ISLAMIC SCHOOL️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ኢስላም በትምህርት ቤት

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


"ከትምህርት እና ሃይማኖታችሁ አንዱን ምረጡ" የአክሱም ከተማ ፖሊስ ለአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች የሰጣቸው ማስጠንቀቂያ

በአክሱም ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ትምህር ቤት መግቢያ በር ላይ BBC News Amharic ያነጋገራቸው ተማሪዎች እና ወላጆች ኃይማኖታዊ መብታችንን በመጠየቃችን ለእንግልት እና እስር ተዳርገናል ይላሉ።

ወ/ሮ ናአራይሚ መሐመድ ልጃቸው ከትምሕርት ቤት ተወስዳ ስለመታሰሯ ተናግረዋል።

ልጃቸው ትምሕርቷን ወይም ኃይማኖቷን እንድትመርጥ በፖሊስ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

"'ልጆቻችሁ የትምሕርት ቤቱን ህግ አክብረው ይመለሱ ወይም ወደ መስጊድ ይሂዱ፤ አንዱን ምረጡ' አሉን" ብለዋል።

@islam_in_school


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የአክሱም ከተማ ፖሊስ ሒጃብ ለብሰው ለማማር ወደ ትምህርትቤት የሄዱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት

"ለምን ሒጃብ ለብሳችሁ ለማማር መጣችሁ?" በሚል ወደ ፖሊስጣቢያ በመውሰድ ተማሪዎቹን ሲያስፈራሩ የሚያሳይ በድብቅ የተበረፀ አጭር ቪድዮ ደርሶናል።

ተማሪዎቹ የለበሷት ስካርፍ ሒጃብ ተመልከቱ። It's just a piece of cloth እኮ።

Uma

@islam_in_school


መጅሊስ መግለጫ አውጥቷል‼

«በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚፈፀሙትን የመብትና የሃይማኖት ጥሰቶችን በሚመለከት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!»

@yasin_nuru_hadis


«የአክሱም እህቶቻችን ዛሬም ወደ ትምህርታቸው መመለስ አልቻሉም። ዛሬም ከየት/ቤቱ በራፍ መግባት ተከልክለው ወደየቤታቸው ተደብድበው ተመልሰዋል። ሁሉም ያየውን የትናንቱን የዶ/ር ጉዕሽ ደብዳቤ «አልደረሰንም፣ አንቀበልም!» ብለው ከልክለዋቸዋል።»

@islam_in_school


ከ1400 ዓመታት በፊት ትግራይ ውስጥ ከዛሬው የተሻለ የሃይማኖት ነፃነት ነበር።

መካ ውስጥ በገዛ ወገኖቻቸው የተገፉ የተንገላቱ ሙስሊሞች ባህር አቆራርጠው የተሰደዱት ወደ ሐበሻ ነበር። "እዚያ ከሱ ዘንድ ማንም የማይበደልበት ፍትሃዊ መሪ አለ" ተብሎ በነብዩ ﷺ የተመሰከረለት ድንቅ መሪ ነበር፣ ነጃሺ። ያኔ በግዛቱ ውስጥ ማንም እንዳይነካቸው ዋስትና ሰጥቷቸው ነበር ለስደተኛዎቹ ሙስሊሞች።

ዛሬ ከ1400 ዓመታት በኋላ በ21ኛው ክ/ዘመን ሙስሊም ለጋ ልጆች፣ ከሩቅ የመጡ እንግዶች ሳይሆኑ ተወላጆች፣ ሻሽ ካልጣላችሁ ተብለው በእምነታቸው ተለይተው ከትምህርት ገበታ ተገፍተዋል።

ይበልጥ መሰልጠን ሲገባ ጭራሽ እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ መሄድ የሚያሳዝንም፣ የሚያሳፍርም፣ የሚገርምም ነው።

@islam_in_school


"...በደብዳቤው መሠረት በዚህ ሶስት ቀን ውስጥ ተማሪዎች ተመልሰው ችግሩ ካልተፈታ ከህዝባችን ጋር በመመካከር የምንወስዳቸውን ሰላማዊ የትግል እርምጃዎች እናሳውቃለን.."

- የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ አደም አብዱልቃድር እና የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሐጂ ሙሓመድ-ካሕሳይ ከተበዳዮች ጎን ለቆሙት ሁሉ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ይህ በትምህርት ቢሮ የተፃፈው ደብዳቤ በሶስት ቀናት ውስጥ ተተግብሮ የሂጃብ ክልከላው በአዎንታዊ መልኩ ካልተፈታ በቀጣይ እንደ እስልምና ጉዳዮች ከህዝቡ ጋር በመመካከር የሚወሰዱ ሰላማዊ እርምጃዎች እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

የትምህርት ቢሮ ችግሩ ይፈታ በማለቱ መግለጫ መስጠታችን አሁን ላይ ትርጉም የለውም ያለው ከፍተኛ ም/ቤቱ እስካሁን በትግል እና ትዕግስት እንደመጠበቃችን መጠን ይህ ደብዳቤ ከተፃፈ ጋዜጣዊ መግለጫው አስፈላጊ አለመሆኑን ገልጸዋል። ነገር ግን በዚህ ሶስት ቀን ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ገበታቸው ካልተመለሱ ከህዝባችን ጋር በመመካከር የምንወስዳቸው ሰላማዊ እርምጃወች እናሳውቃለን ሲሉ ገልጸዋል።

@islam_in_school


የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ በአክሱም ትምህርት ቤቶች የተጣለው የሒጃብ እገዳ ከመመሪያ ውጪ መሆኑን ገልጿል። ነገር ግን ደብዳቤው ላይ ሕግ እና መመሪያ በመጣስ በአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥሰት በፈፀሙ አካላት ተጠያቂ እንደሚሆኑ የሚጠይቅ የለውም። ተማሪዎቻችን ሒጃባቸውን ለብሰው ይማራሉ ወንጀሎችን ተጠያቂ እስኪሆኑ እንታገላለን። ሒጃብ መሰል (መብት) እዩ (ነው)


@islam_in_school


ስለ ተማሪዎች የአለባበስ ስርዓት

Tetemke Brhan Tesha

ተጠምቀ ገብረእግዚአብሔር ይናገራል፦

"በዚህ ሰአት በትግራይ ክልል ተማሪዎች ጩቤ ይዘው ወደ ትምህርት የሚሄዱበት፤  በአንድ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከሰአት ክፍለጊዜ ላይ ጠጥተው ሰክረው እየመጡ ስላስቸገሩ  "ከ6ኛ-8ኛ ክፍል ያሉት ተማሪዎች በጧት ክፍለ ጊዜ ላይ ብቻ እንዲማሩ የተደረገበት ሁኔታ ፤  መምህር እያስተማረ ፊቱን ወደ ሰሌዳ ሲያዞር ድንጋይ የሚወረወርበት፤ ተማሪ ያልሆኑ ጎረምሶች መምህር ክላስ ዘግተው የሚደበድቡበት፤ ሴት ልጆች ወደ ትምህርትቤት ብለው ወጥተው በየጫካው እና በየሰፈሩ እድሜአቸውን በማይመጥን አስነዋሪ ስራ ላይ የሚውሉበት...አረ ስንቱን ልጥቀስ! ባሉበት ወቅታዊ ክልላዊ ሁኔታ እንዲህ አይነት [ሒጃብ የለበሱ] ሴቶች እንደወንጀለኛ በተቆጠሩ ነበር?

📍 ጉዳዩ ሌላ ነው። ይህ የትግራይ ስቃይና ሕመም ቀጣይነት ማሳያ እንደሆነ ግልፅ ሊሆን ይገባል። ይህ የሃይማኖት ሽፋን በማድረግ ትግራይ ወደ ሌላ አዘቅት ለመውሰድ የሚደረግ ጥረት ስለሆነ ካሁኑ በቃ ሊባል ይገባል።"

@islam_in_school


አሁን የደረሰን መረጃ
ሒጃብ ለብሰን ነው የምንማረው ካሉ 159 የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች መካከል 20 ታስረው እንደነበረ ለማረጋገጥ ተችሏል። 17ቱ ከሰዓታት በፊት ተፈተዋል። ሶስቱ (3ቱ) በእስር ላይ ናቸው።

@መሀመድ ሀጎስ

@islam_in_school


በአክሱም ከተማ በሒጃብ ምክንያት ከትምህርት ገበታ የታገዱ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከ150 በላይ መሆናቸው ተገለፀ!

