርሃኔ ገለፁ!
በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሳችሁ መማር አትችሉም መባላቸው ይታወቃል።
ይህንኑ ጥያቄ ይዘን ሂጃብ ለብሶ መማር ክልከላ ከተደረገባቸው ትምህርት ቤቶች አንዱ ወደ ሆነው የአሉሙናይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ርዕሰ መምህር አቶ ብርሃኔ ጋር ሀሩን ሚዲያ ባደረገው የስልክ ቆይታ ርዕሰ መምህሩ ምንም እንኳን ሂጃብ ብለው በግልጽ ባይናገሩም ሴት ተማሪዎች ፀጉራቸዉን ተሸፋፍነው መማር አይችሉም የሚል መመሪያ እንዳላቸዉና በመመሪያው መሰረት ፀጉር መሸፋፈኛና ጌጣጌጥ ለብሶ መማር አይቻልም በማለት አጭር ምላሽ ሰጥተውን ስልኩን ዘግተውብናል።
ርዕሰ መምህሩ ምንም እንኳን ሂጃብ መልበስ አልከለከልንም ቢሉም ፀጉራቸውን ሸፍነው የሚማሩት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች እንደሆነም ይታወቃል።
በዚህ ጉዳይ ወደ አክሱም ከተማ ከንቲባ ወደሆኑት አቶ አበበ መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ የእጅ ስልካቸው ላይ ብንደውልም ስልካቸው ባለመመለሱ ምክንያት ሀሳባቸውን ማካተት አልቻልንም።
© ሀሩን ሚዲያ
#ᴊᴏɪɴ_and_share_ᴏᴜʀ_ᴘᴀɢᴇ
@islam_in_school