መንግስት የግለሰብ መሬት ለሕዝብ ጥቅም የሚፈልግ ከሆነ ቀድሞ ተገቢውን ካሳ የመክፈልና ተተኪ መሬት
የመስጠት ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ
የሕ/መ/ጉ/አ/ጉባኤ መዝገብ ቁጥር 1151/06እና የፌ/ም/ቤት ግንቦት 15 ቀን 2008 ዓ.ም (አመልካች......)
አመልካቾች የዳኝነት ጥያቄ ከቤተሰቦቻችን በውርስ ያገኘነው የገጠር መሬት የመንገዶች ባለስልጣን ለልማት ወስዶ ድንጋይ ሲያወጣ ቆይቶ ሲለቅ በእጃችን ገብቷል፡፡ ከዚህ በኃላ 1ኛ ተጠሪ የነበረው ድርጅት ማዕድን ለማውጣት ፍቃድ ወስጄበታለሁ በማለት ሁከት ስለፈጠረ ይዞታውን ይልቀቅልን የሚል ነበር፡፡ ክርክሩን የተመለከቱት በየደረጃው ያሉት ፍርድ ቤቶች አመልካቾች ክሱን ለማቅረብ መብት የላቸውም በማለት ወስነዋል፡፡ ጉባኤውም ሆነ ምክር ቤቱ የመሬት ይዞታው ባለቤትነት መብትን ከሚመለከታቸው የተለያዩ አካላት ካጣሩ በኃላ መሬቱ የአመልካቾች መሆኑን ማረጋገጥ ችለዋል፡፡ መሬቱ የአመልካቾች እስከሆነ ድረስ መንግስት መሬቱን ለልማት የሚፈልግ ከሆነ በቅድሚያ ተገቢውን ካሳ የመክፈል እና ተተኪ መሬት የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ ይህ ሳይደረግ የአመልካቾች መሬት መውስድ ስለማይቻል አመልካቾች በመሬቱ ላይ ያላቸው ሕገ መንግስታዊ ያለመፈናቀል መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባል ሲል በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 40 ንኡስ አንቀፅ 4 እና 8 መሰረት ወስኗል፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔዎች ማጠቃለያ እና ማብራሪያ ከሚል መጽሐፍ የተወሰደ በያደታ ግዛው ( 2016 ዓ.ም )
ለበለጠ መረጃ ግሩፓችንን ይቀላቀሉ👇
http://t.me/Judge1234