በዛሬው ዕለት ሰኞ ታሕሳስ 21/2017 አዲስ ነገር ይኖራል ብለው የጠበቁ 159 የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ተፈታኝ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሒጃባቸውን ለብሰው ወደ የትምህርት ቤቶቻቸውን ሄደው የነበረ ቢሆንም ዛሬም ሒጃቦችሁን አውልቃችሁ ካልሆነ መግባት አትችሉም ተብለው እንደተመለሱ ተማሪዎቹ ለሀሩን ሚድያ ገልፀዋል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ በበላ ሀገሪቱ ከ499 ሺህ በላይ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል ያለ ቢሆንም በአክሱም ከተማ ግን አንድም ሙስሊም ሴት ተማሪ ምዝገባ አለማድረጉን ተማሪዎች ተናግረዋል።

የ12ኛ ክፍል የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና ፎርም መሙያ የቀሩት ቀናት ጥቂት በመሆናቸው የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

© ሀሩን ሚድያ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ ሌሎችም ባጠቃላይ እያንዳንዱን ሶላት በወቅቱ ለመስገድ የሚቸገሩበት ሁኔታ ከገጠማቸው ዙህርን እና ዐስርን በአንዱ ወቅት፤ መግሪብን እና ዒሻእንም እንዲሁ በአንደኛው በሚመቻቸው ወቅት መስገድ ይችላሉ። መንገደኞች ባይሆኑ እንኳ ማለቴ ነው። ስለዚህ ለምሳሌ አንድ ተማሪ ከመግሪብ ሶላት ቀደም ብሎ 12:00 ላይ ለፈተና እንዲቀመጥ ቢገደድና የፈተናው ጊዜ እስከ ዒሻእ ወቅት የሚረዝም ከሆነ ፈተናውን ካጠናቀቀ በኋላ በመጀመሪያ መግሪብን ይሰግዳል። ካሰላመተ በኋላ እንደገና ዒሻእን ይሰግዳል። ይሄ ሶሒሕ ሐዲሥ የመጣበት ነው። ለተጨማሪ የሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚንን ድምፅ አያይዣለሁ።

ተጨባጭ ምክንያት ካልገጠመው ግን ሁሉንም ሶላት በወቅቱ ነው መስገድ ያለበት። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ إِنَّ ٱلصَّلَوٰةَ كَانَتۡ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِینَ كِتَـٰبࣰا مَّوۡقُوتࣰا }
''ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና።" [አኒሳእ፡ 103]


@islam_in_school


ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ 👐


በዓለማችን ታዋቂውና የተሻለ የሚባለው የእንግሊዝኛ ቁርኣን ትርጉም Sahih International ሲሆን የተዘጋጀውም በ3 ሰለምቴ አሜሪካውያን ሴቶች ነው።

♦️የመጀመሪያዋ ❝ኤምሊይ አሳሚ❞ ወይም አሚናህ ዑሙ-ሙሐመድ ትባላለች። የተወለደችው ካሊፎርንያ ሲሆን ቤተሰቦቿ እምነት የለሾች ናቸው። ኢስላም ሴቶችን እንደሚጨቁን ስትሰማ ለማጣራት ቁርኣንን ማንበብ ጀመረች። ከዚያ በወቅቱ በአሜሪካ በቂ የኢስላም መጽሐፍ ስላልነበሩ ወደ ሶርያ በመሄድ ከደማስቆ ዩኒቨርስቲ ዐረቢኛን አጥንታ ክሱ ቅጥፈት መሆኑን ስታረጋግጥ ኢስላምን ተቀበለች። ከዚያም በ1981 ወደ ሳዑዲዓረቢያ ሄደች።

♦️ ሁለተኛዋ ❝ሜሪ ኬኔዲ❞ የተወለደችው በኦርላንዶ ሲሆን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምሩቅ ናት። ቤተሰቦቿ ክርስቲያኖች ናቸው። በኋላም ወንድሟ ኢስላምን ሲቀበል በእሱ ምክንያት በ1985 ኢስላምን ተቀበለች። ከዚያም በ1987 ወደ ሳዑዲዓረቢያ ሄደች።

♦️ ሶስተኛዋ ❝አመቱላህ ባንትሌይ❞ ስትሆን የካቶሊክ እምነት ተከታይ የነበረችና ከሚኒሶታ ዩኒቨርስቲ የቢዝነስ ማኔጅመንት ምሩቅ ናት። የሰለመችው በ1986 በዓለምአቀፍ የሙስሊም ተማሪዎች ማህበር አማካኝነት በ20 ዓመቷ ነው። ከዚያም በ1987 ወደ ሳዑዲዓረቢያ ሄደች።

👉 በ1990 አካባቢ በሳዑዲ ሳሉ በአጋጣሚ ተገናኝተው ተዋወቁ። በዚያው ሰሞን ሙስጠፋ የተባለ ሰው ቁርኣንን በቀላል እንግሊዝኛ ለመተርጎም ጀምሮት እንደሞተ ሲሰሙ ስራውን ለመጨረስ ተነሱ። በዚህም ከዚያ በፊት ፍፁም አስበውት የማያውቁትን የቁርኣን ትርጉም በ1994 ጀምረው በሶስት ዓመቱ በ1997 አጠናቀቁት።

በኋላም መጽሐፉ በዓለም ላይ ቀላሉና የተሻለው የእንግሊዝኛ ትርጉም ለመሆን የበቃ ሲሆን ሶስቱም በህይወት በመኖራቸው የስራቸውን ፍሬ ለማየት ታድለዋል። ዑሙ-ሙሐመድ ኤምሊይም ከዚያ በኋላ ከ80 በላይ ኢስላማዊ መጽሐፍት አዘጋጅታለች። እነዚህ እህቶችም ኢስላም በቁርኣን ጭምር የሴቶችን እውቀት የሚተማመን መሆኑን ማሳያ መሆን ችለዋል።

ሰልማን

@islam_in_school


በዛሬው እለት በ6 ኪሎ ጀመዓ አዘጋጅነት በአል-አቅሷ መስጂድ በተካሄደው የዳዕዋ ፕሮግራም ላይ ከተማሪዎች ለተነሱ ጥያቄዎች የተመለሱ መልሶች

🎙 በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር


@islam_in_school


#ፈጅር

ለፈጅር ሰላት ወደ መስጂድ ስትገባ ጥቂት ሰጋጆች ስትመለከት ዕወቅ ... አላህ ነው ከእነርሱ(ከባሮቹ) እንድትሆን የመረጠህና አመስግን!!

የፈጅርን ሰላት በጀምዓ ለመስገድ ስለበቃህ እንኳን ደስ አለህ!
በአላህ ጥበቃ ውስጥ ነህ .... በእውኑም በመንፈስም ቤትህ ከሌሎች ቤቶች ብርሀን ነው።

«ጌታዬ ሆይ ጉዳዮቼን ወደ አንተ አቀርባለሁ፣ እንደምታሳካልኝም ተስፋ አደርጋለሁ!» ከሚሉ ባሮቹ ውስጥ ያድርገን!!


@islam_in_school


በቻይና በተካሄደ አለም አቀፍ የሮቦ ሮቦቲክስ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል የተወዳደረው ተማሪ አክረም ሙሀመድ 3ኛ በመውጣት የዋንጫ አሽናፊ ሆነ!

- ሀሩን ሚዲያ፣ ታህሳስ 17/2017

በአዲስአበባ የሚገኘው መወዳ ትምህርት ቤት የ7ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ተማሪ አክረም ሙሀመድ በቻይና በተካሄደ የአለም አቀፍ የሮቦ ሮቦቲክስ ውድድር 3ኛ ደረጃን በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል።

ከ36 በላይ የአለም ሀገራት ተሳታፊ በነበሩበት ውድድር ላይ ጠንካራ ፉክክር እንደነበር የገለፀው ተማሪ አክረም ሙሀመድ በአላህ እገዛ ማሸነፍ ችያለሁ ብሏል።

ተማሪ አክረም በውድድሩ ላይ የሀገሩን ሰንደቅ አላማ ከፍ በማድረጉ በሚማርበት መወዳ ትምህርት ቤት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ተማሪ አክረም ገና ከህፃንነቱ ጀምሮ ለፈጠራ ስራዎች ልዩ ቦታ እንዳለው የገለፁት ወላጆቹ በቻይና በነበረው አለም አቀፍ የሮብ ሮቦቲክስ ውድድር ወቅት የነበረው የምግብ አለመቸት እና የአየር ፀባይ መቀያየር ጫና ባይፈጥርበት 1ኛ ሊወጣ ይችል እንደነበር ገልጸዋል።

ለፈጠራ ስራ ልዩ ቦታ እንዳለው የገለፀው ተማሪ አክረም ሙሀመድ ወደፊት ሀገሩን የሚያስጠራ ኡማውን የሚጠቅም ስራ የመስራት ራዕይ እንዳለው ገልጿል።

- ሀሩን ሚዲያ በዚህ ዙሪያ ከተማሪ አክረም፣ ከቤተሰቦቹ እንዲሁም ከመምህራኖቹ ጋር ቆይታ በማድረግ ያሰናዳውን ዝግጅት በቅርቡ ወደእናንተ ያደርሳል!

© ሀሩን ሚዲያ

@islam_in_school


"..ሂጃብ አልከለከልንም ጸጉራቸውን እንዳይሸፈናፈኑ ነው የከለከልነው.."

- የአክሱም አሉሙናይ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ብርሃኔ


በአክሱም ከተማ ሴት ተማሪዎች ፀጉራቸውን እንዳይሸፍኑ የሚከለክል መመሪያ መኖሩን የአክሱም አሉሙናይ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ብርሃኔ ገለፁ!

በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሳችሁ መማር አትችሉም መባላቸው ይታወቃል።

ይህንኑ ጥያቄ ይዘን ሂጃብ ለብሶ መማር ክልከላ ከተደረገባቸው ትምህርት ቤቶች አንዱ ወደ ሆነው የአሉሙናይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ርዕሰ መምህር አቶ ብርሃኔ ጋር ሀሩን ሚዲያ ባደረገው የስልክ ቆይታ ርዕሰ መምህሩ ምንም እንኳን ሂጃብ ብለው በግልጽ ባይናገሩም ሴት ተማሪዎች ፀጉራቸዉን ተሸፋፍነው መማር አይችሉም የሚል መመሪያ እንዳላቸዉና በመመሪያው መሰረት ፀጉር መሸፋፈኛና ጌጣጌጥ ለብሶ መማር አይቻልም በማለት አጭር ምላሽ ሰጥተውን ስልኩን ዘግተውብናል።

ርዕሰ መምህሩ ምንም እንኳን ሂጃብ መልበስ አልከለከልንም ቢሉም ፀጉራቸውን ሸፍነው የሚማሩት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች እንደሆነ‍ም ይታወቃል።

በዚህ ጉዳይ ወደ አክሱም ከተማ ከንቲባ ወደሆኑት አቶ አበበ መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ የእጅ ስልካቸው ላይ ብንደውልም ስልካቸው ባለመመለሱ ምክንያት ሀሳባቸውን ማካተት አልቻልንም።

© ሀሩን ሚዲያ

#ᴊᴏɪɴ_and_share_ᴏᴜʀ_ᴘᴀɢᴇ

@islam_in_school


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ሰቆቃ‼
==========================

✍ ሙስሊም በመሆን ብቻ ንጹሐን የሚጨቆኑባትና መብታቸው የሚረገጥባት የትግራይዋ አክሱም!

ጸጉራችሁን ገልጣችሁ ካልተማራችሁ መማር አይቻልም ከተባሉት የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች መካከል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ የማትሪክ ፈተና ፎርም መሙላት አልቻሉም። ፎርም መሙላት የሚቻለው ደግሞ ዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 16 ድረስ ነበር።

ስለዚህ ሙስሊም ስለሆኑ ብቻ በግልፅ ከትምህርት እንዲያቋርጡ ተደርገዋል። ይህን የፈጸሙት አካላት የሙስሊሞችን ጸጉር ማየት አምሯቸው አይደለም፤ ይልቁንም ሙስሊም መሆናቸው አስጠልቷቸው ነው። ጸጉራቸውን ገልጠው ቢገቡ እንኳ አሁንም ሌላ ከትምህርት ማስቆሚያ ዘዴ ከመፈለግ ወደ ኋላ አይሉም። ለዛም ነው ሙስሊሞች ከናካቴው በማይደራደሩበት የሒጃብ ጉዳይ የመጡት። እያወራን ያለነው ስለ ኒቃብ ወይም ጂልባብ ሳይሆን ስለ ትንሿ ሒጃብ ነው።

የመቃብርና የመስጅድ ቦታ መነፈጋቸው ሲገርመን፤ ጭራሽ ጸጉር ሸፍነው መሄድ ተከለከሉ። ኡማውና ተቋሙ ግን እስካሁን ጥልቅ እንቅልፍ ላይ ነው። እስከዛሬ «ተቋም ቢኖረን!» እያልን ነበር መሰል ነገሮችን ስንመለከት። ግና አሁን ተቋምም አለን ብለን ከጭቆና ሊታደገን አልቻለም።

@islam_in_school


ነገ ሀሙስ ነው ከቻልን እንፁም አልቻልን ሌሎችን እናስታውስ 😊


ᴊᴏɪɴ and share ᴏᴜʀ ᴘᴀɢᴇ

@islam_in_school


💜 ወፍ የፈለገ ያህል ሰማይ ላይ
ብትበርና ብትበር መሬት ላይ
ማረፏ አይቀሬ ነው‥
๏ የሰው ልጅም የፈለገ ያህል
ቢኖርና ቢኖር መሞቱ አይቀሬ ነው ።
አላህ አሟሟታችንን ያሳምርልን

#መልካም_ቀን

#ᴊᴏɪɴ_and_share_ᴏᴜʀ_ᴘᴀɢᴇ

          @islam_in_school

Показано 20 последних публикаций.